ሴቶች ቦታ በንፁህ እስልምና

ክፍል ስድስት - የወንዶች ስልጣን (መብት)

[ክፍል አንድ] [ክፍል ሁለት] [ክፍል ሦስት] [ክፍል አራትና አምስት] [ክፍል ሰባትና ስምንት] [ክፍል ዘጠኝ] [ክፍል አስር]

M. Rafiqul-Haqq and P. Newton

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

 

1. ወንድ ሊመታና ሚስቱን ያለግንኙነት ሊተዋት ይችላል

በባልና በሚስቶች መካከል ያለው ተፈጥሮአዊ ግንኙነት እንደ ፍቅርና ምህረት እንደሆነ ቁርአን ይገልጣል፡ ‹ለእናንተ ከነፍሶቻችሁ (ከጎኖቻችሁ) ሚስቶችን ወደነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ› ቁርአን 30.21፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያለው ምሁር ሰይድ ኮተብ፣ በዚህ ጥቅስ ውስጥ የተገለጠውንና ወንድ ለተቃራኒ ፆታ ያለውን ተፈጥሮአዊ ስሜት የሚያየው በፈጣሪ የተተከለ አድርጎ ነው፡፡ ከላይ በተጠቀሰው ቃል ውስጥ በሚስትና በባል መካከል ያለውን ‹ፍቅር› የሚለውን ቃል የቀደሙ ምሁራን ያዩት የግብረ ስጋ ግንኙነት ድርጊት እንደሆነ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እዝነት የሚለው ቃል ደግሞ የሚያመለክተው ነገር ወንድና ሚስት ስላላቸው ዘር ነው፡፡ See Razi and Qortobi commenting on Q. 30:21፡፡ መታወቅ ያለበት በጣም ጠቃሚው ነገር ይህ ፍቅርና እዝነት ሴት ከሌለች በስተቀር በወንድ ዘንድ የማይገኝ ነው፣ ነገር ግን በሁለቱም መካከል የሚገኝ የጋራ ነገር ነው፡፡ ስለዚህም ቁርአን ወንዶችን የሚያዛቸው እንደሚከተለው ነው፡ ‹እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ኾናችሁ ልትወርሱና ግልጽን መጥፎ ሥራ ካልሠሩ በስተቀር ከሰጣችኋቸው ከፊሉን ልትወስዱ ልታጉላሏቸውም ለናንተ አይፈቀድም በመልካምም ተኗኗሩዋቸው ብትጠሏቸውም (ታገሡ) አንዳችን ነገር ልትጠሉ አላህም በርሱ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና› ቁርአን 4.19፡፡ በቁርአናዊ ቃላት እና ፅንሰ ሐሳብ መዝገበ ቃላት መሠረት ‹ማአሩፍ› የሚለው ቃል ‹የባህል ሕግ የሚል ሲሆን መልካምን መገናኘት እና ክፉን መከልከል ነው› Dictionary of Qur'anic terms and concepts, Mustansir Mir, Garland publishing inc. New York& London, 1987, p. 235. ይህ ቃል በሌላ ቦታ የተተረጎመው በዩሱፍ አሊ የቁርአን የእንግሊዝኛ ትርጉም ጋር እኩል ሆኖ ነው፡፡ See for example Q. 2:231, 232, 233. በሌላ አነጋገር ሴቶች ጥሩ ባህርይን የሚያሳዩ ከሆነ ደግነት ሊደረግላቸው ይገባል፣ የሚደረግላቸውም ነገር በባህላዊው ሕግ መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡ 

ጥሩ ባልን የሚገልጥ ሐዲትም አለ፤ ‹ከእናንተ ጥሩ የሆነው ለሚስቱ ጥሩ የሆነው ነው› Mishkat al-Masabih, English translation, Book 1, section 'duties of husband and wife', Hadith No. 68.  (ያ ሐዲት በቲርሚዚ ብቻ ነው የተጠቀሰው)፡፡ ነገር ግን ይህ የባሎች መልካምነት በአስቸጋሪ ጊዜያት ምን ያህል ነው የሚቀጥለው፣ ማለትም ሚስት እንደሚገባ ፀባይ በሌላት ጊዜስ?

በቁርአን መሠረት ወንድ ሚስቱን የመገሰፅ ሃላፊነት አለበት፣ እንዲሁም ያለግብረስጋ ግንኙነት እርሷን የመተው፣ ፀባዩዋንም በተመለከተ ዓመፀኝነቷን ለማረም እንዲደበድባትም ሃላፊነት አለበት፡፡ ቁርአን እንደሚከተለው ይናገራል፡ ‹ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው፣ አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው፡፡ ..... እነዚያን ማመጣቸውን የምትፈሩትን ገሥጹዋቸው በመኝታዎችም ተለዩዋቸው (ሳካ ሳደርሱ) ምቱዋቸውም፡፡ ቢታዘዟችሁም (ለመጨቆን) በነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ አላህ የበላይ ታላቅ ነውና› ቁርአን 4.34 The Qur'an, 4:34. (Arberry's translation)፡፡ አንዳንድ ተርጓሚዎች ‹ምቷቸው› ከሚለው ቃል ቀጥሎ ‹ቀለል አድርገው› የሚሉ ቃላትን ጨምረዋል፣ The Holy Qur'an, Yusuf Ali's Translation፡፡ ሌሎች ደግሞ እንደ መሐመድ ፒክታል እና ሮድዌል ‹ምቷቸው› የሚለውን ‹ግረፏቸው› በማለት ተርጉመውታል፡፡

ቁርአን 4.34 ለመሐመድ የተገለጠበት ሁኔታ በጥቅሱ ውስጥ የሚኖረውን ትርጉም ለመረዳት አስፈላጊውን ብርሃን ይሰጣል፡፡ ስለሁኔታውም ብዙዎቹ ተንታኞች የሚከተለውን ጠቅሰዋል፡

‹ከላይ ያለው ጥቅስ ወደ መሐመድ (በመገለጥ) የመጣው ባሏ ፊቷን በጥፊ የመታት አንዲት ሴት ለመሐመድ አቤቱታን ካቀረበችበት ሁኔታ ጋር ተያይዞ ነው (ፊቷም የጥፊው ምልክት እንደነበረበት ነበር)፡፡ በመጀመሪያም ነቢዩ ለእርሷ እንዲህ አላት፡ ‹ተበቀይው› ከዚያም የሚከተለውን ጨመረ፡ ‹እስከማስብበት ድረስ ቆይኝ› አላት፡፡ ከዚያም ከዚህ በላይ የተነገረው ጥቅስ ተገለጠለትና ቀጥሎም ነቢዩ እንደሚከተለው ተናገረ፡ ‹እኛ አንድ ነገርን እንፈልጋለን አላህ ግን ሌላ ነገርን ይፈልጋል፣ አላህ የሚፈልገው ግን የበለጠውን ነው› Razi, At-tafsir al-Kabir, on Q. 4:34፡፡ ከዚህ በላይ የተጠቀሰው መምታት፣ በቀላል መምታት ማለት ያ ካልሆነ በስተቀር፣ ቀላል ነው ተብሎ ሊገለጥ አይቻልም፡፡ ይህ መምታት የመጣው ግብረ ስጋ ግንኙነት ካቆመ በኋላ እንደ የመጨረሻ የማረሚያ እርምጃ ተደርጎ ነው፡፡ ከግብረ ስጋ ግንኙነት ማቆም በኋላ የሚሆን ቀላል ምት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰና ምንም ዓላማ የለሽ ነው፡፡ ነገር ግን ከተግሳፅ በኋላ ቀጥሎም ግብረ ስጋ ግንኙነትን ከመከልከል በኋላ የሚሆነው መምታት ጥብቅ (ኃይለኛ) ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ብቻ ነው ማለትም ምቱ ከፍተኛ ከሆነ ብቻ ነው ሎጂካል የሆነ ቀጣይነት የሚኖረው፡፡ ስለዚህም ግብረ ስጋ ግንኙነትን ከመከልከል በኋላ የሚሆነው ይህ መምታት በጣም ከባድ የሆነ መሆን አለበት፡፡ ይህ መምታትም ባሪያን እንደመግረፍ ያለ ዓይነት አይደለም Mishkat al-Masabih, English translation, Book 1, section 'duties of husband and wife', Hadith No.50. ነገር ግን አደጋ የማያደርስ ዓይነት መምታት ነው እንጂ  Mishkat al-Masabih, English translation, Book 1, section 'duties of husband and wife', Hadith No.76፡፡ (ተቀባይነት ያለው ሐዲት)፡፡ ስለዚህም ባል ዓመፀኛዋን ሚስቱን የመምታት መብት አለው ይህም መምታቱ እንደ ሴት ባሪያን መግረፍ ዓይነት ካልሆነና የአካል አደጋ ካላደረሰ በስተቀር ነው፡፡

ሚሽካት አል-ማሳቢህ የተባለውን ተርጓሚው ካዚ ካሃን ጠቅሶ ‹ሴትን መምታት በቀላሉ ነው› በማለት በጻፈው ፋትዋ ላይ የሚከተለውን የግርጌ ማስታዎሻ አስቀምጧል፡ በአራት ሁኔታዎች ውስጥ ተፈቅዷል፡ 1. በባሏ የሚፈለግ እየሆነ ልብስን የማትለብስ ከሆነ፤ 2. ለግብረ ስጋ ግንኙነት ስትጠራ ሕጋዊ የሆነ ማመካኛ ሳይኖራት እምቢተኛ ከሆነች፤ 3. እንድትታጠብ ከቆሻሻ (እራሷን ለማንፃት) ለፀሎት ስትታዘዝ እና ይህንን ለማድረግ እምቢተኛ ስትሆን እና 4. ያለ ባሏ ፈቃድ ወደ ሌላ አገር ስትሄድ ነው› Mishkat al-Masabih, English translation, Book 1, section 'duties of husband and wife', Hadith No.138፡፡  

በሌላ የግርጌ ማስታዎሻ ላይ ደግሞ የሚሽካት አል-ማሳቢህ ተርጓሚ የተናገረው፡ ‹ማንኛዋም ሴት ባሏ ከእርሷ የሚፈልገውን ነገር እምቢ ልትል አትችልም፣ ይህም ሃይማኖታዊ  ማለትም የወር አበባዋ መውረድ ጊዜ ወይንም በፆም ጊዜ ካልሆነ በስተቀር ብቻ ነው፡፡ አንዳንድ የስነ መለኮት አዋቂዎች ይህንን ክልከላ እራሱ ሕገወጥ አድርገው ይቆጥሩታል ምክንያቱም ባል ከሚስቱ ደስታን በሌላ መንገድ ሊያገኝ ይችላልና ይህም በማቀፍ በመሳም ወ.ዘ.ተ ነው፡፡ በአልጋው ላይ እያለ የሚስት ስራ በሚፈልገው መንገድ ሁሉ ለእሱ ደስታን መስጠት ነውና› Mishkat al-Masabih, English translation, Book 1, section 'duties of husband and wife', Hadith No.140፡፡  

ይህ መምታት በፍፁም የማይሻር የባል መብት ነው፡፡ ኢብን ካቲር በትንተናው ላይ የጠቀሰው በሐዲት ላይ በዛል አሻዝ ኢብን አል-ቃያስ ስልጣን ኦማርን ይጎበኝ በነበረበት ጊዜ የሆነውን ነው፡፡ ‹ኦማር ሚስቱን ወስዶ ደበደባት፣ ከዚያም ለአሻዝ እንዲህ አለው፡ ‹ሦስት ነገሮችን ለእኔ አስታውስልኝ እነዚህም ከነቢዩ ሲናገር ያስታወስኳቸው ናቸው ‹ወንድ ሚስቱን ለምን እንደሚመታት ሊጠየቅ አይገባውም› Ibn Kathir, commenting on Q. 4:34, this Hadith is also reported by Abu Dawood and al-Nisa'i and Ibn Magah.፡፡

ሚስቱን በመምታት በኩል አንድ ወንድ ያለው መብት ለጥንታዊው ጊዜ ብቻ አይደለም የሆነው፡፡ የሳምንታዊ ጋርድያን ጋዜጣ የዘገበው፡ ‹የአረብ ሕግ ባለሙያዎች ማህበር ያቀረበውን የቁርአን ትርጉምን ተከትሎ በ1987 የግብፅ ፍርድ ቤት የወሰነው ባል ሚስቱን የማስተማር ተግባር እንዳለበትና እንዲሁም ደግሞ እንደፈለገው እርሷን የመቅጣት መብትም እንዳለው ነው› Guardian Weekly, 23/12/1990, Violence against Women Highlighted, p. 13.

ዘመናዊው ምሁር እና ተንታኙ ሰይድ ኮተብ፣ ከዚህ በላይ ባለው (በሚገኘው) ጥቅስ ያለውን የባልን ሚስቱን የመምታትን መብት ስጦታ በተመለከተ ጉዳዩን ለማሳመን እንደሚከተለው ጥረትን አድርጓል፡ ‹የሕይወት እውነታ እንዲሁም የአንዳንድ ሳይኮሎጂካል ማፈንገጦች ሁኔታ የሚያመለክተው ቢኖር ይህ አቀራረብ (ማለትም ሚስትን መምታት) በተለይም የአንድን ዓይነት ማፈንገጥ በተመለከተ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነው አቀራረብ ነው፣ ይህም የሰውን ባህርይ በማደስ በኩል እና በተመሳሳይ ሰዓት እሷን በማርካት በኩል ነው!

ይህ ዓይነቱ ሳይኮሊጂካዊ ማፈንገጥ ባይኖርም እንኳን፣ አንዳንድ ሴቶች ጠባቂያቸውና ባላቸው አድርገው ሊወስዱት የሚወዱት ወንድ፣ በአካል ካልቀጣቸው በስተቀር ምናልባትም የወንድን ስልጣን አያውቁም ይሆናል፡፡ ይህ የሁሉም ሴቶች ተፈጥሮ ባይሆንም እንዲህ ዓይነቱ ነገር ይኖራል፡፡ ይህ የመጨረሻ እርምጃ የሚፈለገው ይህ ዓይነቱ ነገር ይስተካከል ዘንድ ነው እናም ጥብቅ በሆነው ድርጅት ማለት (በጋብቻ) ውስጥ የሚኖረው ኑሮ በሰላምና በፀጥታ ነው› Sayid Qotb, Fi Zilal al-Qur'an, commenting on the Qur'an 4:34.

ከዚህ በላይ ያለውን ጥቅስ አስመልክቶ አንዳንድ ምሁራን እንደሚከተለው ተናግረዋል፡- ‹የሴቶች ዓመፀኝነት (ነሹዝ) የጤንነት ጉዳይ (ሁኔታ) ነው፡፡ እሱም ሁለት ዓይነት ነው፡ አንደኛው ሴት እራሷን የሰጠች የትዳር ጓደኛ አድርጋ በማቅረቧ ደስተኛ ስትሆን እና በመደብደቧና ቶርች በመደረጓ ደስታን ስታገኝ ያለው ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ነው ማሶሺዝም በመባል የሚታወቀው፡፡ ሁለተኛው ዓይነት ደግሞ ሴት ሌላውን ጓደኛ መጉዳትና የበላይነትን ማሳየት ስትወድ የሚሆነው ነው፡፡ ይህም ሳዲዝም በመባል የሚታወቀው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቷ ሴት እሾኋን ከማስወገድና ተፅዕኖ የምታሳድርበትን የጦር መሳሪያዋን ከማስወገድ ውጭ (ከመስበር ውጭ) ምንም መፍትሄ አይኖራትም፡፡ ይህ የሴት የጦር መሳሪያ ሴትነቷ ነው፡፡ ነገር ግን ሌላዋ ሴት ዝቅ በማለቷ እና በመመታት ደስ የሚላት ስትሆን መድሃኒቷ መምታት ነው፡፡ ስለዚህም የቁርአኑ ትዕዛዝ፡ ‹በአልጋዎቻቸው ላይ ዝጓቸው፣ እና ምቷቸው› የሚለው ትዕዛዝ የዓመፀኛ ሴቶችን (ባህርይ) በመረዳት በኩል ካለው የጊዜው የሳይኮሎጂካል ግኝት ጋር አብሮ የሚሄድ ነው፡፡ ይህም የቁርአን አንዱ ሳይንሳዊ ተዓምር ነው ምክንያቱም ስለ ዓመፀኛ ሴቶች በሳይኮሎጂ ሳይንስ የተነገረውን ጥራዝ ጥቅልል አድርጎ ያቀርበዋልና፡፡› The Australian Minaret, published by the Australian Federation of the Islamic Councils, November 1980, p.10.

ከዚህ በላይ ያሉት ሁለቱ ጥቅሶች የሚናገሩት የተጣመመችን ማሶሺት ሴት እንድትደበደብ የሚናገረው የቁርአን ጥቅስ ከዚህ የተዛባ ጤንነቷ እርሷን ይፈውሳታል በማለት ነው፡፡ ነገር ግን እርሷ የምትፈልገውን ደስታ መስጠት ጠማማነቷትን ይጨምረዋል ማለት ነውን? ለአንድ ሰካራም ሰው ተጨማሪ መጠጥ መስጠት ከስካሩ ያድነዋልን? ሳዲስት የሆነችውን ሴት ለምን መምታት ያስፈልጋል? እርሷ የራሷ መንገድን እንድትይዝ ለምን አንፈቅድላትም እንደ ማሶሺስቲኳ? ለምንድነው እርሷ ሌሎችን እንድትመታና እንድታሰቃይ የማይፈቅድላት? ምንም እንኳን ይህ ድርጊት ለጥቂቶች ጠማማዎች ሴቶች ጠቀሜታ የተባለ ቢሆንም ይህ በማንኛውም ምክንያት ለሚያምፁ ሚስቶች ሁሉ ይሆናል ማለት እንችላለንን? (ደግሞስ ፍትሃዊ ነውን?)፡፡

ሚስቶችን መምታት ፍትሃዊ (ትክክል) ቢሆንም ባይሆንም ይህ የወንድ መብት ነው ደግሞም የእሱ ብቻ ነው፡፡ የሚስቱን ዓመፀኝነት የሚፈራ ሰው በመጀመሪያ እርሷን መገሰፅ አለበት፡፡ ያ የማይሰራ ከሆነ ደግሞ ባል እርሷን ከግብረ ስጋ ግንኙነት ማግለልና ማራቅ አለበት፡፡ ያ የማይሰራ ከሆነ ደግሞ እርሷን የመምታት መብት አለው፡፡

ሰይድ ካተብ የገለፀው እርሷን መገሰፅ የማይሰራ ከሆነ የሚስትን ከግብረ ስጋ ግንኙነት መተው ስላለው ሃይል ሲናገር፡ ‹አሁን ሁለተኛው ደረጃ ይመጣል፣ ... ወንድ ከፍ ያለ የሳይኮሎጂያው እርምጃ መውሰድ አለበት ይህም ከእርሷ ውበትና መስህብ ተቃራኒ የሆነ ነው፣ ይህም እርሷን በአልጋዋ ላይ በመተውና በመዝጋት ነው፣ ምክንያቱም አልጋ የፈተናና የመቃጠል ቦታ ነውና ይህም ዓመፀኛዋ ሴት በኃይሏ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የምትደርስበት ነውና፡፡ አንድ ሰው ከእርሷ ፈተና የእራሱን ሁኔታ ዝንባሌ ከተቆጣጠረ ከዚያም እርሱ እርሷ ካላት በጣም የተሳለ እና ውድ ዋጋ ካለው መዋጊያዋ (የጦር መሳሪያዋ) ያስፈታታል፡፡› Sayid Qotb, Fi Zilal al-Qur'an, commenting on the Qur'an 4:34.

ሌላው ምሁር ደግሞ ከዚህ በላይ የጠተቀሰውን በመድገም እንደሚከተለው ተናገረ፡ ‹ይህ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማዕቀብ ለሴት ዓመፀኝነት መድሃኒት ነው፣ ይህም እርሷ በጣም ከምታከብረው ከሴትነቷ ነገር ... ስለዚህም በሴት ላይ እጅግ በጣም ከፍተኛ ድል (እሷን በማሸነፍ) ማድረግን ያመጣል› Al-Bahi al-Khuli, Al-Islam wa-l-Mar'ah al-Mu'aserah, Dar al-Qalam, Kuwait, 1984, p. 105.

ወንድ ስለዚህም ሚስቱን ያለ ግብረ ስጋ ግንኙነት የመተውና የመምታትም መብት አለው፣ ይህም በእሷ ውስጥ የዓመፀኝነትን መኖር ከፈራ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሴት፣ በባሏ ውስጥ ዓመፀኝነት አለ በማለት ብትፈራ ወደ እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ልትገባ አትችልም፣ በሚከተለው ጥቅስ ውስጥ ግልጥ እንደሆነው፡ ‹ሴትም ከባልዋ ጥላቻን ወይም ፊቱን ማዞርን ብታውቅ በመካከላቸው መስማማትን ቢስማሙ በሁለቱ ላይ ኃጢአት የለም፡፡ መታረቅም መልካም ነው፡፡ ...› ቁርአን 4.128፡፡ The Qur'an 4:128. (Arberry's translation)፡፡ ከቁርአን 4.128 እና 4.34 ውስጥ ግልጥ እንደሆነው፣ ሴት ከባሏ በኩል ዓመፀኝነትን ስትፈራ ቁርአን ዲፕሎማሲያዊነትን ያዛል፡፡ ነገር ግን ወንድ ሚስቱ ዓመፀኝነትን አድርጋለች ብሎ ቢፈራ ቁርአን ኃይልን መጠቀምንና በግብረስጋ ግንኙነት መተውን ያዛል፡፡ 

በሚቀጥለው ሐዲት ውስጥ ቡካሪ ሚስት ከባሏ በኩል ጭከና እና መተው እንዳጋጠማት ስትፈራ የሚኖራትን ምርጫ ምሳሌ ሰጥቷል፡ ‹አይሻ እንዲህ አለች (‹ሚስት ከባሏ በኩል ጭከናንና መተውን ከፈራች ...› የሚለውን ጥቅስ በተመለከተ) ባሏ ከዚህ በኋላ ሊያቆያት በማይፈልግበት ጊዜ፣ ሊፈታት እና አንድ ሌላ ሴትን ሊያገባ ሲፈልግ ይህ ሴትን ያሰጋታል፣ ስለዚህም ለእሱ እንዲህ አለችው፡ ‹አትፍታኝ አኑረኝ፣ ከዚያም ሌላ ሴትን አግባ በእኔም ላይ ምንም ወጪንም አታውጣ ከእኔም ጋር አትተኛ፡፡› ይህ በአላህ ቃል ተጠቅሷል፡ ‹እነሱ በመካከላቸው የወዳጅነትን ስምምነት ካደረጉ ምንም ነቀፋ የለባቸውም፣ እንደዚህ ዓይነቱ ስምምነት የተሻለ ነው› Sahih Bukhari, Arabic-English translation, vol. 7, Hadith No. 134. ስለዚህም በቡካሪ ጤናማ ሐዲት መሰረት፣ ድጋፍን ያገኘው የወዳጅነት ስምምነት ከባሏ በኩል መተውንና ጭከናን ለምትፈራው ሴት ባሏ ሌላ ሴትን እንዲያገባ ለቧላ ፈቃድ እራሷን ማስገዛቷና የገንዘብንና የግብረ ስጋ ግንኙነት መብቷን መልቀቋ ነው፡፡

ዓመፀኛዋን ሚስት መምታት ከመፍታት በፊት የሚመጣው የመጨረሻው እርምጃ ነው፡፡ በመጀመሪያ መገሰፅ አለባት፡፡ ይህ ካልሰራ ባሏ ያለግብረ ስጋ ግንኙነት ለብቻዋ ሊተዋት መብት አለው፡፡ ከሴት ጋር በደግነት አብሮ መኖር በማለት ቁርአን የሚናገረው ነገር ዓመፀኛዋን ምቱ እና ከግብረ ስጋ ግንኙነትም አርቁ ከሚለው ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም፣ ከደግነቱ ጋር አብሮ ይህ መምታት ተጨምሯል፡፡ ነቢዩ እራሱ ከሙስሊሞች ሁሉ ለሚስቶቹ በጣም ደግ የነበረው ሁሉንም ለአንድ ወር ያህል ከግብረ ስጋ ግንኙነት ትቷቸው ነበር Sahih Bukhari, Arabic-English translation, vol. 7, Hadith No. 130  እና 131፡፡ ኢማም ጋዛሊ እንደሚከተለው አስቀምጦታል፡ ‹በሴቶች ውስጥ ክፋትና ድካም አለባቸው፡፡ ለክፋታቸው ዲፕሎማሲና ክፋት፤ ጠንካራ መሆን፤ መድሃኒቶች ናቸው፣ ለድካማቸው ግን ደግነትና ጨዋነት መፍትሄዎች ናቸው፡፡› Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p. 52.

ባሎች ሚስቶችን ከሚይዙበት አያያዝ በተቃራኒ በእስልምና ልጆች እናቶቻቸውን ማየት ያለባቸው በከፍተኛ አክብሮት እንደሆነ ከሚከተሉት ሁለት ሐዲቶች እንረዳለን፡ አቡ ሁራይራ እንደዘገበው አንድ ሰው ወደ አላህ መልእክተኛ (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) መጣና ጠየቀው፡ ‹ኦ የአላህ መልእክተኛ በፍቅርና በጥበቃ በተመለከተ በእኔ ላይ ከፍተኛውን መብት ያለው ማን ነው?› እርሱም መለሰ፡ ‹እናትህ ናት›፡፡ ከዚያስ ማን ነው? እርሱም መለሰ፡ ‹እናትህ ናት›፡፡ ቀጥሎስ ማን ነው? እርሱም መለሰ፡ ‹እናትህ ናት› ከዚያስ ማን ነው? እርሱም መለሰ፡ ‹አባትህ ነው›፡፡

እንዲሁም፡ ‹ገነት ከእናቶች እግር ስር ናት›፡፡ ዶክተር ሻቢብ ሃሳን በሁለተኛው ላይ የሚከተለውን ትንተና ሰጠ፡ ‹ከዚህ በላይ ያለው ሐዲት ‹ዳኢፍ› ከሚለው ቃል ጋር ነው፣ ነገር ግን የእርሱ ትርጉም ያለው በኢብን ማጃህ እና አል-ናሳይ ነው፣ አንድ ሰው ወደ ነቢዩ (አላህ ይባርከውና ሰላምን ይስጠው) መጣና እንዲህ አለው፡ ‹ኦ የአላህም መልክተኛ! ወደ ጦርነት ዘመቻ መሄድ አቅጃለሁ ነገር ግን ያንተን ምክር ልጠይቅ መጥቻለሁ› እርሱም አለው፡ ‹እናትህ በሕይወት አለችን?› እርሱም አለ፣ ‹አዎን› እርሱም አለ፡ ‹ከዚያም ከእርሷ ጋር ቆይ አትክልት ቦታው ከእግሯ በታች ነውና› AN INTRODUCTION TO THE SCIENCE OF HADITH, Al-Quran Society London, Author: Dr. Suhaib Hasan

አንዳንድ እናቶች በሲዖል ውስጥ ያለው በጣም ዝቅተኛ ቦታ የሚገባቸው መሆኑ እውነት ነው፡፡ ስለዚህም ገነት በእያንዳንዱ እናት እግር ስር አለመሆኑ ሎጂካል እውነት ነው፡፡ ‹ገነት ከእግሯ ስር ነው› የሚለው ቃል የተነገረው ስለ አንዲት ሴት ነው ምናልባትም ቀጥተኝነቷ በመሐመድ ስለምትታወቅ ሴት ነው፡፡ ከዚህም በላይ መሐመድ የሚዋጉትን ወታደሮቹን ሁሉ በቤት እናቶቻቸው በሕይወት ካሉት ጋር እንዲቆዩ ያለማዘዙ እውነታ ግልፅ የሚያደርገው ነገር ይህ አጠቃላይ እውነታ ሳይሆን ስለአንዲት ሴት ነው፣ እርሷም በጣም አሮጊትና የልጇን (ብቻ?) እንክብካቤን የሚያስፈልጋት መሆኑን ነው፡፡ 

ያ ሐዲት ሳሂህ ቢሆንም እንኳን መታወቅ ያለበት ነገር ሁለቱም ሐዲቶች ትኩረት ያደረጉት በተለይም በእናቶች ላይ ነው እንጂ በአጠቃላይ ሴቶች ላይ አይደለም፡፡ ሁለቱም ሐዲቶች ልጅ የሌሏቸውን ሚስቶች አላስገቡም እንዲሁም በእርግጥ ደግሞ ብቸኛ ሴቶችን ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ መታየት ያለበት ነገር ሁለቱም ሐዲቶች በልጆችና በእናቶች መካከል ያለውን የተለየ ግንኙነት ይናገራሉ እንጂ በባልና ሚስት መካከል ያለውን አይደለም፡፡ ስለዚህም ወንድ ልጅ ለእናቱ በጣም ከፍተኛ የሆነውን ክብር እየሰጠ እያለ፣ የዚች ሴት ባል እርሷ ዓመፀኛ ትሆናለች ብሎ የሚፈራት ከሆነ እርሷን ለመተው፣ ለመምታት  እኩል መብት አለው፡፡

የወንዶችን መብቶች ሚዛናዊ ለማድረግ ይረዳሉ ተብለው የሚቆጠሩትና የሚጠቀሱት  ሌሎች አንዳንድ ሐዲቶች የሚከተሉት ናቸው፡ ከእናንተ በጣም ጥሩ የሆነው ለሚስቱ በጣም ጥሩ የሆነው ነው E.g. No. 410 in "500 Ahadith"፡፡ ከእናንተ በጣም ጥሩ የሆኑት (ለአሂሎቻቸው) ጥሩ የሆኑት ናቸው ማለትም ለሚስቶቻቸው እና ለልጆቻቸው፡፡ እኔ ደግሞ ለቤተሰቤ ከእናንተ በጣም የተሻልሁ ነኝ፡፡ as quoted in "Family Values in Islam"

አነዚህ ሐዲቶች መታየት ያለባቸው በታሪክ እውነታዎች ዓይን ነው፡፡ ‹መሐመድ ሚስቶቹን ለሙሉ ወር ነው የተዋቸው› Sahih Bukhari, English-Arabic, Book VII, Kitab an-Nikah, Hadith No. 130፡፡ በአንድ ሁኔታ ውስጥ እርሱ ሁለቱንም አይሻንም ሐፍሳንም ጠራቸው፡ ‹የዮሴፍ ጓደኞች› በማለት ይህም እጅግ በጣም አዋራጅ የሆነ አባባል ነበር፡፡ Ihya' 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, pp. 50-51፡፡ እንዲሁም ደግሞ ሳውዳን ለመፍታት አቅዶ ነበር ይህም አሮጊት ከመሆኗ በቀር ሌላ ምንም ምክንያት አልነበረውም፡፡ (ኢን ካቲር በቁርአን 4.128 ላይ ሲተነትን)፡፡ የመሐመድ የበላይነት እንደ ባል እርሱን አላገደውም እንደ ማንኛውም ሙስሊም ወንድ መብቱን ከመጠቀም አላገደውም፡፡

2. ወንዶች እስከ አራት ነፃ ሴቶች ለማግባትና ያልተወሰነ ቁጥር ካላቸው ባሪያ ሴቶች ጋር ግን ግብረ ስጋ ግንኙነትን ማድረግ ይችላሉ፡፡ ወንዶች ከአንድ ሴት በላይ እንዲያገቡ እንደሚከተለው ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል፡

‹ወላጅ አልባ የሆኑትን (ልጃገረዶች) መንከባከብ የማትችሉ እንደሆነ ከፈራችሁ ከዚያም ጥሩ የሚመስሏችሁን ሌሎችን ሴቶች ልታገቡ ትችላላችሁ፣ ሁለት፣ ሦስት ወይንም አራት የሆኑትን፡፡ ነገር ግን በእነሱ መካከል እኩልነትን አናደርግም ብላችሁ የምትፈሩ ከሆነ አንዲትን ሴት ብቻ አግቡ ወይንም የሚኖራችሁን ማንኛውንም ባሪያ ሴት፡፡ ይህም ፍትሐዊ እንዳትሆኑ የሚያደርጋችሁን ነገር ከእናንተ ላይ ያስወግደዋል› The Qur'an 4:372፡፡

አንዳንዶች ግን ቢሆንም ተከራክረዋል እኩል ማድረግ የማይቻል ስለሆነ በሚቀጥሉት ጥቅሶች መሠረት ከአንድ በላይ ሚስትን ማግባት አይፈቀድም፡ ‹የምትችሉትን ሞክሩ፣ ሚስቶቻችሁን ሁሉ በእኩልነት ልትንከባከቡ አትችሉም፡፡ እራሳችሁንም በማናቸውም ላይ ተቃዋሚዎች አድርጋችሁ አታቅርቡ› The Qur'an 4:129. (Dawood's translation)፡፡

ነገር ግን ብዙዎቹ ተንታኞች የተስማሙበት፡ በቁርአን 4.3 ላይ ያለው እኩልነት የሚመለከተው ጊዜንና ገንዘብን በማከፋፈል ላይ ሲሆን በቁርአን 4.129 ላይ የተጠቀሰው ደግሞ ወንድ ለሚስቶቹ ባለው ፍቅርና ዝንባሌ ላይ ነው Tuffaha, Ahmad Zaky, Al-Mar'ah wal-Islam, Dar al-Kitab al-Lubnani, Beirut, first edition, 1985, p. 58. See also Razi and al-Jalalayn on the above verses. And Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p. 54. And Ibn al-'Arabi, Ahkam al-Qur'an, vol. 1, p.504፡፡

በተጨማሪም የሚከራከሩት መሐመድ እራሱ በሚስቶቹ ላይ ባለው አቅርቦት በጣም ያዳላ ነበር፣ ምክንያቱም እርሱ አይሻን ከሌሎቹ ሚስቶቹ ይልቅ ይወዳት ነበርና Razi, At-tafsir al-kabir, commenting on Q. 4:12975፡፡ ስለዚህም ባል ገንዘቡንና ጊዜውን በማከፋፈል ላይ ሚዛናዊ እስከሆነ ድረስ እስከ አራት ድረስ ሊያገባ ይችላል፡፡ ሌሎች ደግሞ የሚያምኑት የሚስቶች ቁጥር እስከ ዘጠኝ ሚስቶች እንደተገደበ ነው፣ ምክንያቱም ሁለት፣ ሦስትና አራት ሲደመሩ የሚሰጡት ዘጠኝ ነውና፣ መሐመድም እራሱ በሚሞትበት ሰዓት ዘጠኝ ሚስቶች ነበሩትና ስለዚህም የእሱን መንገድ መከተል ደግሞ የተፈቀደ የኑሮ መንገድ ነው Razi, At-tafsir al-kabir, commenting on Q. 4:3፡፡

ሌሎችም የሚያምኑት ከዚህ በላይ ያለው ጥቅስ በሚስቶች ላይ የቁጥር ገደብ የሌለ መሆኑን የሚያስረዳ እንደሆነ ነው፡፡ ምክንያቱም ቁጥሩ ሁለት ወይንም ሦስት ወይንም አራት ሳይሆን የሚለው ቃል በቃል ሁለት፣ ሦስትና አራት ነውና ይህም ትርጉሙ ሁለት እና ሦስት እና አራት ወ.ዘ.ተ ነውና Razi, At-tafsir al-kabir commenting on Q. 4:3፡፡ አብዛኛዎቹ የሚያምኑት አንድ ሰው ሊያገባ የሚችለው የሚስቶች ቁጥር በአራት መወሰን እንዳለበት ነው፡፡ ምክንያቱም በሐዲቶች ላይ አስር ሚስቶች ስላለው ሰው በተዘገበው ምክንያት የተነሳ ነው፡፡ እርሱም ሙስሊም ሲሆን መሐመድ ለእርሱ እንዲህ አለው፡ ‹አራቱን አስቀርና ሌሎቹን ፍታ› Razi, At-tafsir al-kabir commenting on Q. 4:3፡፡

ከአንድ በላይ ሚስት የማግባት ምክንያት በታላቁ የሙስሊም ምሁር በጋዛሊ እንደሚከተለው ተሰጥቷል፡ ‹አንዳንድ ሰዎች እንደዚህ የሚያስገድድ የግብረስጋ ፍላጎት ስላላቸው አንድ ሴት ለእነሱ በቂ አይደለችም (ከዝሙት) እነሱን ለመጠበቅ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ስለዚህም ሊያገቡ የሚመርጡት ከአንድ ሴት በላይ ነው ስለዚህም እስከ አራት ሚስቶች ሊያገቡ ይችላሉ፡፡ Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p.34፡፡

ከዚህም በላይ ወንዶች ከሴቶች ባሪያዎቻቸው ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት የማድረግ መብት አላቸው፡፡ ‹አንድ ሰው ባሪያ ሴትን ቢገዛ የግዢው ስምምነት መጨመር ያለበት ከእርሷ ጋር ግብረስጋ ግንኙነት የማድረግ መብትንም ነው› Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al-'Elmeyah, 1990, vol. 4, p፡፡ ‹ይህም ስምምነት በመጀመሪያ ደረጃ እርሷን ንብረት ለማድረግ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከእርሷ ጋር በግብረ ስጋ ግንኙነት በእርሷ መደሰትን ነው›› Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al-'Elmeyah, 1990, vol. 4, p፡፡

እንዲሁም አንድ ሰው ከሚስቱ ውጭ ከሴት ባሪያው ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት የማድረግ ምክንያትም በጋዛሊ እንደሚከተለው ተሰጥቷል፡ ‹በአረቦች መካከል የሚያስገድድ ስሜት የተፈጥሮአቸው አንድ ክፍል ስለሆነ የሃይማኖት ሰዎቻቸው ግብረ ስጋ ግንኙነት የማድረግ ፍላጎት በጣም ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለዚህም ልብን ለእግዚአብሔር አምልኮ ክፍት ለማድረግ ዓላማ እነሱ ከሴት ባሪያዎቻቸው ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነትን እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸዋል፣ ሆኖም በሆነ ወቅት ይህንን የሚፈሩ ከሆነ ስሜታቸው ዝሙትን ወደ መፈፀም ሊመራቸው ይችላል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ተግባር ባሪያ የሚሆን ልጅ ወደ መውለድ የሚመራ መሆኑ እውነት ቢሆንም፣ ማለትም የጥፋት ሁኔታ የሆነው ... ነገር ግን ልጅን ባሪያ ማድረግ ከሃይማኖት ጥፋት ይልቅ የቀለለ ጥፋት ነው፡፡ ምክንያቱም አዲስ የተወለደውን ልጅ ባሪያ ማድረግ ጊዜያዊ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ዝሙትን መፈፀም ዘላለማዊ ጥፋት ነው› Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p. 33፡፡

ጋዛሊ የዚህን አስገዳጅ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎትን ምሳሌ እንደሚከተለው ሰጥቷል፡ ‹መናኝና ምሁር የነበረው የኦማር ልጅ፣ ፆምን ይገድፍ የነበረው ከምግብ በፊት ግብረ ስጋ ግንኙነትን በማድረግ ነበረ፡፡ ከመጨረሻውም ምግብ በፊት እርሱ ከሦስት ባሪያዎች ጋር ግንኙነትን አድርጎ ይሆናል› Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p. 33፡፡

እንደዚሁም ደግሞ ቡካሪ የዘገበው፡ ‹ነቢዩ የማፍ ልማድ ነበረው (ማለትም የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ) በአንድ ሌሊት ከሁሉም ሚስቶቹ ጋር አድርጓል በዚያን ጊዜም እርሱ ዘጠኝ ሚስቶች ነበሩት› Sahih Bukhari, Arabic-English translation, vol. 7, Hadith No. 142. And vol. 1, Hadith No.268. 84፡፡ ምክንያቱም፣ ‹አንድ ጊዜ እራሱ ስለ እራሱ (ሲናገር) ለግብረ ስጋ ግንኙነት የአርባ ወንዶች ኃይል እንደተሰጠው ነው› Mohammad Ibn Saad, al-Tabakat al-Kobra, Dar al-Tahrir, Cairo, 1970, Vol 8, p. 139፡፡

እንዲሁም፣ ‹ከተከታዮቹ ሁሉ በጣም ሃይማኖተኛ የነበረው አሊ አራት ሚስቶች እና አስራ ሰባት ቅምጥ የሴት ባሪያዎች ነበሩት› Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p.27፡፡ ይህም ቁጥር የሌላቸው ሌሎች ተከታዮች ሦስትና አራት ሚስቶች እንዲሁም ሁለት ሚስቶች ያሏቸው ሆነው እያለ ነበር› Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p.27፡፡

ከላይ ባለው የቁርአን ጥቅስ ውስጥ ከባሪያ ሴቶች ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈቀድን አስመልክቶ ራዚ የተናገረው፡ ‹እግዚአብሔር ከብዙ ባሪያ ሴቶች ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት እንዲደረግ ስጦታን ሰጥቷል ይህም አንዲት ነፃ ሴትን እንደ ማግባት ቀላል የሆነ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ለባሪያ ሴቶች የሚደረጉት ሃላፊነቶችና ስጦታዎች ጥሎሽ ከሚጣልላቸው (ነፃ ሴቶች) ቀላሎች ናቸው፣ ስለዚህም ጥቂትም ይኑሯችሁ ወይንም ብዙ ምንም አያሳስብም፣ እንዲሁም በእነሱ መካከል ሌሊቶቻችሁን በማደላደል በኩል እኩል ማድረጋችሁና አለማድረጋችሁ ምንም አያሳስብም የግብረ ስጋ ድርጊታችሁን ጨረሳችሁ አልጨረሳችምም ምንም ችግር የለበትም› Razi, At-tafsir al-kabir, commenting on Q. 4:3፡፡

ተንታኙ ኮርቶቢ ያንን ጥቅስ ያየው ማለትም ቁርአን 4.3 በወንድ ሙስሊሞች አገልግሎት ላይ የሚውሉት ባሪያ ሴቶች፡ ‹የግብረ ስጋ ግንኙነትም ሆነ የገንዘብ ምንም መብት የላቸውም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር አንዲት ነፃ ሴትን እንዲሁም  በአንድ አይነት ሁኔታ ውስጥ ‹የሴት ባሪያን እንዲኖራችሁ› አድርጓል፡፡ ይሁን እንጂ ወንድ በግል ይዞታነት መብት የሴት ባሪያዎች ይኖሩታል፣ እንዲሁም ለባሪያዎች ይደረግ ዘንድ በሚገባው ደግነት› Qortobi, commenting on Q. 4:3፡፡

ስለዚህም ‹ሃይማኖታዊ የሆኑት ሰዎች የግብረ ስጋ ግንኙነት የማድረግ ፍላጎታቸው በጣም ከፍተኛ ነው፣ እንዲሁም እግዚአብሔርን ለማምለክ ልብን ነፃ ለማድረግም አላማ ነው› እነሱም እስከ አራት ሴቶች ድረስ እንዲያገቡ እና ያልተወሰነ ቁጥር ካላቸው የሴት ባሪያዎች ጋርም እንዲገናኙ ተፈቅዶላቸዋል፣ ይህም ስጦታው ‹ባሪያ የሆነን ልጅ ወደ መውለድ የሚያመጣም ቢሆን እንኳን፣ ይህም የጥፋት ዓይነት ቢሆንም እንኳን›፡፡

3. ሚስቱን በመፍታት ላይ የወንድ መብት

ፍቺ በብዙ ማህበረ ሰብ ውስጥ እጅግ አሰቃቂ ነገር ነው፡፡ ይሁን እንጂ በእስልምና የሚታየው እንደ ሕጋዊ መብት ማለትም የተፈቀደ ድርጊት እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ ሐዲት እንደሚከተለው ይናገራል፡ ‹ከተፈቀዱት ነገሮች ውስጥ በአላህ ዘንድ በጣም የተጠላው ነገር ፍቺ ነው› Mishkat al-Masabih, Book II, Divorce, Hadith No. 137፡፡

የመፍታት ኃይል በአብዛኛው ያለው በወንድ እጅ ውስጥ ነው፡፡ ቡካሪ የዘገበው ሐዲት ያሳየው ምን ያህል ቀላል፣ የተፈቀደ እና የተጠላ ድርጊት እንደሆነ ነው፡፡

አንድ ሰው በእስልምና እንዲህ ሊል ይችላል፣ ‹ማናቸውንም ሚስቶቼን ተመልከት የምትፈልግ ከሆነ እርሷን ለአንተ እፈታልሃለሁ› Sahih Bukhari, English translation by M. Muhsin Khan, Vol. VII, pp. 6&7, see Hadith No. 10፡፡ ይህም ከፈቃድ ውጭ፣ ከሚመለከታቸው ባልና ሚስትም ፍቅር ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡

‹የዖማር ልጅ እንደዘገበው፡ በስሬ በጣም የምወዳት ሚስት አለችኝ ነገር ግን ዖማር አይወዳትም እናም ‹ፍታት› በማለት ተናገረኝ፡፡ ነገር ግን እኔ አይሆንም አልኩኝ፡፡ ከዚያም ዖማር ወደ አላህ መልክተኛ መጣና ለእርሱ ጉዳዩን ነገረው፡፡ የአላህም መልክተኛ ‹ፍታት› አለኝ› Mishkat al-Masabih, Book 1, duties of parents, Hadith No. 15፡፡ (Quoted by Tirmizi and Abu Daud) ፡፡

4. ልጆችን በማሳደግ በኩል የወንድ ዕድሎች

ልጆችን በማሳደግ በኩል ወንድ ዕድለኛ ከሆነው ቡድን በኩል ነው፡፡ ጋዚሪር የሚባለው ዘመናዊ የእስልምና ሕግ ምሁር እንደሚከተለው ጽፏል፡

‹ሃናፋውያን ብዙውን የሙስሊም ማህበረ ሰብ የሰጡት የተናገሩት፡ ‹የልጆችን ማሳደግ ሁኔታ እንደሚከተለው ነው፡፡ በቅድሚያ ሚስት እስልምናን መቃወም አይኖርባትም፡፡ እርሷ እስልምናን ከተቃወመች፣ ልጆችን የማሳደግ ምንም መብት አይኖራትም፡፡ ሁለተኛም፣ እርሷ መልካም ባህርይ ያላት መሆን አለባት ምክንያቱም እርሷ በተከለከለ የግብረ ስጋ ግንኙነት መበከሏ ከተመሰከረ፣ ወይንም በስርቆት፣ ወይንም ዝቅተኛ ስራ ካላት ለምሳሌ ለቅሶ አስለቃሽ ከሆነች፣ ወይንም ዳንሰኛ ከሆነች ልጅ ማሳደግ መብቷን ታጣለች፡፡ ሦስተኛ፣ የልጅ አባት ያልሆነን ሰው ለማግባት አይፈቀድላትም፡፡ እርሷም እንደገና ካገባች ልጅ የማሳደግ ምንም መብት አይኖራትም፣ ይህም አዲሱ ባሏ ከልጁ ጋር በአባት በኩል አጎት ሆኖ ካልተዛመደው በስተቀር ነው፡፡ ነገር ግን እርሷ የሌላ አገር ሰውን ካገባች ልጅን የማሳደግ ምንም መብት አይኖራትም፡፡ አራተኛ ልጇን ያለ ጠባቂ መተው አይኖርባትም፡፡ በተለይም ልጇ ሴት ልጅ ከሆነች፣ ምክንያቱም ሴቶች ልጆች ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ስለዚህም እናትየዋ ወደ ረዘም ላለ ጊዜ ወደ ውጭ የምትሄድ ከሆነ እና ልጇን የምትረሳ ከሆነ ልጅን የማሳደግ መብት አይኖራትም፡፡ አምስተኛ፣ አባትየው ድሃ ከሆነ እና እናትየው ልጅን ያለ ክፍያ አላሳድግም ካለችና የልጁ አክስት ‹እኔ ልጁን በነፃ እጠብቀዋለሁኝ ካለች› ከዚያም አክስትየዋ ልጁን የማሳደግ መብት ይኖራታል፡፡  የእስልምናን ሃይማኖት መከተል የልጅ ማሳደግን መብት የማግኘት ሁኔታ አይደለም፣ አንድ ባል ከመጽሐፉ ሰዎች አንዲቷን ቢያገባ እርሱ ሃይማኖቱን እስካልካደ፣ ወይንም እስካልረከሰ ድረስ እርሷ ልጅ የማሳደግ መብት ይኖራታል፡፡ ነገር ግን ያ ካልሆነ ማለትም እርሷ ልጇን ወደ ቤተክርስትያን ስትወስድ ቢያያት ወይንም የአሳማ ስጋ ስትመግበው ቢያይ  ወይንም ወይንን ጠጅ ስትሰጠው ቢያይ አባትየው ከእርሷ ላይ ልጁን የመንጠቅ መብት ይኖረዋል፣ ጤነኝነት (ንፁህነት) በሁሉም ዘንድ የተደገፈ ቅድመ ሁኔታ ነውና› 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al- 'Elmeyah, 1990, vol. 4, p. 522፡፡  

የማሳደግን የጊዜ ገደብ በተመለከተ ደግሞ፣ ጋዚሪር የጨመረው፡

‹ሃኒፋይቶች እንደሚከተለው ብለዋል፡ ልጁ ሰባት ዓመት እስከሆነው ድረስ እናትየዋ የማሳደግ ሃላፊነት አለባት፡፡ ሌሎች ደግሞ የተናገሩት፣ ‹ዘጠኝ ዓመት እስኪሆነው ድረስ ነው› ነገር ግን በሕጋዊ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የመጀመሪያው ሐሳብ ነው፡፡ ለሴት ልጅ ግን ሁለት ዓይነት አመለካከቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው የወር አበባን እስክታይ ድረስ የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው የታዳጊ ዕድሜ እስክትደርስ ነው ማለትም ዘጠኝ ዓመት እስኪሆናት ድረስ ነው፣ ይህ ነው በሕግ ዘንድ ተቀባይነት ያለው› 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al- 'Elmeyah, 1990, vol. 4, p. 522፡፡

እናትየው ልጇን በጣም አስቸጋሪ በሆኑት ዓመታት ውስጥ ልትይዝ ትችላለች በሌሊት በመንቃት ጡት ልታጠባ እና የሽንት ጨርቅ ልትቀይር ሽንት ቤት አጠቃቀምን ልታሰለጥን ወ.ዘ.ተ፡፡ ከዚያም ልጅ ከመረዳት ወጥቶ መርዳት ሲችል አባትየው ይንከባከበዋል፡፡

5. በገነት ውስጥ ያሉ ወንዶች ለዘላለም ውብ ከሆኑ ድንግል ሴቶች ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነትን ይደሰታሉ፡

ሙስሊም ወንዶች በዚህ ዓለም ሕይወት ውስጥ ብዙ ሚስቶች ተፈቅዶላቸዋል፡፡ በገነት ውስጥ በውበታቸው ፍፁም በሆኑ በተጨማሪ ሴቶች ይሸለማሉ፡፡ ሙዓዝ የአላህ መልክተኛ ተናገረ ያለውን የሚከተለውን ዘግቧል፡ ‹ሴት በዚህ ዓለም ውስጥ ባሏን ማስቸገር አይኖርባትም፣ ነገር ግን ንፁህ ዓይን ያላት ድንግል የሆነችው ሚስቱ (ሁሪስ) ለእርሷ እንዲህ አትላትም፡ ‹አታስቸግሪው፡፡ አላህ ያጥፋሽና፣ እርሱ ካንቺ ጋር የሚያልፍ እንግዳ ብቻ ነው እንዲሁም አንቺን ጥሎሽ ወደ እኛ ለመምጣት ጊዜው በጣም ቅርብ ነው› Mishkat al-Masabih, Book 1, duties of husband and wife, Hadith No.62፡፡

ለዚህ ልማድ የሚሽካት ኤዲተር የሆነው በግርጌ ማስታወሻው ላይ የሚከተለውን ጽፏል፡ ‹ማንም ሴት ለባሏ ችግርና ጭንቀትን መስጠት አይኖርባትም፡፡ በቤት ውስጥ እርሷ ሰላምንና ምቾትን ልትሰጠው ይገባታል፡፡ ነገር ግን በተቃራኒው መንገድ የምታደርግ ከሆነ በገነት ውስጥ እርሷ የእርሱ ጓደኛ ልትሆን አትችልም፡፡ እዚያ ንፁህ ዓይን ያላቸው ድንግሎች የእርሱ ጓደኞች ይሆናሉ›፡፡ ምክንያቱም ቁርአን ተስፋ የገባው እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሰዎች በገነት ውስጥ ውብ የሆኑ ሴቶችን ነውና፡፡ የእነሱም ገለፃ የሚከተለው ነው፡ ‹እነሆ እነዚያ (ወንዶች) ተግባሮቻቸውን የጠበቁት የሚሆኑት በአትክልት ቦታዎች መካከል እና በውሃ ምንጭ መካከል ነው የሚሆኑት ከሐር በተሰሩና በሐር በተጌጡ ልብሶች ለብሰው ፊት ለፊት እየተያዩ፡፡ እንዲሁም ደግሞ (ይሆናል)፡፡ እኛም ከ(ሁሪዎች) ጋር እናጋባቸዋለን ነጭ ከሆኑትና የሚያምሩ ሰፋፊ ዓይኖች ካሏቸው ጋር› The Qur'an 44:51-54 (Pickthall's translation)፡፡ ‹በዚህ ውስጥ የቤት ሰራተኞች እይታቸውን በመገደብ፣ በፊታቸው በማንም ሰው ወይንም ጂኒ ያልተነኩ ሆነው እንደ ቀይ ፈርጥ ተወዳጅ፣ እንደ እምነ በረድ ውብ ሆነው› The Qur'an, 55:56-58 (Arberry's translation)፡፡ ‹ውብ እና ነጭ የሆኑት (ሁሪስ) ... ከትልቅ ጥቁር ዓይን ጋር፣ በአዳራሾቻቸው ውስጥ ተጠብቀው› The Qur'an, 55:72 (Rodwells translation)፡፡

‹በእርግጥ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት የዋስትና ቦታ ይጠብቃቸዋል፣ ይህም የአትክልት ቦታና የወይን ቦታ ነው እንዲሁም ጡታቸው ትልልቅ የሆኑ ሴቶች ሰራተኞች Pickthall in his translation of the Qur'an omits this description all together, although it is found in Dawood's, Rodwell's, and Arberry's translations) ዕድሜያቸው ተመሳሳይ የሆነ እንዲሁም ሙሉ የሆነ ፅዋ› The Qur'an, 78:33 (Arberry's translation)፡፡

ከዚህም እግዚአብሔርን የሚፈሩቱ በገነት ውስጥ ካሉ ሴቶች ጋር ይጋባሉ፡፡ እነዚያም ሴቶች ሌሎችን በፍፁም አይመለከቱም፣ ከባሎቻቸው በስተቀር፡፡ እነሱም በአዳራሾቻቸው ውስጥ ይገደባሉ፡፡ እነዚያ ሴቶች በገነት ውስጥ ያሉት ነጮች ናቸው እንደዚሁም በአረቢያ እንዳሉት ጥቁር ቆዳ እንዳላቸው አይደሉም፡፡ የእነሱም ውበት ፍፁም ነው የሚሆነው፡፡ ዓይኖቻቸውም ሰፋፊና ትልልቅ ናቸው እናም ጡቶቻቸውም ‹ካዋ-ኢብ› ናቸው፣ ማለትም ያበጡና ጠንካራዎች እንጂ የሟሸሹ (የወደቁ) አይደሉም› Ibn Kathir, commenting on Q. 78:33፡፡

እንዲሁም ሐዲት የሚነግረን፡ ‹በገነት ውስጥ ... እያንዳንዱ ሰው ሁለት ሚስቶች ይኖሩታል (በጣም ውብ የሆኑ) የጭን አጥንቶቻቸው መቅኒ ከስጋዎቻቸው ስር ያበራሉ እንዲሁም በገነት ውስጥ ሚስት የማይኖረው ማንም አይገኝም› Sahih Muslim, English translation, Hadith No. 6793, see also 6794, 6795 &6797፡፡

ሌላ ሐዲት የሚስቶችን ቁጥር ሰባ ሁለት ያደርሰዋል፡፡ ሰባ ሴቶች በተለይም ተፈጥረዋል ሁለቱም የሰው ሴቶች ናቸው Ibn-Kathir commenting on Q. 56:35-37፣ የምድር ሚስቶቹ ከውቦቹ ውስጥ ሊጨመሩ ይችላሉ፣ ነገር ግን በገነት ውስጥ ለእርሱ ተጨማሪ ሴቶች ይኖሩለታል ይህም እስከ ሰባ ሁለት ድረስም እንኳን ነው፡፡ ‹ቅዱሱ ነቢይ እንዲህ አለ፡- ‹አማኙ በገነት ውስጥ የግብረ ስጋ ግንኙነትን ያደርግ ዘንድ እንዲህና እንዲህ ዓይነት ጥንካሬ (ብርታት) ይሰጠዋል፡፡ ቀጥሎም እንደሚከተለው ተጠይቆ ነበር፡ ‹ኦ የአላህ ነቢይ!` እርሱ ይችላልን?› እርሱም አለ፡ ‹እርሱ የአንድ መቶ ሰዎች ጥንካሬ ይሰጠዋል› Mishkat al-Masabih, English-Arabic translation, Book IV, Chapter XLII, Paradise and Hell, Hadith No.24፡፡ (ይህ ሐዲት የተጠቀሰው ከቲሪምዚ ሲሆን በቲሪምዚ የተመደበውም እንደ ሳሂህ ነው ማለትም ጤናማና ምንም ስህተት የሌለው ሐዲት ተደርጎ ነው›) Sunan at-Tirmizi, kitab sifat al-Ganah, Hadith No. 2536፡፡

ኢብን ካቲር በትንተናው ውስጥ ያተኮረበት በገነት ውስጥ የሚደረገው የግብረ ስጋ ግንኙነትን ተፈጥሮ ልክ እንደ ምድር የሆነ አድርጎ በሌላ ሐዲት እንደተገለፀ ነው፡

‹ነቢዩ እንደሚከተለው ተጠይቆ ነበር፡ እኛ በገነት ውስጥ ግብረ ስጋ ግንኙነት ይኖረናልን? እርሱም መለሰ፡ ‹አዎ በእርሱ ነፍሴን በእጆቹ በያዛት፣ እናም ይደረጋል ዳማን፣ ዳማን (ማለትም በመረበሽና በግፊት የሚደረግ ግብረ ስጋ ግንኙነት ነው Ibn-Kathir, vol. 8, page 11, commentary on Q. 56:35-37, published by Dar Ash-sha'b, editorial footnote by the publisher explaining the meaning of 'dahman'.)፣ ይህም ካለቀ በኋላ እርሷ እንደገና ንፁህ እና ድንግል ወደመሆን ትመለሳለች› Ibn-Kathir, vol. 8, commenting on Q. 56:35-37. 108. The Qur'an 36:55, published by Dar Ash-sha'b, editorial footnote by the publisher explaining the meaning of 'dahman'፡፡

እስልምና የሴትን ድንግልና ለዘላለም የመውሰድን (ማለትም ሁልጊዜ እንደገና) ጉዳይ በባህል የተያያዘው ከገነት ጋር ነው፡፡ በጣም ታዋቂው ተንታኝ አል-ጃላላያን ያየው በቁርአን ጥቅስ ላይ የተጠቀሰውን መደሰትን ነው ‹‹የገነት ነዋሪዎች አሁን በመደሰት ላይ ናቸው› Ibn-Kathir, vol. 8, The Qur'an 36:55, published by Dar Ash-sha'b, editorial footnote by the publisher explaining the meaning of 'dahman'፡፡ ‹ይህም የሴቶችን ድንግልና የመውሰድ ተግባርን ይጨምራል› በማለት ነው፡፡ Tafsir al-Jalalayn on Q. 36:55፡፡

ታላቁ ምሁር ጋዛሊ የጠቀሰው አል-ኦዛይ ከቀደሙት ምሁራን እንዱ የሆነውና ከላይ ያለውን ጥቅስ የተነተነው ‹በደስታ ተጠምደዋል ማለት የድንግሎችን ድንግልና የመውሰድ ነው በማለት ተናግሯል›፡፡ Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol IV, p. 575፡፡ እንዲሁም ደግሞ ታላቁ ተንታኝ ኢብን አባስ ከላይ ስላለው ጥቅስ የተናገረው፡ ‹(ፋክሁን) ማለት የድንግሎችን ድንግልና በመውደስ መደሰት ማለት ነው› ብሎ ነው፡፡ Ibn 'Abbas, Tanweer al-Miqbas, commenting on Q. 36:55፡፡

አንድ ሰው እጅግ በጣም የግብረ ስጋ ግንኙነት ደስታ የሚኖረው በምድር ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በገነትም ነው፡፡ በምድር ላይ ብዙ ሴቶችን አግብቶ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ምድራዊ ሕይወቱም ካለፈ በኋላ በገነት ውስጥ በጣም ቆንጆ የሆኑ ሴቶች እንዲኖሩት ተስፋ ሊያደርግ ይችላል፡፡ እርሱም እስከ ሰባ ሁለት ውቦች ሊኖሩት ይችላል፣ እንዲሁም የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ እንዲችል የአንድ መቶ ሰዎች ብርታት ይሰጠዋል፡፡ እርሱም ግብረ ስጋ ግንኙነትን በታላቅ ግፊትና ረብሻም ሊያደርግ ይችላል፣ በሌላ ጎኑ ለሴቶች ግን ምንም የተስፋ ቃል አልተገባላቸውም፡፡ ለአንድ ሴት ስለ አንድ ወንድ እንኳን የተገባ የማረጋገጫ ቃል የላትም፡፡

አሁንም እንደገና ሁሉም ጥቅምና ደስታ ያለው ለወንዱ ነው፣ ሴቶቹ ለዘላለም ለእርሱ ዓላማ መጠቀሚያ መሆን አለባቸው፡፡ ደስታ የእሱ ነው ለእርሷ ግን በዚህም ዓለም ሆነ በሚመጣው ዓለም ያላት ረብሻ ነው፡፡ 

የዚህ ምክንያቱ ምንድነው?

በእስልምና ወንዶች ከሴቶች ይልቅ እንዲህ ዓይነት መብት ያላቸው ለምንድነው? የሚከተለው ጽሑፍ በአብዛኛው የተወሰደው በእስልምና ሕግ ላይ በአሁኑ ጊዜ ባለ በዘመናዊው ምሁር ጋዚሪ ከተዘጋጀው ስራ ነው፣ ይህ የእሱ ስራ ወንዶች በሴቶች ላይ ለምን የበለጠ መብት እንዳላቸው ይገልጥ ይሆናል፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡ 

ሴቶች በንፁህ እስልምና በሚለው ጽሑፍ ስር የቀረቡት እውነታዎች በትክክል እንደሚያስረዱት ከሆነ በሙስሊም ሴቶችና ወንዶች መካከል ያለው ልዩነት እጅግ በጣም የጎላ ነው፡፡ ግን ለምን፣ ልዩነቱስ የመነጨው ከማን ነው? የሚሉ ጥቄዎችን ስናነሳ መልሱ ከእግዚአብሔር ወይንም ደግሞ ከሰዎች መሆን አለበት ነው፡፡ መቼም ከእግዚአብሔር ሊሆን አይችልም ምክንያቱም እግዚአብሔር ወንዶችንም ሴቶችንም እኩል እንደሚያይ ተፈጥሮ እንኳን እራሱ ያስተምረናልና፡፡  ታዲያ ከማን ነው፣ መሆን ያለበት ከሰው ባህላዊ ልማዳዊ አመለካከት እንዲሁም ከባህል ከመነጨ የወንዶች የበላይነትና የእራስ ወዳድነት ነው፡፡ ከዚህ በላይ ያሉት ሐዲቶች እንደሚያመለክቱት የአረብ ወንዶች የግብረ ስጋ ግንኙነት ከፍተኛ ፍላጎት ችግር አለባቸው ይላሉና፡፡ 

የሆነው ሆኖ፣ የሴቶችና የወንዶች ከፍተኛ ልዩነቶች ምንጭ እግዚአብሔር ከሆነ የሙስሊሞችን አምላክን ፍትሃዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚጥል ነው፡፡ ከሰዎች ነው የመነጨው ወደማለት ከመጣን ደግሞ የእስልምናን እውነተኛነት ችግር ውስጥ የሚጥል ነው፡፡ 

በሁለቱም መንገድ እስልምናን እንደ ትክክለኛ እምነት ለመውሰድና ለመቀበል ለአዕምሮ በጣም ይከብዳል፡፡ እዚህ ላይ ነው ለአንባቢዎች አዕምሮ ግልጥ ጥያቄን ለማቅረብ የምንፈልገው፡፡ የምንከተለውን ሃይማኖት የምንከተልበት አንድ የተጨበጠ ቁም ነገርን ልናገኝበት ያስፈልጋል፡፡ ከዚህም በላይ ለሰዎች ልጆች ሁሉ ማለትም ያለምንም የፆታ ልዩነት የሚሰጠው የተስፋ ቃል ምንድነው የሚለውንም ልንጠይቅ ይገባናል፡፡   እውነተኛው አምላክ እግዚአብሔር ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች ያለው አመለካከት ምንድነው? ይህንን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ዘር ያለምንም የፆታ ልዩነት በእግዚአብሔር ላይ ያመፀና የእግዚአብሔር የፍርድ ቁጣ የሚጠብቀው እንደሆነ ነው፡፡ 

ነገር ግን ለኃጢአተኛው ለሰው ልጅ እግዚአብሔር ያዘጋጀው አስደናቂ ምህረት እጅግ ግሩም ነው፡፡ ይህም ምህረት የመጣው በልጁ በጌታ በኢየሱስ ወደ ምድር መምጣትና በመስቀል ላይ ኃጢአተኞችን ወክሎ መሞት ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ማንኛውም ሰው፣ ማለትም ወንድም ይሁን ሴት ንስሐ ገብቶ በጌታ በኢየሱስ በኩል ወደ እግዚአብሔር ለምህረት ቢቀርብ ይቅር እንደሚባል አዲስ ሕይወትን እንደሚቀበልና የዘላለምም መንግስት ሕይወትን እንደሚያገኝ ይናገራል፡፡  ይህ መልእክት ወጥ ነው፤ ሎጂካል ነው፤ የእግዚአብሔር ነው፣ አንባቢዎች ሆይ ለዘላለም ሕይወት ወደሚጠቅማችሁ ወደዚህ መልእክት እንድትመጡ መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ እንድታነቡ ወደ ፈጣሪያችሁ ወደ እውነተኛው እግዚአብሔር እንድትመጡ እንጋብዛችኋለን፣ እግዚአብሔር በፍቅሩና በፀጋው ይርዳችሁ አሜን፡፡

ወደ ክፍል ሰባትና ስምንት ይቀጥሉ::

የትርጉም ምንጭ:  The Place of Women in Pure Islam  

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ