ሙስሊም ብሆን ኖሮ

Dallas M. Roark, PhD

ቅንብር በአዘጋጁ

ሙስሊም ብሆን ኖሮ በቁርዓን 5.51 ላይ በተጻፈው ጥቅስ እደነቅ ነበር ‹እላንተ ያመናችሁ ሆይ ይሁዶችንና ክርስትያኖችን ረዳቶች (ጓደኞች፣ ጠባቂዎች አጋዦች) አድርጋችሁ አትያዙ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው ከናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከነርሱ ነው አላህ አመጠኞችን ሕዝቦች አያቀናም›፡፡ ይህ አረፍተ ነገር ትክክል አለመሆኑን የሚያረጋግጡ ምሳሌዎች አሉ፡፡ በአፍጋኒስታን ውስጥ የነበረውን የዲክታተሮች አገዛዝ ለማክተም፣ በኢራቅ ውስጥ ከነበረው አምባገነን አገዛዝ ሕዝቡን ነፃ ለማውጣት፣ እና የኩርድ ሙስሊሞች ባገኙት ነፃነት እጅግ በጣም ደስ እንዲላቸው ለማድረግ የረዱት ሙስሊም ያልሆኑ አገሮች ናቸው፡፡ ባለፈው ምዕተ ዓመት መጨረሻ አካባቢ ሙስሊም ያልሆኑ አገሮች ሙስሊም ካልሆኑ አገሮች ጋር ተዋግተው ሙስሊሞችን ነፃ አውጥተዋል፡፡ በዚያን ጊዜ ከዚህ በላይ በሱራ ከተጠቀሰው ጥቅስ በተፃራሪ መንገድ የአይሁድ ዶክተሮች የኮሶቮ ሙስሊሞችን አክመዋል፡፡ እኔ ሙስሊም ብሆን ኖሮ ክርስትያኖችንና አይሁዶችን በመጥላት ስለሚሰብከው ኢማም ሁለት ጊዜ አስብ ነበር፡፡ አንድም ጊዜ ያላዩአቸውን እና ያላገኙአቸውን አይሁዶችንና ክርስትያኖችን በመጥላት ብዙ ኢማሞች ይሰብካሉና፡፡

ይህ ሙስሊሞች የሚያሳዩት እና የሚሰብኩት ሁኔታ አንድ ሰው እጅግ በጣም ከፍ ያለ ትምክህት ነው በማለት ሊገልጠው የሚችለው ነገር ነው፡፡ ወደ ምዕራብ የሚመጡ ብዙ ሙስሊሞች በሚያጋጥማቸው ወዳጃዊ አቀባበል ይደነቃሉ፡፡ የመሐመድን ጠላቶች የእናንተ ጠላቶች አድርጋችሁ ለምን ትቆጥራላችሁ? በሚገርም መልኩ ብዙ ሙስሊሞች ሂንዱዎችንም ወዳጃዊዎችና ሞቅ ያለ አቀባበል ያላቸው ሆነው ያገኙዋቸዋል፡፡ በሂንዱዎች ፍቅርና ደግነትም ይገረማሉ፡፡ እኔ ሙስሊም ብሆን ኖሮ በእንደዚህ ዓይነት ነገር እገረምና ይህ - ለምን ሆነ? ብዬ እጠይቅ ነበር፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- ቁርዓንን አንብቤ ምን እንደሚል ለመረዳት እፈልግ ነበር፡፡ ብዙ ሙስሊሞች በአረብኛ ይሸመድዱታል ነገር ግን ትርጉሙ ምን እንደሚል አይረዱትም፡፡ አንድ ሰው ካልተረዳው የአረብኛ ጥቅሙ ምንድነው? ብዙ ሙስሊሞች ቁርዓን ምን እንደሚል በፍፁም አያውቁም፡፡ ስለዚህም እነሱ እራሳቸው ሊጠይቁት የሚችሉትን ብዙ ነገሮች እንደሚል ሲያዩ ይደነግጣሉ፡፡ እኔ ሙስሊም ብሆን ኖሮ ቁርዓን ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንደሚል ለማወቅ እፈልግ ነበር፡፡

ለምንድነው አንድ ሰው በአረብኛ መፀለይ ያለበት? እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ከሆነ ከአረብኛ ሌላ ሌሎች ቋንቋዎችን አያውቅም ማለት ነውን?

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- ሙስሊም ያልሆነው ዓለም መሐመድ ከህፃን ሴት ልጅ ጋር ግብረስጋ ግንኙነት አድራጊ ወይም (ፔዶፋይል) ነው በማለት ለምን እንደሚያስብ ለማወቅ እፈልግ ነበር፡፡

ሳሂህ ቡካሪ እንደተረከው ‹ነቢዩ አይሻን ያገባት የስድስት ዓመት ልጅ ሆና ሲሆን ጋብቻው የተፈፀመው ግን የዘጠኝ ዓመት ልጅ ስትሆን ነው ከዚያም ከእሱ ጋር ለዘጠኝ ዓመታት አብራው ኖራለች (ማለትም እሱ እስኪሞት ድረስ)፡፡ Sahih Bukhari Volume 7, Book 62, Number 64፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- መሐመድ እስከፈለገው ቁጥር ድረስ ሚስት ሲኖረው እኔ በአራት ሚስቶች መወሰኔ ለምን እንደሆነ ለማወቅ እፈልግ ነበር፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የተጻፉት የቁርአን ምዕራፎች የመጀመሪያው ሱራ የሚመለከተው መሐመድን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ተራ ሙስሊሞችን ነው፡፡

ሀ. ‹አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ እነዚያን መህሮቻቸውን የሰጠሃቸውን ሚስቶችህን አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም እነዚያን እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች እነዚያንም ከአንተ ጋር የተሰደዱትን የአጎትህን ሴቶች ልጆች የአክስቶችህንም ሴቶች ልጆች የየሹማህንም ሴቶች ልጆች የየሹሜዎችህንም ሴቶች ልጆች (ማግባትን) ለአንተ ፈቅደንልሃል የአመነችንም ሴት ነፍሷን (ራሷን) ለነቢዩ ብትሰጥ ነቢዩ ሊያገባት የፈለገ እንደ ኾነ ከምእምናን ሌላ ላንተ ብቻ የጠራች ስትኾን (ፈቀድንልህ) በነርሱ (በምእምናን ) ላይ በሚስቶቻቸውና እጆቻቸው በጨበጧቸው (ባሮች ነገር) ግዴታ ያደረግንባቸውን በእርግጥ ዐውቀናል ባንተ ላይ ችግር እንዳይኖር (ያለፉትን ፈቀድንልህ) አላህም መሐሪ አዛኝ ነው፡፡› 33.50፡፡

ለ.‹በየቲሞችም (ማግባት) አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ (ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ) ከሴቶች ለናንተ የተዋበላችሁን ሁለት - ሁለት ሦስት - ሦስትም አራት - አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረትን ያዙ ይህ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው› 4.3፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- ቁርዓን በእውነት ያልተፈፀሙ ልብ ወለድ ተረቶችን ለምሳሌም ያህል በዋሻ ውስጥ ለዘመናት (ለሦስት መቶ ዓመታት) እንደኖሩ፡፡ እና በሌላው ዓለም እንደ ተረት የሚቆጠሩት ሌሎችም ታሪኮች ለምን እንደተጨመሩበት አስብ እና በትክክል የእግዚአብሔርን ቃል ስለመያዙ እጠይቅ ነበር፡፡ ለምሳሌም ያህል፡-

‹ጎበዞቹ ወደ ዋሻው በተጠጉና፡- ጌታችን ሆይ ከአንተ ዘንድ እዝነትን ስጠን ለኛም ከነገራችን ቅንን አዘጋጅልን ባሉ ጊዜ (አስታውስ)› 18.10፡፡ ‹በዋሻቸውም ውስጥ ሦስት መቶ ዓመታትን ቆዩ ዘጠኝንም ጨመሩ› 18.25፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- መሐመድ የተቹትን፣ የተቃወሙትንና ስለ እሱም አሽሙር ያለበትን ግጥም የጻፉትን ሰዎች ለምን ይቅር እንዳላለ እጠይቅ ነበር፡፡ ሙስሊም ብሆን ኖሮ እነሱ ለምን የሞት ቅጣት እንደተቀበሉ እጠይቅ ነበር፡፡ የአሽሙር ዓይነት አነጋገር የሞት ቅጣት ይገባው ነበርን?

መሐመድ አጎቱን አቡ ላሃብን፣ መልእክቱን ስላልተቀበለው ረግሞታል፡፡ እርግማኑም በቁርዓን ውስጥ 111.1-5 ላይ ተጽፎ ይገኛል ‹የአቡ ለሃብ ሁለት እጆች ከሰሩ (ጠፉ እርሱ) ከሰረም፡፡ ከርሱ ገንዘቡና ያም ያፈራው ሁሉ ምንም አልጠቀመውም፡፡ የመንቀልቀል ባለቤት የኾነችን እሳት በእርግጥ ይገባል፡፡ ሚስቱም (ትገባለች) እንጨት ተሸካሚ ስትኾን፣ በአንገትዋ ላይ ከጭረት የኾነ ገመድ ያለባት ስትኾን፡፡›

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- ሰዎች መሐመድን እንደ ነቢይ ባለመቀበላቸው ብቻ፣ ሙስሊሞች ለምን እንደሚገድሏቸው እጠይቅ ነበር 2.191 ‹ባገኛችኋቸው ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው ከአወጧችሁም ስፍራ አውጧቸው መከራም ከመግደል ይበልጥ የበረታች ናት በተከበረው መስጊድም ዘንድ በርሱ ውስጥ እስከሚገድሉዋቸው ድረስ አትጋደሉዋቸው ቢጋደሉዋችሁም ግደሉዋቸው የከሓዲዎች ቅጣት እንደዚህ ነው›፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- ሰዎችን በአላህ እንዲያምኑ ማስገደድ በእውነት እውነተኛ እምነት ስለመሆኑ በመጠራጠር ጥያቄን አቀርብ ነበር፡፡ ሙስሊም ብሆን ኖሮ ሰዎች በአላህ ለማመንም ሆነ ላለማመን ነፃ መሆን እንዳለባቸው አስብ ነበር፡፡ (እመኝ ነበር)፡፡ እኔም ሰዎች አላህን እንዲያመልኩ ሲገደዱ አላህ እንደሚሰደብ አድርጌ ነበር የምቆጥረው፡፡ እሱ አይገደውምን ወይንም አያውቅምን? የግዳጅ አምልኮ እውነተኛ አምልኮ ሊሆን ከቶ አይችልም፡፡ እኔ ሙስሊም ብሆን ኖሮ ስለዚያ እጠይቅ ነበር፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- ኢየሱስ እንደ አንድ ነቢይ በባህርዩ፣ በስነ ምግባሩ፣ በአስተምህሮው ከመሐመድ በጣም በላቀ መልኩ ለምን ጥሩ እንደነበረ በማሰብ እጠይቅ ነበር፡፡ ‹መላእክት ያሉትን (አስታውስ)፡- መርየም ሆይ አላህ ከርሱ በኾነው ቃል ስሙ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በኾነ (ልጅ) ያበስርሻል› 3.45፡፡

‹እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።› ማቴዎስ 5.44-45፡፡

መሐመድ አለ፡

‹ለነሱም ከማንኛውም ኀይልና ከታጀቡ ፈረሶችም የቻላችሁትን ሁሉ በርሱ የአላህን ጠላትና ጠላታችሁን ሌሎችንም ከነርሱ በቀር ያሉትን የማታውቁዋቸውን አላህ የሚያውቃቸውን (መናፍቃን) የምታሸብሩበት ስትኾኑ አዘጋጁላቸው፡፡ ከማንኛውም ነገር በአላህ መንገድ የምትለግሱትም ምንዳው ወደናንተ በሙሉ ይሰጣል እናንተም አትበደሉም፡፡› 8.60፡፡

ቁርዓን የጠቆመው ነገር ቢኖር ኢየሱስ በቀጥታ ወደ ሰማይ እንደተወሰደ ነው፡፡ መሐመድ ግን ሞቶ ተቀብሯል፡፡ ‹እኛ የአላህን መልእክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን በማለታቸውም (ረገምናቸው) አልገደሉትም አልሰቀሉትምም ግን ለነሱ (የተገደለው ሰው በኢሳ) ተመሰለ. እነዚያም በርሱ ነገር የተለያዩት ከርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም በእርግጥም አልገደሉትም፡፡ ይልቁንስ አላህ ወደርሱ አነሳው አላህም አሸናፊ ጥበበኛም ነው› 4.157-158፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- መሐመድ ሽፍትነትን ሲያካሂድ ንፁሃን ሰዎችን ሲገድልና ሲያስገድል በአንዳንድ መገለጦቹ ላይ ደግሞ አላህ ሐሳቡን ቀይሯል ሲል በአረቢያ በነበሩ አረቦች ያለምንም ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ጥያቄ ውስጥ አስገባው ነበር፡፡

‹ከተከበረው ወር (ከረጀብ) በርሱ ውስጥ ከመጋደል ይጠይቁሃል በላቸው በርሱ ውስጥ መጋደል ታላቅ (ኃጢአት) ነው ግን ከአላህ መንገድ (ሰዎችን) መከልከል በርሱም መካድ ከተከበረውም መስጊድ (ማገድ) ባለቤቶቹንም ከርሱ ማውጣት አላህ ዘንድ ይበልጥ ታላቅ (ወንጀል) ነው ፈተናም (ማጋራት) ከመግደል ይበልጥ ከባድ ነው (ከሐዲዎች) ቢችሉ ከሃይማኖታችሁ እስከሚመልሳችሁ ድረስ የሚዋጉዋችሁ ከመኾን አይቦዝኑም ከናንተ ውስጥም ከሃይማኖቱ የሚመለስና እርሱም ከሐዲ ኾኖ የሚሞት ሰው እነዚያ (በጎ) ሥራቸው በቅርቢቱ በመጨረሻይቱም አገር ተበላሸች እነዚያ የእሳት ጓደኞች ናቸው እነርሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው› 2.217፡፡

መሐመድ በመጀመሪያ በቅዱስ ወር ውስጥ ጦርነትን አላደረገም ነበር ደግሞም ጦርነት ካደረጉት ሰዎች ምርኮን አይካፈልም ነበር፡፡ በኋላ ግን ቆይቶ ሐሳቡን በመቀየር በቁርዓን ውስጥ እንዲቀመጥ አደረገ፡፡ ከዚህም በላይ በተጠቀሰው ቁርዓን ጥቅስ ውስጥ እንዲረጋገጥ አደረገ፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- ሴቶች ለምን እንዲሸፈኑ እንደተደረገ ጥያቄን እጠይቅ ነበር፡፡ ሴቶችም ልክ እንደ ወንዶች ስሜት አላቸው፣ ታዲያ ወንዶችስ ሰውነታቸውን ለምን አይሸፍኑም ነበር፡፡ እኔ ሙስሊም ብሆን ኖሮ ሴቶች ይዘውት የሚጓዙትን እስር ቤት በመሸከማቸው፤ ይህም እንዲያውም በሞቃታማው የዓየር ባህርይ ውስጥ ሁሉ መሆኑን የጭከና ስራ እንደሆነ ነው የማስበው፡፡ ይህም የሆነው የሙስሊም ወንዶች ስሜታቸውን ስለማይቆጣጠሩ ብቻ ነው፡፡ እኔም ሙስሊም ብሆኑ ኖሮ በሞቃት የዓየር ንብረት ሁኔታ ውስጥ ሴቶች ምቾት በሚሰጣቸው ልብስ ክብር እንዲሰጣቸው አስብ ነበር፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- ሴቶች ከወንዶች እኩል የሆነ መብት ለምን እንደማይኖራቸው እጠይቅ ነበር፡፡ መሐመድ ሴቶች አዋቂዎች አይደለም ብሎ በመናገሩ የተነሳ ግማሽ ቢሊዮን የሚሆኑ ሴቶች ሙሉ የሰብኣዊ መብታቸውን ተነጥቀዋል፡፡ እኔ ሙስሊም ብሆን ኖሮ በዚህ የእኩልነት ጉድለት የተነሳ በጣም እቸገር ነበር፡፡ በምዕራቡ ዓለም ውስጥ እጅግ በጣም አስደናቂ የሆኑ ብዙ ግኝቶች፣ አዳዲስ ነገሮች በሴቶች ተፈልስፈዋል እንዲሁም ተገኝተዋል፡፡ በእስላማዊ አገሮች ውስጥ ለሴቶች አዕምሮ የዝቅተኛነት ቦታ ስለተሰጠው የጎደለውን ሳስብ አሁንም ጥያቄ ያድርብኛል፡፡

‹ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው፡፡ መልካሞቹም ሴቶች (ለባሎቻቸው) ታዛዦች አላህ ባስጠበቀው ነገር ሩቅን ጠባቂዎች ናቸው፡፡ እነዚያንም ማመጣቸውን የምትፈሩትን ገሥጹዋቸው በመኝታዎችም ተለዩዋቸው (ሳካ ሳታደርሱ) ምቱዋቸውም፡፡ ቢታዘዡዋችሁም (ለመጨቆን) በነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ አላህ የበላይ ታላቅ ነውና› 4.34፡፡

ይህንን አንድ ሰው ከክርስትያን አመለካከት ጋር ሊያነፃፅረው ይችላል ‹አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።› ገላትያ 3.28፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- አንድ ሙስሊም ሰው የሲዊድናዊትን ሴት በመድፈሩ ትክክል እንደሆነ የሚቆጥርበትንና፣ አንድ ሲዊድናዊ ሰው ግን አንዲትን ሴት በሃይማኖት ምክንያት መድፈሩን ትክክል አይደለም ሲለው ሙስሊሙ ግን ትክክል ነው በማለት የሚናገረውን ሳስብ ጥያቄ ያድርብኛል፡፡ የትኛውም የአይሁዳዊም ሆነ የክርስትያን ቅዱስ መጽሐፍና ጽሑፍ ሴትን ስለመድፈር ምንም ድጋፍን አይሰጥም፡፡ (ፍትሃዊ ነው አይልም)፡፡ ሙስሊም ብሆን ኖሮ ይህ ከስነ ምግባርና ከትክክለኛ አስተሳሰብ የመነጨ እንዳልሆነ ነው የማስበው፡፡

በሲዊድን ውስጥ የተዘጋጀ ጥናት እንደሚያሳየው፡ ‹ወንጀልን በመከላከል ካውንስል ‹ብራ› መሠረት ሴቶችን አስገድደው ደፋሪዎች በመሆን ከታወቁት መካከል አራት እጥፍ የሚሆኑት ከሲዊድን ውጭ የተወለዱ ናቸው፡፡ ይህም በሲዊድን ውስጥ ከተወለደው ጋር ሲነፃፀር ነው፡፡ ከአልጀሪያ፣ ከሊቢያ፣ ከሞሮኮ፣ እና ከቱኒዝያ የሆኑት መጤዎች ናቸው የአስገድዶ መድፈር ቡድን ውስጥ በብዛት ያሉበት፡፡ በዚህ የጥናት ዝርዝር መሠረት ብዙዎቹ ወንጀለኞች መጤዎቹ ናቸው፡፡›

ሙስሊም ብሆን ኖሮ:- ሙስሊም ያልሆነን ሰው የወደደችን ሴት ልጅ የመግደል የክብር ግድያ ለምን እንዲኖር እንደተደረገ እጠይቅ ነበር፡፡ ወይም ሙስሊም ካልሆነ ሰው ጋር ግንኙነት አድርጋለች የተባለችን ሴት ልጅ የመግደል ክብር፡፡ ሙስሊም ሴት ልጆች የራሳቸውን ግንኙነት በተመለከተ ለምን ምርጫን ለማድረግ እንደማይችሉ እጠይቅ ነበር፡፡

March 15, 2005 WorldNetDaily.com የተባለ ድረ ገፅ እንደዘገበው ‹በበርሊን ያሉ ፖሊሶች ‹የክብር ግድያ› በሚል እና በተከታታይ በሆነው ወንጀል የተሳተፉ ሦስት ወንድማማቾችን መያዙን ዘግቧል›፡፡ የ23 ዓመት ወጣት የሆነችው ተርኪሽ ሴት፣ ሃቱን ሱሩኩ፣ የተገደለችው በብዙ ጥይት እራሷንና ልቧን በመደብደቧ ነው፡፡ ይህም ግድያ የሚያለክተው ‹የክብር ግድያ› የተባለውን ምልክት ሆኖ ነው፡፡ ሳይኮሎጂስቱ ፓሊስ በቢቢሲ ዜና አማካኝነት የተናገረው በበርሊን ከሚኖሩት 200,000 ቱርኮች መካከል ይህ ስድስተኛው የክብር ግድያ ሲሆን ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ ለ45 ጊዜ ያህል ተመሳሳይ ወንጀል ተፈፅሟል፡፡ ሱሩኩ በአማጮች አማካኝነት ካገባችው የስምንት ዓመት ባሏና አጎቷ የ5 ዓመት ወንድ ልጇን በመያዝ አምልጣ ነበር›፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- በሙስሊም አገሮች ውስጥ የሚደረጉ ‹የክብር ግድያዎችን› ፖሊስ ለምን እንደማይመረምርና እንደማያጣራ ጥያቄ ይሆንብኝ ነበር፡፡ ሙስሊም ብሆን ኖሮ አባቶች በሴቶች ልጆቻቸው ላይ ሙስሊም ያልሆነ ሰውን ካገቡ እስከመግደል ድረስ የሚያደርስ ሙሉ የቁጥጥር ስልጣን ለምን እንዳላቸው ጥያቄ ያድርብኝ ነበር፡፡

‹የሳዑዲ አረቢያዋ ልዕልት ሚሻ-አል የክብር ግድያ ለዚህ አንድ ምሳሌ ነው፣ ግድያውም የእስልምና የፍርድ ቤት ሕግን ስርዓት የተከተለ ሳይሆን በአያቷ ትዕዛዝ ብቻ የተደገረ ነበርና›፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ መሐመድ ብቻ ስለተናገረው በቀን አምስት ጊዜ ለምን መፀለይ እንዳለብኝ ጥያቄን እጠይቅ ነበር፡፡

‹ሶላትንም በቀን ጫፎች ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም መልካም ሥራዎች ኃጢአቶችን ያስወግዳሉና ይህ ለተገሣጮች ግሣጤ ነው፡፡› 11.114፡፡

ነገር ግን የክርስቶስን ቃላትና በማቴዎስ 6.5-7 ላይ ያሉትን ከዚህ ጋር አወዳድሯቸው፡፡ ‹ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።›

ሙስሊም ብሆን ኖሮ;- መሐመድ በመጀመሪያ ሲፀልይ ወደ ኢየሩሳሌም አቅጣጫ እንደነበረና እኔ ወደ ኢየሩሳሌም አቅጣጫ ከመፀለይ ይልቅ ወደ መካ አቅጣጫ ለምን መፀለይ እንዳለብኝ እጠይቅ ነበር፡፡ እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ አይኖርምን?

‹የፊትህን ወደ ሰማይ መገላበጥ በእርግጥ እናያለን ወደምትወዳትም ቂብላ እናዞርሃለን ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ (ወደ ካዕባ) አግጣጫ አዙር የትም ስፍራ ብትኾኑም (ስትሰግዱ) ፊቶቻችሁን ወደርሱ አግጣጫ አዙሩ እነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት መሆኑን ያውቃሉ አላህም ከምትሠሩት ሥራ ዘንጊ አይደለም› 2.144

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- በቁርአን ውስጥ እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ግድያዎችና ወንጀሎች እያሉ እስልምና ለምን የሰላም ሃይማኖት ተብሎ ሊጠቀስ እንደሚችል እጠይቅ ነበር፡፡ ጥቂት ምሳሌዎችን ለመስጠት ያህል፡-

‹እነሱ እንደካዱ ብትክዱና እኩል ብትኾኑ ተመኙ! በአላህም ሃይማኖት እስከሚሰደዱ ድረስ ከነሱ ወዳጆችን አትያዙ (ከእምነት) ቢያፈገፍጉም ያዙዋቸው (ማርኩዋቸው)፡፡ ባገኛችሁበትም ስፍራ ግደሉዋቸው ከነሱም ወዳጅንና ረዳትን አትያዙ› 4.89፡፡ ‹እውከትም እስከማትገኝ ሃይማኖትም ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚሆን ድረስ ተጋደሉዋቸው ቢከለከሉም አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡› 8.39፡፡ ‹የተከበሩትም ወሮች ባለቁ ጊዜ አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸው ያዙዋቸውም ክበቡዋቸውም ለነሱም (መጠባበቅ) በየመንገዱ ተቀመጡ ቢጸጸቱም ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ ግዴታ ምጽዋትንም ቢሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና› 9.5፡፡ ‹እላንተ ያመናችሁ ሆይ እነዚያን በአቅራቢያችሁ ያሉትን ከሐዲዎች ተዋጉ ከናንተም ብርታትን ያግኙ አላህም ከሚጠነቀቁት ጋር መኾኑን ዕወቁ› 9.123፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ያሉ ሴቶች በመታወቂያቸው ላይ የአባታቸው ፎቶ ወይንም የወንድማቸው ወይንም የጠባቂያቸው ፎቶ እንጂ የእነሱ ፎቶ እንዳይኖር ስለመደረጉ እጠይቅ ነበር፡፡ ሙስሊም ሴቶች በራሳቸው መብት እንደሙሉ ሰው ለምን ተቀባይነት የሌላቸው ስለመሆኑ እኔ ሙስሊም ብሆን ኖሮ እጠይቅ ነበር፡፡

ሪያድ ሳውዲ አረቢያ - ‹የሳውዲ ሴቶች ከአሁን በኋላ እንደከዚህ በፊት ፊታቸውን የማያሳይ መታወቂያ ይዘው አይሄዱም፡፡ ከ2006 አጋማሽ ጀምሮ ለእያንዳንዷ የሳውዲ ሴት ፊቷ ያለበት (ፎቶዋ ያለበት) የመታወቂያ ካርድ ይኖራታል፡፡ ይህም ሴቶች አሁን ባሉበትና ስማቸውን ብቻ በያዘ የቤተሰብ ካርድ ጥገኝነት መታወቅ ዘመንን ያከትመዋል፡፡  ‹የወንድ ጠባቂ የሌላት የሳውዲ ሴት ፓስፖርት ያለወንድ ጠባቂ አረጋጋጭነት ብቻውን በቂ ይሆናል› በማለት ተረኪ ሙሐመድ አል-ማላፌክ፣ የጂዳ የሲቪል ስታተስ መምሪያ ሃላፊ አስታወቀ፡፡ RIYADH, 13 March 2005.

‹በፊት የሳውዲ ሴቶች ስማቸው ብቻ ይጻፍ ነበር እንጂ ፎቶ ወይንም ምስላቸው አይኖርም ነበር፣ እነሱም ስማቸው የሚቀመጠው በአባታቸው ወይንም በባላቸው መታወቂያ ውስጥ ነበር፡፡› ‹የማንኛውም አገር ዜጋ የሆኑ ሴቶች በሳዉዲ አረብያ ውስጥ መኪና እንዲነዱ አይፈቀድላቸውም ይህም ሳዉዲ አረቢያን በዓለም ውስጥ በዚህ ሕግ የመጀመሪያዋ አገር አድርጓታል›፡፡ ‹ብቻቸውን የሚሄዱ የሳውዲ አረቢያ ሴቶች፣ ወይንም አንድ ወንድ፣ ባለቤታቸው ወይንም የቅርብ ዘመዳቸው አብሯቸው ከሌለ፣ ሴትኛ አዳሪዎች ወይንም ግብረ ገብ ያጓደሉ በመሆን ለመያዝና ለመታሰር አደጋ ውስጥ ይወድቃሉ›፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ሃይማኖታቸውን በሌላ እምነት ከቀየሩ ለምን እራሳቸው እንደሚቆረጥ እጠይቅ ነበር፡፡

‹የክርስትያን ቤተሰብ ጥብቅና ቡድን የ41 ዓመት አፋጋኒስታናዊ ለሆነው ለአብዱል ራህማን የጥገኝነት ፈቃድ እንዲሰጠው ለፕሬዜዳንት ቡሽ ጥያቄ አቀረቡ እሱ ወደ ክርስትና እምነት ሃይማኖቱን ስለቀየረ በሸሪዓ ሕግ መሠረት የሞት ፍርድ ይጠብቀው ነበርና› March 30, 2006 WorldNetDaily.com (ወደ ክርስትና የተቀየሩ ሙስሊሞች ድረ ገፅ ላይ እንዲህ ዓይነት ብዙ ምሳሌዎችን ይሰጠናል)፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- በዓለም ላይ ላለው ክፉ ነገር ሁሉ የእስልምናው ዓለም ለምን አይሁዶችን እንደሚወነጅል ጥያቄ ይሆንብኝ ነበር፡፡ የ9/11 ሽብርተኞች ሙስሊሞችና ብዙዎቹም ደግሞ ከሳዉዲ አረቢያ መሆናቸውን ለምን ሙስሊሞች እንደማይቀበሉትም ሙስሊም ብሆን ኖሮ እጠይቅ ነበር፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- በሙስሊምና ሙስሊም ባልሆነ ሰው መካከል አለመግባባት ሲፈጠር ሌላው ሙስሊም እውነትን ሳይመረምር ለምን ሙስሊሙን እንደሚደግፍ እጠይቅ ነበር፡፡ በዚህም አመለካከት የተነሳ ፍትህ በሙስሊም ባህል ውስጥ የበላይነት ይኖረዋል የሚል ክፍተኛ ጥርጣሬ ያድርብኝ ነበር፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ፡- ኢየሱስ ክርስትያኖች እንደሚሉት የእግዚአብሔር ልጅ ስለ መሆኑ እና ስለ አለመሆኑ እጠይቅ ነበር ምክንያቱም እሱ ብዙ ተዓምራትን አድርጓል ሙታንን አስነስቷል ለዕውራን ማየትን ሰጥቷል ሽባዎችን ፈውሷል ለምፃሞችን አንፅቷል፡፡ ነገር ግን መሐመድ ከእነዚህ ውስጥ ማናቸውንም ነገሮች አላደረገም፡፡ እኔ ሙስሊም ብሆን ኖሮ በዚህ ሁሉ ነገር በእርግጥ እደነቅና እጠይቅ ነበር .... ‹ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው ከበኋላውም መልእክተኞችን አስከታተልን የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው ነፍሶቻችሁ በማትወደው ነገር መልክተኛ በመጣላችሁ ቁጥር (ከመከተል) ትኮራላችሁን? ከፊሉን አስተባበላችሁ ከፊሉንም ትገድላላችሁ፡፡› 2.87፡፡ ‹አላህ በሚል ጊዜ (አስታውስ) የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ በአንተና በእናትህ ላይ (የዋልሁላችሁን) ጸጋዬን አስታውስ በሕጻንነትና በከፈኒሳነት (የበሰለ ሰው ኾነህ) ሰዎችን የምትናገር ስትኾን በቅዱሱ መንፈስ (በገብርኤል) ባበረታሁህ ጊዜ ጽሕፈትንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ባስተማርኩህ ጊዜ ከጭቃም የወፍ ቅርጽ ብጤ በፈቃዴም ወፍ በምትኾን ጊዜ ዕውርም ኾኖ የተወለደንና ለምጻምንም በፈቃዴ (ከመቃብራቸው) በምታወጣ ጊዜ የእስራኤልንም ልጆች በተአምራት በመጣህባቸውና ከነሱ እነዚያ የካዱት ይህ ግልፅ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም ባሉ ጊዜ (ሊገድሉህ ሲያስቡ) ከአንተ ላይ በከለከልሁ ጊዜ (ያደረግሁልህን ውለታ አስታውስ)› 5.110፡፡ ሙስሊም ብሆን ኖሮ እነዚህን ሁሉ እያነሳሁ በመጠየቅ መልስ ለማግኘት እጥር ነበር፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

አንባቢ ሆይ በዚች ሙስሊም ብሆን ኖሮ በምትለው ጽሑፍ ውስጥ ጠቃሚ የሆነንና ጥያቄ የሚጭርን ነገር እንደተገነዘብክ እንገምታለን፡፡ በእርግጥ ሙስሊም ብሆን ኖሮ እጅግ ብዙ የማነሳቸው ጥያቄዎች ነበሩኝ፡፡ አንተስ ምንም ጥያቄ የለህምን? አሁን ዛሬ ብትሞት ከሃይማኖትህ የምታገኘው ምን እርግጠኝነት አለ፡፡ በፍርድ ቀን ከፍርድ ስለማምለጥ እርግጠኝነትን የማይሰጥ ሃይማኖት ጥያቄ ለምን አልፈጠረብህም? የዘላለም ሕይወት ነገር እኮ ቀላል እና ጊዜያዊ አይደለም፡፡ አስብበት ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስን አግኝና አንብብ፡፡ የዘላለምን ሕይወት የምታገኝበትን እውነት ታገኝበታለህ እግዚአብሔር ይርዳህ፡፡

 

 

የትርጉም ምንጭ: If I were a Muslim ...

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ