2. ሸሀዳ

ዕራ 2

ሸሀዳ

እንዴት ነው ሙስሊም መሆን የሚቻለው?

ኢስላም  የሚለው የአረብኛ ቃል መገዛት የሚል ትርጓሜ አለው፡፡ ሙስሊም የሚለው የአረብኛ ቃል  የተገዛ የሚል አቻ ትርጓሜ አለው፡፡ ይሄኛው መገዛት ምን ማለት ነው? በቁርአን ላይ ስለ አላህ የተቀመጠው  ትልቅ ስዕላዊ  መግለጫ ሁሉን የሚገዛ ጌታ፣ በሁሉም ነገር ላይ ሙሉ በሙሉ ስልጣን ያለው የሚል ነው ነው፡፡ ወደ እስልምና መግባት ማለት ለአላህ ለመገዛት መስማማት ማለት ነው፡፡ ይሄም ደግሞ የሚደረገው ሸሀዳን (የእስልምና የእምነት አንቀጽን) በማነብነብ ነው፡፡ ይኸውም -

አሽሃዱ አነ ኢላሃ ኢላ አላህ

አሽሃዱ አነ መሐመደን ረሱል አላህ

ከአላህ በቀር  ምንም አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ መሐመድም  የአላህ መልዕክተኛ እንደሆኑ እመሰክራለሁየሚል ነው፡፡  

ሸሀዳን ተቀብለህ ለራስህ ብታነበንብ በአጭር ቃል ሙስሊም ሆነሃል ማለት ነው፡፡ እነዚህ ጥቂት ቃላት ብቻ ቢሆኑም አንድምታቸው በጣም ሰፊ ነው፡፡ ሸሀዳን ማነብነብ መሐመድ በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ያንተ መሪ ይሆን ዘንድ የቃል ኪዳን አዋጅ ነው፡፡ ሙስሊም መሆን (የተገዛ መሆን) ማለት መሐመድን ለእያንዳንዱ የሕይወት ምዕራፍ መመርያን እንደሚሰጥ የመጨረሻ እና ልዩ የአላህ መልዕክተኛ መቀበል ማለት ነው፡፡  የመሐመድ መመርያዎች የተገኙት ከሁለት ምንጮች ነው፡፡ ሁለቱም በእስልምና የመጽሐፍ ጥቅልል ውስጥ በአንድ ላይ ይገኛሉ፡፡

§  ቁርአን- ለመሐመድ ከአላህ የተገለጠለት መጽሐፍ ነው፡፡

§  ሱና- የመሐመድ ምሳሌዎች ማለትም

አስተምህሮቶቹ- ተከታዮቹ እንዲያደርጉት ያስተማራቸው

ድርጊቶቹ- መሐመድ ያደረጋቸው ተግባራት

የመሐመድ ምሳሌነቶች ለሙስሊሞች በሁለት  ዋና ቅርፆች ተመዝግበው ይገኛሉ፡፡ አንደኛው የሐዲስ ስብስብ ማለትም መሐመድ ያደረጋቸው እና የተናገራቸው በትውፊቶች ተመዝግበው ያሉ ሲሆኑ ሌላው ቅርፅ ሲራዎች የሚባሉት ናቸው፡፡ እነርሱም የመሐመድን የህይወት ታሪክ በቅደም ተከተል አስቀምጠው የያዙ ናቸው፡፡

የመሐመድ ባህርይ

የመሐመድ ምሳሌነቶች ልንከተላቸው የሚገቡ ናቸውን? የመሐመድ አንዳንድ የሕይወቱ ክፍሎች አዎንታዊ ሲሆኑ ሌሎች የሚደነቁ፣ በጣም አስደሳች እና ፍጹም ማራኪ ናቸው፡፡ በየትኛውም የስነምግባር ደረጃ ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል ስህተት የሆኑ የታሪክ ተከታይ ሁኔታዎችም አሉ፡፡ በሲራዎች እና በሐዲስ አስደንጋጭ የሆኑ ሁነቶችን መመልከት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ያህል ግድያ፣ ስቃይ፣ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል እና ሙስሊም ባልሆኑት ላይ ሽብርን ማነሳሳትን ያጠቃልላል፡፡

እነዚህ ጽሑፎች መሐመድ እንደ ግለሰብ ማን እንደነበር እንደ ማስረጃ ሆነው የሚረብሹን ብቻ አይደሉም፡፡ ይኼ ደግሞ  ለሁሉም ሙስሊሞች  እንደምታ አለው፡፡ የመሐመድ ምሳሌዎች በቁርአን መሰረት በአላህ ተገቢ የተደረጉና ሰዎች ሊከተሏቸው የሚገቡ የላቁ ምሳሌዎች ናቸው ስለዚህም በሙስሊሞች እንደ መለክያ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፣ ጥቅም ላይ ሲውሉም ነበር፡፡

ከሁሉም በላይ በሸሀዳ የታሰረ ማንኛውም ግለሰብ እነዚህን የመሐመድ ምሳሌዎች ሊከተላቸው እና ባህርያቶቹን የበለጠ ሊወርሳቸው ግድ ነው፡፡ የዚህ መሰረት በሸሀዳ እወጃ ውስጥመሐመድም የአላህ መልዕክተኛ ናቸውየሚለው ነው፡፡ ይሄንን በንግግር መድገም መሐመድን የህይወትህ መሪ አድርጎ መቀበል ማለት ነው፡፡

በቁርአን ውስጥ መሐመድን ዋና ምሳሌ አድርጎ መከተል ለተከታዮቹ ሁሉ ግዴታ እንደሆነ ተነግሯል፡

መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡ ከትእዛዝም የሸሸ ሰው (አያሳስብህ)፡፡ በእነሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና” (480)

አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝም ሰው፣ አላህንም የሚፈራና የሚጠነቀቀው ሰው፤ እነዚያ እነርሱ ፍለጎታቸውን የሚያገኙ ናቸው፡፡” (2452)

የመሐመድን ትዕዛዝ እና ምሳሌ መቃወም አለማመን ነው፡፡ ይሄም ደግሞ በቀጣይ ዘመን ወደ ህይወት ውድቀት እና ወደ ገሃነመ እሳት ይመራል፡፡ ይሄም እርግማን በቁርአን በሙስሊሞች ላይ ተደንግጓል፡

ቅኑም መንገድ ለርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምዕመኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም በተሾመበት ጥመት ላይ እንሾመዋለን) ገሀነምንም እናገባዋለን መመለሻይቱም ከፋች!” (4115)

አላህ ከከተሞቹ ሰዎች (ሀብት) በመልክኛው ላይ የመለሰው (ሀብት) ከናንተ ውስጥ በሀብታሞቹ መካከል ተዘዋዋሪ እንዳይሆን ለአላህና ለመልክተኛው ለዝምድና ባለቤትም አባት ለሌላቸው ልጆችም ለድኾችም ለመንገደኛም (የሚሰጥ) ነው፤ መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት ከርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፤ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡” (597)

ከአላህ የኾነ ማድረስን መልዕክቶቹንም በስተቀር (አልችልም) አላህንና መልክተኛውንም የሚያምጥ ሰው ለርሱ የገሀነም እሳት አልለው በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ” (7223)

ቁርአን መሐመድን የሚቃወም ማንኛውንም ሰው የመዋጋት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡

ከነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡት ሰዎች እነዚያን በአላህና በመጨረሻው ቀን የማኑትን አላህና መልክተኛው እርም ያደረጉትን እርም የማያደርጉትን እውነተኛውንም ኃይማኖት የማይቀበሉትን እነርሱ የተዋረዱ ኾነው ግብርን በእጆቻቸው እስከሚሰጡ ድረስ ተዋጉዋቸው” (929)

ጌታህ ወደ መላዕክቱ እኔ (በርዳታዬ) ከናንተ ጋር ነኝና እነዚያን ያመኑትን አጥናኑ፤ በነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ ከአንገቶችም በላይ (ራሶችን) ምቱ ከነርሱም የቅርንጫፎችን መለያያ ሁሉ ምቱ ሲል ያወረደውን (አስታውስ) ይህ እነርሱ አላህንና መልክተኛውን ስለተቃወሙ ነው፡፡ አላህንና መልክተኛውንም የሚቃወም ሁሉ አላህ ቅጣቱ ብርቱ ነው፡፡” (812-13)

ቁርአን፡- የመሐመድ የግል ሰነድ

ነገሮችን  የሚረዱ ሙስሊሞች እንደሚያምኑት ከሆነ ቁርአን ፍጹም የሆነ የአላህ መገለጥ ያለበት፣ የሰው ልጆችን በአላህ አማካይነት የሚመራ፣ ለመልክተኛው መሐመድ የወረደ መልዕክት ነው፡፡ መልክተኛውን የምትቀበል ከሆነ መልዕክቱን መቀበል ግድ ነው፡፡ ስለሆነም ሸሀዳ ሙስሊሞችን በቁርአን እንዲያምኑ እና እንዲታዘዙት ያስገድዳል፡፡ ሊሰመርበት የሚገባው ቁልፍ ሀሳብ ቢኖር በቁርአንና በመሐመድ መካከል ያለው ቅርበት የጀርባ አጥንት እና የሰው አካል ያህል መሆኑ ነው፡፡

ሱና በሰው አካል ሲመሰል ቁርአን ደግሞ በጀርባ አጥንት እንደማለት ነው፡፡ አንዳቸው ያለ አንዳቸው መቆም አይችሉም፡፡ አንደኛውን ያለ አንደኛው መረዳት አይቻልም፡፡

ኢስላማዊ ሸሪኣ፡- ሙስሊም የሚኮንበት መንገድ

የመሐመድን ትምህርት እና ምሳሌነት ለመከተል ሙስሊሞች ቁርአን እና ሱናን መመልከት አለባቸው፡፡ ይሁንና እነዚህ መጽሐፍት ለአብዛኞቹ ሙስሊሞች ውስብስብ ለመረዳት እና  በራሳቸው ለመጠቀም አዳጋች ናቸው፡፡ ቆየት ባሉት የእስልምና ምዕተ ዓመታት  የመሐመድን ሱና  በሚስጥር መያዝ እና ማደራጀትን በተመለከተ አብዛኞቹ ሙስሊሞች እምነታቸውን ያደረጉት ጥቂት በሆኑ ሊቆች ላይ እንደነበር ለእስልምና የኃይማኖት መሪዎች ግልፅ ሆኖላቸዋል፡፡ ቁርአንንም የሚመሩበት ህግ እንዲሆን በስልት እና ወጥነት ባለው መልኩ እንዲደራጅ አድርገዋል፡፡  ስለሆነም ቁርአን እና የመሐመድን ሱና መሠረት በማድረግ  የእስልምና የሕግ አዋቂዎች ከዚህ ያወጡት ሀሳብ ሸሪኣ ወይንም እንደ እስላም የሚኖሩበት ሀሳብ ነው፡፡

እስላማዊው ሸሪኣ የመሐመድ ሸሪኣ ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያቱ ደግሞ መሠረቱ የመሐመድ ትምህርት እና ምሳሌ ስለሆነ ነው፡፡ ይህ የሕግ ሥርዓት አጠቃላይ የህይወትን መንገድ የሚገልጽ ነው፡፡ ያለ ሸሪኣ እስልምና የሚባል ነገር የለም፡፡

የመሐመድ ሱና  ለሸሪኣ ህግ መሠረት በመሆኑ ምክንያት እርሱ ያደረገውን እና በሐዲስና በሲራ የተመዘገበውን እያንዳንዱን ጥቃቅን ነገር ቸል አለማለት አስፈላጊ ነው፡፡ ስለ መሐመድ አለማወቅ ስለ ሸሪኣ አለማወቅ ማለት ነው፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ በእስልምና ስር የሚኖሩትን ሰዎች ሰብአዊ መብት ያለማወቅ ማለት ነው፡፡ መሐመድ ያደረገውና የሸሪኣ ህግም ሙስሊሞችን የሚያዘው በመቶ ሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሙስሊሞችም ሆነ ሙስሊም ባልሆኑ ሰዎች ህይወት ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ የመሐመድ ህይወት እና አሁን ያሉ ሰዎች ግንኙነት ቀጥተኛ ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ሲበዛ የበረታ እና አስፈላጊ ሆኖ ይኖራል፡፡

ስለ ሸሪኣ ህግ መታወቅ ያለበት ሌላው ነገር ቢኖር በፓርላማ የፀደቀው እና በህዝብ ተቀባይነት ያገኘው ህግ ሊለወጥ የሚችል ሲሆን የሸሪኣ ህግ ግን መለኮታዊ ሥልጣን ያለው ፍጹም  እና ሊለወጥ የማይችል መሆኑ ነው፡፡ እንደ ሁኔታው ሊለወጡ የሚችሉ አዳዲስ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ሙስሊም የሸሪኣ ሊቃውንት ሸሪኣ እንዴት በተግባር መተርጎም እንዳለበት ለመወሰን ምክንያትንና ንጽጽሮችን ይጠቀማሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ለውጦች የዳር ዳር እና ዋናውን የማይነኩ ናቸው፡፡

የስኬት ተስፋ

እስልምና ትክክለኛውን ምሪት ማግኘትን በተመለከተ የሚያስበው ምንድን ነውለአላህ ለሚገዙ እና ምሪቱን ለሚቀበሉ  በህይወታቸውና በቀሪው ዘመናቸው ስኬት ታስቦላቸዋል፡፡ ወደ እስልምና መጠራት ማለት ወደ ስኬት መጠራት ማለት ነው፡፡ ይሄም የስኬት ጥሪ በአዛን ጊዜ ማለትም ለሰላት ጥሪ በሚደረግበት ጊዜ በቀን አምስቴ ይታወጃል፡፡

አላህ ታላቅ ነው! አላህ ታላቅ ነው!

አላህ ታላቅ ነው! አላህ ታላቅ ነው!

ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ

ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ

መሐመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆኑን እመሰክራለሁ

መሐመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆኑን እመሰክራለሁ

ለማምለክ ! ለማምለክ !

ወደ ስኬት ! ወደ ስኬት !

አላህ ታላቅ ነው! አላህ ታላቅ ነው!

አላህ ታላቅ ነው! አላህ ታላቅ ነው!

ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡

የስኬት አስፈላጊነት ዋና ነገር መሆኑን ቁርአን አፅንዖት በመስጠት ይናገራል፡፡ የሰው ልጆችን አሸናፊዎችና የተቀሩት በማለት በሁለት ይከፍላቸዋል፡፡  የአላህን ምሪት በተደጋጋሚ የማይቀበሉትን የከሰሩ  በማለት ይጠራቸዋል፡፡

ከኢስላም ሌላ ኃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎች ነው፡፡” (385)

ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፤ በእርግጥም ከከሃዲዎቹ ትኾናለህ ማለት ወደ አንተም ወደነዚያም ካንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል፡፡” (3965)

ስኬትንና ውድቀትን በተመለከተ እስልምና ብዙ ማውራቱ ብዙዎቹ ሙስሊሞች እስልምናን ካልተቀበሉት የተሻሉ እነደሆነ በኃይማኖት ትምህርት ቤቶቻቸው ይማራሉ ማለት ነው፡፡ ኃይማኖታቸውን ያጠበቁ ሙስሊሞች ካላጠበቁት ይልቅ የተሻሉ እንደሆኑ ይነገራቸዋል፡፡

የተከፈለ ዓለም

በየምዕራፎቹ እንደምንመለከተው ስለ ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን ስለሌላ እምነት ተከታዮችም ቁርአን ብዙ የሚናገራቸው ነገሮች አሉት፡፡ የእስልምና ህግ ሙዳየ ቃላቶች እንደሚያመለክቱት አራት ዓይነት ሰዎች ይገኛሉ፡፡

1)    የመጀመርያና ዋናዎቹ እውነተኛ ሙስሊሞች ናቸው፡፡

2)    ግብዞች ተብለው የሚጠሩ ሌሎች ቡድኖች አሉ ከሙስሊሞች ያፈነገጡ ናቸው፡፡

3)    ጣዖት አምላኪዎች  ከመሐመድ በፊት  የበላይነት የነበራቸው ቡድኖች ናቸው፡፡ ጣዖት አምላኪዎች ለሚለው ቃል አቻውሙሽሪክየሚል ሲሆን ሸሪክ ማድረግ የሚል ትርጓሜ አለው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ማንኛውም ወይንም የትኛውም ነገር አላህን ይመስላል ማለት ነው፡፡

4)    የመጽሐፉ ሰዎች የሚባሉት ሙሽሪክንዑስ ቡድን ናቸው፡፡  ምክንያቱም ቁርአን ክርስቲያኖችንና አይሁዶችን ሸሪክ የፈጸሙ ሲል ይከሳቸዋልና፡፡

የመጽሐፉ ሰዎች የሚለው ፅንሰ ሀሳብ ክርስትናና የአይሁድ ኃይማኖት ተመሳሳይነት ያላቸውና ከእስልምና የተገኙ መሆናቸውን ያመለክታል፡፡ እስልምና የአይሁድና የክርስትና ኃይማኖት መገኛ፣ እናት ኃይማኖት ነው፡፡ እንደ ቁርአን አስተምህሮ ከሆነ ክርስትናና የአይሁድ ኃይማኖት ከመጀመርያው በአንድ አምላክ የሚያምኑ ነበር ማለትም በሌላ አነጋገር ሙስሊም ነበሩ፤ ነገር ግን ቅዱሳት መጽሐፍቶቻቸው ስህተት የገባባቸውና የተለወጠ ስለሆነ መቼም ቢሆን እውነተኛ ሊሆን አይችልም የሚል ዕሳቤ አለው፡፡ ይሄ ማለት ክርስትናና የአይሁድ ኃይማኖት መገኛቸው እስልምና ሆኖ እውነትን ያዛቡ፣ ያጣመሙ ናቸው ተከታዮቻቸውም በስህተት ጎዳና እየነጎዱ ናቸው ብሎ ያስተምራል፡፡  ከዚህ በተጨማሪም ክርስቲያኖችና አይሁዶች መሐመድ መጥቶ ቁርአን እስኪወርድለት ድረስ ከጨለማ መላቀቅ አልቻሉም ሲል አስተምህሮቱን ያስቀምጣል፡፡

እነዚያ ከመጽሐፉ ባለቤቶች ከአጋሪዎቹም የካዱት ግልጹ አስረጅ እስከመጣላቸው ድረስ (ከነበሩበት ላይ) ተወጋጆች አልነበሩም፡፡” (981)

መሐመድ ለክርስቲያኖችና ለአይሁዶች አለመረዳታቸውን ለማስተካከል የመጣ የአላህ ስጦታ ነበር፤ ስለሆነም መሐመድን የአላህ መልዕክተኛ ቁርአንን ደግሞ የመጨረሻው መገለጥ አድርገው መቀበል እንዳለባቸው ያሳስባል፡፡ (515 5728 447)

ቁርአን ስለ ክርስቲያኖችና አይሁዶች አዎንታዊ የሆነ እና አሉታዊ የሆነ አስተያየት አለው፡፡ አዎንታዊ በሆነው ብርሃን ስንመለከት አንዳንድ ክርስቲያኖችና አይሁዶች ታማኞችና እውነተኛ አማኞች ናቸው ሲል ሀሳብ ይሰጣል (3113-114)፡፡ ቢሆንም በዚሁ በተመሳሳይ ምዕራፍ እንደምናገኘው የነዚህ ሰዎች እውነተኛነት የሚፈተነው ሃቀኞቹ ሙስሊሞች ወደመሆን በመምጣታቸው ነው (3199)፡፡

ምንም እንኳ ክርስቲያኖችና አይሁዶች በአንድ ምድብ ውስጥ ሆነውየመጽሐፉ ሰዎችቢባሉም አይሁዶች በቁርአን ላይ የበለጠ በአሉታዊ ጎናቸው ተገልጸዋል፡፡ እንደ ምሳሌ አድርገን ብንወስድ ቁርአን ሙስሊሞችን ከመውደድ አንፃር ክርስቲያኖች ቀረብ የማለት አዝማምያ ሲያሳድሩ አይሁዶችና ጣዖት አምላኪዎች ግን በሙስሊሞች ላይ ብርቱ የሆነ ጠላትነት አለባቸው ሲል ያስተምራል (582)፡፡ ቢሆንም  የቁርአንን የመጨረሻ ፍርድ በምንመለከትበት ጊዜ በተመሳሳይ መልኩ ለክርስቲያኖችም ሆነ ለአይሁዶች አሉታዊ የሆነ አመለካከት አለው፡፡ ተቃውሞ ቁልፍ በሆኑ ስነ መለኮታዊ ንግግሮች ውስጥ የተገለጠ ሲሆን እምነታቸውን በትክክል በሚከተሉ ውስሊሞች የዘወትር ጸሎትም ውስጥ እንዲሁ ተካቶአል፡፡

የእለት ጸሎቶች

በቁርአን እጅግ የታወቀው ምዕራፍ አል-ፋቲሃ (የመክፈቻ ምዕራፍ) የሚለው ነው፡፡ ይህንን ምዕራፍ በየእለት ጸሎት መደጋገም ግዴታ ነው፡፡ እያንዳንዱ ጸሎት በስግደት ጊዜ የሚደገም ነው፡፡ አንድ በእምነቱ ታማኝ የሆነ ሙስሊም እነዚህን ጸሎቶች በቀን 17 ጊዜና በዓመት 5,000 ጊዜ በላይ መድገም ይኖርበታል፡፡

አል -ፋቲሐህ ምሪት የሚጠየቅበት ጸሎት ነው፡፡

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

ምስጋና ለአላህ ይግባው የዓለማት ጌታ ለሆነው፤

እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ

የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው

አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታ እንለምናለን

ቀጥኛውን መንገድ ምራን

የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸው

በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና

ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን በሉ)፡፡

ይህ  ሙስሊሞች መንገዳቸው እንዲቀናና አላህ እንዲመራቸው የሚጠይቁበት የጸሎት ጥያቄ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ መመራትን አስመልክቶ ከልብ የሆነ እውነተኛ መልእክት ነው፡፡ ነገር ግን የአላህን ቁጣ የሚቀበሉ ወይንም ከትክክለኛው መንገድ ርቀው በስህተት ጎዳና ያሉት  እነማን ናቸው? እጅግ ብዙ ሙስሊሞች በህይወት ዘመናቸው በየእለቱ በሚያደርጉት ጸሎት መቶ ሺህ ጊዜ መጥፎ ስም የሚሰጥዋቸው እነዚህ ሰዎች ማን ይሆኑ ይሆን? መሐመድ የዚህን ምዕራፍ ትርጓሜ እንዲህ ሲል ግልፅ አድርጓል፡፡አይሁዶች ቁጣ የሚገባቸው ሲሆኑ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዳተኞች ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ሙስሊም በየቀኑ የሚጸልየው ጸሎት በአላህ ቁጣ ክርስቲያኖችና አይሁዶች እንዲወገዱ የሚል ትኩረት ያዘለ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

ሙስሊም ያልሆኑት ሊያውቁት የሚገባ ነገረ መለኮታዊ ጥያቄ

ከተከበረ መንፈሳዊ ስርኣት በመዘለለ ቁርአንና ሱና የሚከተሉትን ያስተምራሉ

1)    በአላህ ላይ ሸሪክ ማድረግን አጥብቀው የፈጸሙ፣ በመሐመድና በአንድ አምላክ ባለማመናቸው የቀጠሉ ክርስቲያኖችና አይሁዶች ማለትም ወደ እስልምና ያልተለወጡት የሚጠብቃቸው ገሃነም ነው፡፡

2)    ሙስሊሞች ከሌሎች ህዝቦች የበላይ ናቸው፡፡ የተለዩ ህዝቦች ናቸው፡፡ ሚናቸውም እኩይና ሰናይ የሆኑትን  ማስተማር  ማለትም የትኛው ነው የሚያስከብረው፣ የተከለከለው፣ አሳፋሪ የሆነው ምንድን ነው የሚሉትን ማስተማር ነው፡፡  (3110)

3)    የእስልምና እድል ፈንታ በሌሎች ኃይማኖቶች ላይ የበላይ ሆኑ መግዛት ነው፡፡ (4828)

4)    የበላይ የመሆንን ሀሳብ ወደ ስኬት ለማምጣት ሙስሊሞች በክርስቲያኖችና በአይሁዶች ላይ (በመጽሐፉ ሰዎች ላይ) ጦርነትን ይከፍታሉ፡፡ ይህ የሚሆነው ደግሞ እስኪሸነፉ፣ ራሳቸውን በትህትና ማዋረድ እስከሚችሉ እና ለሙስሊሙ ማህበረስብ ግብር መገበር እስከሚችሉ ድረስ ነው፡፡  

ከነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡት ሰዎች እነዚያን በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን አላህና መልዕክኛው እርም ያደረጉትንም እርም የማያደርጉትንና እውኛውንም ኃይማኖት የማይቀበሉትን፤ እነርሱ የተዋረዱ ኾነው ግብርን በእጆቻቸው እስከሚሰጡ ድረስ ተዋጓቸው” (9 29)

5)    በመጨረሻው ዘመን የአይሁድ እምነትና ክርስትና ይጠፋሉ፡፡ መሐመድ እንዳስተማረው ከሆነ ዒሳ (የሙስሊሞች ኢየሱስ) ወደ ምድር በሚመለስበት ጊዜ ክርስትናን ከምድረገጽ ያጠፋል (መስቀልን ይሰብራል፡፡) ክርስቲያኖች ኢስላማዊውን ህግ ታግሰው እስከመጨረሻው እንዲገዙ ያደርጋል፡፡ የሙስሊም ምሑራን ሐዲሱን እንደሚተረጉሙት  ከሆነ  የሙስሊሞች ነብይ የሆነው ዒሳ ሁሉንም ክርስቲያኖችና  የሌሎች እምነት ተከታዮችን በሰይፍ በመጠቀምም ቢሆን ወደ እስልምና እንዲለወጡ ያስገድዳቸዋል፡፡

6)    ከላይ ለመግለጽ ከተሞከረው በተጨማሪ  አይሁዶችን አስመልክቶ እጅግ ብዙ  የተለዩ ነገረ መለኮታዊ አስተሳሰቦች አሉ፡፡  መሐመድ እንዳስተማረው በመጨረሻው ዘመን ድንጋይ ድምጽ በማሰማት ሙስሊሞች አይሁዶችን እንዲገድሉ ይረዳቸዋል፡፡

የተፈቀደ ማታለል

ኢስላማዊ ሸሪኣን አስመልክቶ ችግር ያለበት አንዱ አመለካከት ውሸትና ማታለልን የተመለከተ ነው፡፡ በእስልምና መዋሸት እጅግ ከባድ ኃጢአት ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ነገር ግን የመሐመድን ምሳሌ መሰረት በሚያደርጉ የሙስሊም ሊቃውንት ውሸት የሚፈቀድባቸው አንዳንድ ሁኔታዎች እንዳሉ ይታመናል፤

ሙስሊሞች እንዲዋሹ የሚፈለግበትና የሚጠየቁበት በዛ ያሉ የተለዩ ሁኔታዎች አሉ፡፡ በሳሂህ አል ቡኻሪ ውስጥ በሚገኝ አንድ ምዕራፍ ላይ በህዝቦች መካከል ሰላምን የሚያሰፍን ውሸታም አይደለም ይላል፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ የመሐመድን ምሳሌ በምንመለከትበት ጊዜ ለሙስሊሞች እንዲዋሹ የሚፈቀድበት ሁኔታ ቢኖር ሰዎችን በሚያስታርቁበት ጊዜ ነው፡፡ ምክንያቱም ውጤቱ አዎንታዊ ስለሚሆን ነው፡፡ የህጋዊ ማታለል ሌላው አውድ ሙስሊሞች ሙስሊም ባልሆኑት ሰዎች አደጋ ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ የሚያደርጉት መዋሸት ነው (328)፡፡ ከዚህ ክፍል የምንወስደው ታቂያ የሚለውን  ፅንሰ ሀሳብ ነው፡፡ ይሄም የሚያመለክተው ሙስሊሞችን ከመታደግ አንፃር ስለሚደረግ ውሸት ነው፡፡

የሙስሊም ምሑራን የደረሱበት ድምዳሜ ቢኖር ሙስሊም ያልሆኑት የፖለቲካውን ስልጣን የበላይነት በሚያገኙበት ጊዜ እራስን ከመጠበቅ አንፃር ወዳጅነትንና መልካምነትን ማሳየት ለሙስሊሞች ጠቀሜታ አለው፡፡ ስለሆነም ጠላቶቻቸውን በልባቸው ይዘው በእምነታቸው መፅናት አለባቸው፡፡ የዚህ አስተምህሮ አንዱ እንድምታ እንደሚያሳየው ታዛቢ ሙስሊሞች የፖለቲካ ስልጣናቸው እየጨመረ በሄደ ቁጥር ሙስሊም ላልሆኑት ህዝቦች የሚኖራቸው የወደጅነት ስሜት እየቀነሰና በእነርሱ ላይ የሚኖራቸውም እምነት ምጸታዊ እየሆነ ይመጣል፡፡

የሸሪኣ ህግ ሙስሊሞችን እንዲዋሹ የሚያበረታታበት ሌሎች ሁኔታዎች በባልና በሚስት መካከል የጋብቻን ጥምረት ለማስቀጠል፣ ክርክሮችን ለመፍታት ጥረት በሚደረግበት ጊዜ፣ እውነቱን መናገር ራስን ለአደጋ ሊያጋልጥ በሚችልበት ሁኔታ ውስጥ፣ አንድ ሰው የግል ሚስጥሩን ሲነግረን እና በጦርነት ወቅት ነው፡፡

በአጠቃላይ ውሸትን በተመለከተ እስልምና የሚያስተምረውውጤቱ የተጠቀምክበትን መንገድ ያጸድቃልበሚል መርህ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ አንዳንድ ምሑራን የተለያዩ ውሸቶችን በተመለከተ ደህና የሆኑ መለያዎችን አስቀምጠዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ሙሉ በሙሉ ከመዋሸት የተሳሳተን መረጃ መስጠት የተሻለ ነው ብለው ያምናሉ፡፡

በግብረ ገብነት የተጎዳ ማኅበረሰብ

እንደየሁኔታው የሚለዋወጥ የመዋሸትና እውነትን የመናገር ስነ ምግባር በጣም አውዳሚ ሊሆን ይችላል፡፡ መተማመንን አጥፍቶ ግራ መጋባትን ይፈጥራል፡፡ ሃገራዊና ፖለቲካዊ የሆነውን ባህል ያጠፋል፡፡ ባሎች በተደጋጋሚ ሚስቶቻቸውን የሚያታልሉ ከሆነ በመካከላቸው ያለውን መተማመን ክፉኛ ይሸረሽርና ትዳራቸውን ይጎዳል፡፡ በማኅበረሰብ ደረጃ የሚደረገው ህጋዊው ማታለል አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ያለቸውን የመተማመን ህይወት እንዳይቀጥል እንቅፋት ይሆናል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ግጭቶች እንዲቀጥሉና እርቅን ማድረግ አዳጋች እየሆነ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡  አንድ ሰው እስልምናን በሚተውበት ጊዜ ይህንን የመሐመድ ምሳሌነት መከተል እንደሚያቆም የታወቀ ነው፡፡

እስኪ ስለ ራስህ አስብ

ዕውቀት ከሚደራጅበትና ግልጽ እንዳይሆን ከሚደረግበት አካሄድ የተነሳ በአንዳንድ ርእሰ ጉዳዮች ላይ እስልምና በእርግጥ ምን እንደሚያስተምር ማወቅ አዳጋች ነው፡፡ የእስልምና ዋና ምንጭ ትልቅና ውስብስብ ነው፡፡ የሸሪኣ ህግን አስመልክቶ መረጃዎች እንደ ዋና ምንጭ የተቀዱት ከቁርአንና ከነብዩ መሐመድ ፈለግ ነው፡፡ ሂደቱም በክህሎት የደረጀ እንደሆነ ይታሰባል፡፡ አንድ ሰው ስልጠናዎችን ለመውሰድ እረዥም ጊዜ ሊፈጅበት ይችላል፡፡ አብዛኛዎቹ ሙስሊሞች ግን ይሄንን ማድረግ አይችሉም፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ ተግባራዊ ከሆነ አመለካከት ስንነሳ እምነትን አስመልክቶ ዓላማቸውን ከማሳካት አንጻር ሙስሊሞች ምሪትን የሚቀበሉት  ከምሑራኖቻቸው ነው፡፡ በእርግጥ የእስልምና የህግ አዋቂዎች እምነትን አስመልክቶ ምክር ለሚያስፈልጋቸው ሙስሊሞች ከነርሱ ይልቅ የኃይማኖት ዕውቀት ያላቸውን ሰዎች ማናገር የተሻለ እንደሚሆን ያስገነዝባሉ፡፡ የሸሪኣ ህግን አስመልክቶ ሙስሊሞች ጥያቄ ቢኖራቸው ህጉን በተመለከተ ተገቢ ዕውቀት ያለውን ሰው መጠየቅ ይኖርባቸዋል፡፡

የእስልምና ኃይማኖት ዕውቀት  ሁሉን ነገር በግልጽ ከማስቀመጥ አንፃር  ከመጽሐፍ ቅዱስ   አስተምህሮ ጋር የተለየ አመለካከት ያለው ነው፡፡  በእስልምና አንዳንድ ነገሮች መገለጽ የለባቸውም ከተባለ ወይንም ደግሞ እነዚህ ነገሮች ኢስላምን መልካም ባልሆነ ብርሃን የሚገልጹ ከሆነ ለውይይት እንዲቀርቡ አይደረግም፡፡ ስለ እስልምና ያለው መረጃ ለማወቅ አስፈላጊ ነው ወይንስ አይደለም በሚል ጥያቄ ላይ ተመስርቶ እንደየሁኔታው ግልጽ ይደረጋል፡፡

ይህ ማለት ግን አሁን ያሉት ሙስሊሞችም ሆኑ ቀድሞ የነበሩት ስለ ቁርአንም ሆነ ስለ መሐመድ ፈለግ ምንም ዓይነት ግልጽ አስተሳሰብ እንዲያገኙ መብቱ የላቸውም ማለት አይደለም፡፡

አሁን ያለንበት ዘመን ከመቼውም ዘመን ይልቅ የመጀመሪያ የሆኑ ማሳረጃዎችን ማግኘት የሚቻልበት ሁኔታ ስላለ ክርስቲያኖች፣ አይሁዶች፣ እግዚአብሔር የለሾችም ሆኑ ሙስሊሞች  የሚያውቁትን ነገር ለሌሎች ለማሳወቅ ማንኛውንም አጋጣሚ ሊጠቀሙ ይገባል፡፡