አጫጭር ዜናዎች 

ፀረ ክርስትያን ዓመፆች እና “የሰላማዊ” ሙስሊሞች ፀጥታ
በ Piero Gheddo
ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

በግብፅ ውስጥ “በክርስትያን ሰርግ ላይ” ከደረሰው ጥቃት ሁለት ቀናት በኋላ እጅግ በጣም ብዙ ጥቃቶች በተለያዩ አገራት፤ ማለትም በፊሊፒንስ፣ በማዕከላዊ አፍሪካ፣ በማሊ፣ በናይጀሪያ፣ እና በሶሪያ በተከታታይ ተደርገዋል፡፡ በአላህና በቁርአን የሚያምኑ ብዙ ሰዎች ሰላማዊዎች ናቸው እንዲሁም በነፃነትና በሰላም መኖርን ይወዳሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ብዙዎቹ ሰላም ወዳዶች ነን የሚሉት ስለነዚህ ጥቃቶች ተቃውሞ የማያደርጉት ለምንድነው?  የሙስሊሞች ማህበራት ወይንም ቡድኖች  እራሳቸውንና ሌሎችን የሚያጠፉትን እና “የእስላም ሰማዕታት” ነን የሚሉትን ትክክል አይደለም በማለት ተነስተው የማይቃወሙት ለምንድነው?

Milan (AsiaNews) - በቅርብ ቀን ከፊሊፒንስ የተመለሰ አንድ ጣሊያናዊ ሰው የነገረኝ ነገር እንደሚከተለው ነው፡ “ሚንዳኖ በተባለው ትልቅ ደሴት ላይ ብዙ መቶ አክራሪዎች ከደሴቱ ማዕከል እና ከሌሎችም ትናንሽ ደሴቶች ተሰባስበው በሌሊት በመምጣት የዛምቦንጋ ከተማን ዳርቻ አጠቁና ቤቶችንና ጎጆዎችን አቃጥለው ዘረፉአቸው፡፡ ብዙዎችን ገድለውና አቁስለው በርካታዎችን ምርኮና ታጋች አድርገው ወደ መጡበት ተመለሱ፡፡” ጣሊያናዊው የተናገረው፤ “እንደዚያ ዓይነቱ የታቀደ ግድያ፣ ጥቃት፣ ዝርፊያና ጠላፋዎች በጣም ተደጋግመዋል፣ ነገር ግን እንደ አሁኑ ያለ መጠነ ሰፊ ጥቃት በክርስትያኖች ላይ ሲደረግ የመጀመሪያ ሊሆን ይችላል” በማለት ሲሆን፣ “አዲስ ጥቃት ይደረጋል ተብሎ ፍርሃትና ስጋቶች አሉ ነገሮችም ከዚህ በፊት እንደነበሩት በፍፁም ሊሆኑ አይችሉም” ብሎ ነው፡፡ የፊሊፕንስ መንግስት ጦር ሰራዊት ለመላክ ተገዷል ስለዚህም ተጨማሪ ጦርነት፤ የአፀፌታ የበቀል ጥቃቶችና ብዙ ውድመቶች ይጠበቃሉ፡፡ የሰዎች ሕይወትና ኢኮኖሚ ችግር ውስጥ እንደዘቀጠ ብዙዎች ወደ አገሪቱ ሌላ ክፍል ተሰድደዋል፡፡ ከመካከለኛው ምስራቅ አገሮች (ማለትም ከነኩየት) ለዑላማዎቹ፣ ለመስጊዶችና ለቁርአን ትምህርት ቤቶች ወጣቶችን ለማሰልጠንና ክርስትያን መንግስትን በመቃወም እንዲፀኑና “ለእስልምናም መስዋዕት” መሆንን እንዲቀበሉ በርካታ ገንዘብ ይላካል፡፡ ሳላፊስቶች በሚንዳኖ ደሴት ላሉት ለጥቂት ሙስሊሞች የራሳቸው ክልላዊ መንግስት እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ፣ ይህም ማሌያንና፤ ማሌሲያን፤ ቦርኒየንን አደባልቆ አንድ ወጥ የሆነ የእስላም መንግስትን ለመመስረት ነው፡፡ 

እነዚህ ሁሉ በዋና ዋናዎቹ የዜና ማሰራጫዎች ላይ ለመውጣት መንገድን አያገኙም ነግር ግን አሁንም እጅግ በጣም ብዙ ነገር (ውስጥ ውስጡን) አለ፡፡ ከሦስት ቀናት በፊት (በግብፅ በደቡባዊ ካይሮ) ጊዛ በተባለ ቦታ ላይ በክርስትያኖች የሰርግ ስርዓት ላይ ጥቃት ተደርጎ ነበር፣ በቅርቡ በተገኘው መረጃ መሰረት ከዚያም ጥቃት የተነሳ አራት ሰዎች እንዲሞቱና 18 ደግሞ እንዲቆስሉ ተደርጓል ፡፡

በባንግላዴሽ ሰዎች ሁል ጊዜ መቻቻል ያለበትን እስልምና ይደግፋሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የውጭ ሚሽነሪዎችና የካቶሊክ ሴቶች መነኩሴዎች እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል፣ ነገር ግን በቅርብ ዓመታት ብዙ እስላማዊ እንቅስቃሴዎች እና ቡድኖች በጣም በመነሳሳት ላይ ናቸው፡፡ እነርሱም ለባንግላዴሽ መንግስት “የሻሪያ ሕግ” የምድሪቱ ሕግ እንዲሆን ጥሪ እያቀረቡ ነው፣ ይህም አገሪቱን ለቀናት በማቆም እና የማያቋርጥ ሰላማዊ ሰልፍ እና የስራ ማቆም በማድረግ ቀጥሏል፡፡ ይህም ብዙውን ጊዜ የሚሆነው አገሪቱን አስፈላጊ ባልሆነ ብጥብጥ ውስጥ በማስገባት ነው (ተጓዦችና ሰራተኞች ተገድደው ይቆማሉ፣ ይደበደባሉ፣ በስለት ይወጋሉ አንዳንድ ጊዜም ይገደላሉ)፡፡ አናሳ የሆኑት ክርስትያኖች፣ ሒንዱዎችና ቡዲስቶች በከፍተኛ ጫና ውስጥ ናቸው፣ በየዕለቱም የሚደረግባቸው የውሸት ውንጀላ፣ ፍትሕ ያጣ ጭቆና፣ እና ብጥብጥ ችለው ለመኖር ተገደዋል፡፡ የባንግላዴሽ ምርጫም እየቀረበ ባለበት ወቅት ብዙዎች በጣም የባሰ ነገር ይመጣል በማለት ፈርተዋል፡፡

ማዕካለዊ አፍሪካ ሪፑብሊክ በአፍሪካ ውስጥ ካሉትና በጣም ያልተረጋጉት አገራት አንዷ ናት፣ ይህም የሆነው ወደ አገሪቱ ውስጥ ከገቡት የውጭ የሙስሊም “ጋንጎች” የተነሳ ነው (ከናይጀሪያ፣ ከቻድ፣ ከኒዠር፣ እና ከሱዳን) የተውጣጡና፣ ፕሬዚዳንት ቦዚዝን ከስልጣን አስለቅቀው በዋና ከተማዋ በባንጉይ ውስጥ ስልጣን በያዙት ማለት ነው፡፡ Mondo e Missione (October 2013) እንዳቀረበው ከሆነ፣ የሴሌካ ተዋጊዎች ባጠቁበት ጊዜ (አሁን እየመሩ ያሉት እስላሚስቶች)፣ ሆስፒታሎች እና የጤና ማዕከላት ተዘርፈው የጤና ሰራቶኞች በሙሉ ተሰድደዋል፡፡ የጤናው ሁኔታ አስፈሪ ነው፣ በኢስላማዊ ወታደሮች ኢላማ ውስጥ የገቡት ክርስትያኖች ናቸው፡፡ አንድ የወንጌላውያን አገልጋይ እንዳለው፣ “ታስረውና፣ ተደብድቦ፣ ሕይወታቸውን ለማዳን እንዲችሉ ገንዘብ እንዲያስረክቡ ተገድደዋል፡፡ የሴሌካ አማፂዎች የአምልኮ ቦታዎችን አፈራርሰው ዘርፈዋቸዋል፣ ብዙዎችን ገድለው ብዙ መቶ ሺዎችን አካባቢያቸውን ለቀው እንዲሰደዱ አስገድደዋቸዋል፣ ይህም በተለይ ያነጣጠረው በክርስትያኖች ላይ ብቻ ነው”፡፡ በማዕካላዊ አፍሪካ ባሉት አራት ወረዳ ሲኖዶሶች ውስጥ ቢያንስ በየቤተክርስትያኖቹ ውስጥ ያሉት ከግማሽ በላይ የሆነው ንብረታቸው በከፍተኛ ሁኔታ ተዘርፏል፣ ወድሟል ወይንም ተወስዷል፡፡ በሁሉም ቦታ ላይ ሰዎች እየተሰደዱ ነው፡፡ ሜግር ጁዋን ጆሴ አጉሬ፣ የተባለው የባንጋሶ ካህን እንዳለው፣ “ሲቪሎች ይገደላሉ ልጃገረዶች ይደፈራሉ፣ በሲኖዶስና በቤተክርስትያናት ውስጥ ያገኙትን ሁሉ ነገር፣ መኪኖችን፣ ሞተር ባይስክሎችን፣ ማቀዝቀዣዎችን፣ ቴሌቪዥኖችን እና ብርድ ልብሶችንም ጭምር ይወስዳሉ፡፡ ሁሉንም ነገር አውድመዋል ከትምህርት ማዕከላት እስከ ሕፃናት ማስተማሪያ ማዕከላት ቦታዎች ድረስ፡፡ እንዲሁም በቦሆንግ ከተማ ውስጥ ከውጭ የመጡ የሴሌካ ተዋጊዎች የሙስሊም ካልሆኑ ውስጥ አንድ ጎጆ ቤትን እንኳን አላስተረፉም፡፡” በቦሆንግ ሲኖዶስ የተላለፈው መረጃ እንደሚያሳየው፡፡ “በመላ ከተማው ውስጥ የሙስሊም ወገን ቤት ካልሆነ በስተቀር ተመሳሳይ ሁኔታ ብቻ ነው ሊታይ የሚችለው፣ ስለዚህም ጣሪያ የሌላቸው፣ ባዶ ቤቶች እንዲሁም የተቃጠሉ ግድግዳዎች ብቻ ናቸው የሚታዩት”፡፡

ለማለት እስከማያስፈልግ ድረስ በጥቁር አፍሪካ ውሰጥ በሌሎች ቦታዎች የሚደረገው ነገር ምንም ልዩነት የሌለው ነው፡፡ ሰሜን ማሊ ለዓላማና ለዚሁ ሲባል የሚተዳረው በኢስላሚስት ጋንጎች ነው፡፡ ደቡቡ ማሊ ከጥፋት የተረፈው በፈረንሳይ ልዩ ጦር ሰራዊት ጣልቃ ገብነት አማካኝነት ብቻ ነው፡፡ በናይጀሪያ  በቦኮ ሃራም በቤተክርስትያናትና በክርስትያኖች ላይ የሚደርሰው ተደጋጋሚ ጥቃት ያቀረበው ዕቅድ ሙስሊሞች ያልሆኑትን ከሰሜናዊው የናይጀሪያ ክፍል ማባረር ላይ ብቻ ነው፡፡ ባሳለፍነው መስከረም ወር ብቻ ከ500 በላይ የሚሆኑ ክርስትያኖች ለእንደዚህ ያለው ጥቃት ሰለባዎች ሆነዋል፡፡

ምዕራባውያን አገሮች “ይህ እውነተኛው እስላም አይደለም” በማለት እራሳቸውን እያታለሉ ነው፡፡ በእርግጥ እውነተኛው እስልምና ምንድነው? አሸባሪዎችና ሳላፊስቶች ሙስሊሞች ነን ስለሚሉና ይህንንም የሚያደርጉት እስልምናን ደግፈን ነው እስካሉ ድረስ በእስልምና ውስጥ ማዕከላዊውን ስፍራ ይዞ የሚገኘው አሸባሪው እስልምና ብቻ መሆኑ ነው፡፡ በአላህና በቁርአን የሚያምኑ ብዙዎቹ በሰላምና በነፃነት ብቻ ለመኖር እንደሚፈልጉ እኔ አውቃለሁ፡፡ ከኢንዶኔዥያ እስከ ሞሮኮ ድረስ፣ ከሶማሊያ እስከ ሴኔጋል፣ ከሞዛምቢክ እስከ ግብፅ እንዲሁም እስከ ቱርክ እያንዳንዱን የእስላም አገር ጎብኝቻለሁ፡፡ በሁሉም አገር ያሉ ክርስትያኖች መነኩሴዎች ካህናት እንዲሁም የአካባቢ ፓስተሮች ወይንም ጳጳሶች ሁል ጊዜ ተመሳሳይ ነገርን ሲናገሩ ሰምቻለሁ፡፡ አሁንም የመጠየቅ መብቱ አለን፤ ለምንድነው  ሰላማዊዎች ነን የሚሉትና በቁጥር ብዙዎች የሆኑት ሙስሊሞች በእነዚህ አሻባሪዎችና ሁከተኞች ላይ በተቃውሞ የማይነሱት ለምንድነው? የሳላፊስቶችን ሁከትና ብጥበጣ እንዲሁም የአሸባሪዎችን እንቅስቃሴ እና ሌሎችን ለመግደልና “የእስላም መስዋዕት” እንሆናለን በማለት እራሳቸውን የሚያጠፉትን፣ ተነስቶ ትክክል አይደለም በማለት ለመቃወም  አንድም ሙስሊማዊ ማህበር ወይንም ቡድን ያልተነሳው ለምንድነው? በጣሊያን ውስጥ የእምነት ነፃነታቸው የተከበረላቸው ከሁለት እስከ ሦስት ሚሊየን የሚደርሱ ሙስሊሞች ይገኛሉ፡፡ በአካባቢያው ሙስሊሞች የሚደረገውን ስልታዊ ሽብር አንድ ጊዜም እንኳን ተነስተው ያልተቃወሙት ስለምንድነው?

እንደዚህ ዓይነት ጥያቄዎች የታሰቡት ሙስሊሞችን ለማጥቃት አይደለም፡፡ እኔ የጣሊያን ሕዝብ እርግጠኛ እንዲሆንና የምፈልገው፤ ወደ ሶርያ ልዑክ የነበረው Domenico Quirico, La Stampa የተናገረውን የሚከተለውን ነገር  የጣሊያን ሕዝብ እንዳይቀበል ብቻ ነው፡፡ እርሱ በእስላማዊ ጎሪላዎች ለወራት ተይዞ ታግቶ ነበር ቆይቶም ከተለቀቀ በኋላ ሲጽፍ “እኛም ለማስተዋል የማንፈልገው ሞደሬት እስላም የሚባል እንደሌለ፣ የአረብ ስፕሪንግ እንቅስቃሴ እንዳከተመ እና የእርሱ አዲስ ምዕራፍ ያካተተው ኢስላማዊና ጂሃዲስት ዕቅድ ሆኖ ታላቅ የኢስላማዊ ካሊፌት መንግስት መመስረት እንደሆነ ነው፣ ይህም እስላማዊ የፖለቲካ ዕቅድ ተግባራዊ የሚሆነው በሶርያ ውስጥ ሲሆን ይህም በጦር መሳሪያዎች በጦር ሰራዊቶችና ገንዘብ ብዛት ነው”

እኛ በክርስቶስ እና በዓለም አቀፏ ሁሉን ባቀፈችው ቤተክርስትያን የምናምን አማኞች መፀለያችንን እንቀጥላለን፤ ለሙስሊሞች ማስረዳታችንን ስለ እምነታችን መከራከራችንን እንቀጥላለን፡፡ እንዲሁም ሙስሊሞች እርዳታ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ሁሉ የሰብዓዊ እርህራሄያችንን በመግለጥ ከጎናቸው እንቆማለን፣ ነገር ግን አንዳንድ ጥያቄዎችን ለመጠየቅና አንዳንድ ጉዳዮችንም ለማንሳት መብቶች አሉን፡፡


የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

ከላይ የቀረበው ትኩስ ዜናና የጋዜጠኛው የPiero Gheddo የመጠየቅ መብት አለን ማሳሰቢያ ያነጣጠረው በዓለም ዙሪያ ስለሚደርሱት መጠነ ሰፊና ማቋረጫ የሌላቸው ኢስላማዊ ጥቃቶች ላይ ነው፡፡ በሁሉም ቦታ ጥቃቶቹ ያነጣጠሩት በሲቪሎችና በክርስትያኖች ላይ ነው፡፡ ክርስትያኖች ሰላማዊ ኑሮን ከመኖር በላይ ሙስሊሞችን ሲያጠቁ የትም አገርና ቦታ ላይ አይታይም፡፡ ታዲያ ስለምን ይጠቃሉ? 

የተዘረዘሩትን ዓይነት ግድያዎች፣ ዘረፋዎች፣ ደፈራዎች፣ ጭካኔያዊ ተግባሮች ማከናወን ለምን አስፈለገ? በእርግጥ ይህ ከአንድ ሃይማኖትና ከተከታዮቹ ይጠበቃል ወይ? እነዚህን ጥያቄዎች ሙስሊሞች እንዲያስቡባቸው እናቀርብና፣ የክርስትያኖች እምነት መጽሐፍ፣ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያቀርበው እምነት ላይ ትኩረታችንን እንድናደርግ እንወዳለን፡፡

የክርስትያኖች አምላክ እግዚአብሔር የሰዎችን ልጆች ሁሉ የሚወድና፣ የሰዎች ልጆች በምድር ላይ በሰላምና በደስታ ያለምንም ልዩነት እንዲኖሩ፣ በሚቀጥለውም ዓለም ከእርሱ ጋር በደስታ ዘላለምን እንዲያሳልፉ ጥሪን ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር ሰዎች ሰዎችን እንዲያጠቁ፣ ሰዎች በሰዎች ላይ ክፉ ነገርን እንዲሰሩ አይፈልግም፡፡ 

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያስተማረው የሚከተሉትን ነገሮች ነው፡ “ጠላቶቻችንን እንድንወድ፣ ለእነርሱም እንድንፀልይላቸው፣ የበደሉንን ይቅር እንድንል፣ ከሰዎች ሁሉ ጋር በሰላም እንድንኖር ነው”፣ ከዚህም በላይ ሰዎች ለሰዎች ማድረግ ያለባቸው ብዙ የስነ ምግባር እውነታዎችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን የሚከተለው ጥቅስ ከማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 7.12 ላይ ለሰዎች ሁሉ ስነ ምግባር ጠቃሚ ጥቅስ ነው፡ “እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና።”

ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠይቀውንና ያዘዘውን ዓይነት ሕይወት ሰዎች ለመኖር አይቸሉም፡፡ ምክንያቱም በተፈጥሯቸው ኃጢአተኞች ስለሆኑ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያዘውን ከእግዚአብሔር ጋር የታረቀ፣ ሰላምና ደስታ እንዲሁም እርካታ ያለው በተስፋ የተሞላ ሕይወት ለመኖር እውነተኛ የሆነ የልብ ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ ይህንን የሚሰጠው ደግሞ ሃይማኖት አይደለም፡፡ ሰዎች ይህንን እውነተኛ አዲስ ልብ እንዲቀበሉ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ኢየሱስ ለሰው ልጆች ካለው ፍቅር የተነሳ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ዋጋ ከፍሏል፡፡ ይህንን አስደናቂ አዲስ ልብ ለማግኘት ሰዎች ማድረግ የሚገባቸው ኃጢአተኛ ልባቸውን ለእርሱ በማቅረብ ንስሐ ገብተው ይቅር እንዲላቸውና መጠየቅ ብቻ ነው፡፡

እግዚአብሔር ቸር ስለሆነ አዲስ ልብን ለሰዎች በክርስቶስ ሞት አማካኝነት ለመስጠት በውስጣቸውም አዱስን ሕይወት ለመፍጠር ዝግጁ ነው፡፡  

ይህንን አዲስ ሕይወት ያገኙ ሰዎች የሚኖራቸው አመለካከት በጣም የተለየ ይሆናል ሰዎችን የሚወዱ ለሰዎች መልካምን የሚያደርጉ ይሆናሉ በውጤቱም ደስተኞችና ሰላም ያላቸው በመሆን በምድር ላይ የሚኖራቸውን አጭር ጊዜ በሰላም ማሳለፍ ይችላሉ፡፡


Reference (የመረጃ ምንጭ): http://www.asianews.it/index.php?l=en&art=29339&sendtofriend=12478

 

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ