3. የዲህሚ ውል

ዕራፍ 3

የዲህማ ውል

እንደ ጎርጎሳውያኑ የዘመን አቆጣጠር 2006 . የሮማው ካቶሊክ ጳጳስ የነበሩት ቤኒዲክት በብዙዎች ዘንድ የታወቀላቸወን የረጌንስበርግ ገለፃ አድርገው ነበር፡፡ የንግግራቸውንም ሀሳብ የወሰዱት ንጉስ ማኑኤል ሁለተኛ የተባሉት የመሐመድን በሰይፍ የታጀበ እምነትን የማሰራጫ ስብከት ትእዛዝ በተመለከተ የተናገሩትን በመጥቀስ ነበር፡፡

የጳጳሱ መልዕክት በዓለም ዙርያ ከሚኖሩ ሙስሊሞች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ አስነስቶ ነበር፡፡ አንድ ትኩረትን የሳበ ምላሽ የተሰጠው ግን የሳውዲ አረቢያው የእስልምና ህግጋትን የማስረዳት ስልጣን በነበራቸው ሼከ አብዱላዚዝ አል ሼክ ነበር፡፡ በወቅቱ ርዕሰ ጉዳዩን አስመልክቶ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫእስልምና ኃይልን በመጠቀም የተጀመረ ኃይማኖት አይደለምብለዋል፡፡ የሙግት ሀሳባቸውንም ሲያጠናክሩበዚህ ምክንያት እስልምናን መክሰስ ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም በእምነት ጉዳይ አረመኔ መሆን የሚቻለው በሦስተኛ ምርጫ ነው፡፡ የመጀመርያው ምርጫ ሰላማዊ ነው፡፡ ሁለኛተው ሰይፍ ማንሳት ነው፡፡ሦስተኛውን እንዲህ ሲሉ ነበር ያስቀመጡትእጅ እንዲሰጡ ማድረግና ቀረጥ ማስከፈል ከዚያም በቀዬአቸው ለመኖር ፈቃደኛ ይሆናሉ፡፡ ይሄንንም የሚያደርጉት ኃይማኖታቸው በሙስሊሞች የበላይ ጠባቂነት ስር መሆኑን ስለሚያጤኑ ነው

የእስልምና ህግ አዋቂው ከመሐመድ ምሳሌ በመነሳት ያነበቡትን እንዲህ ሲሉ ያስቀምጣሉቁርአንንና የመሐመድን ፈለግ ያነበበ ሁሉ አንድ የሚረዳው እውነት አለ”  የህግ አዋቂው ለማመላከት የሞከሩት ሦስቱ ምርጫዎች እነዚህ ነበሩ፡፡

1)    ወደ እስልምና መለወጥ

2)    ሰይፍ (መግደል ወይም መገደል)

3)    ለእስልምና ኃይል እጅ መስጠት

የመጀመሪያዎቹ ሁለት ምርጫዎች ወደ መሐመድ የሚወስዱ ናቸው፡፡ እርሱም እንዲህ ነበር ያለው

አላህ ትእዛዝን ሰጥቶኛል፡፡ ትእዛዙም ሰዎች ሁሉ ከአላህ በቀር ሊመለክ የሚገባው ሌላ ነገር እንደሌለ እስኪመሰክሩ ድረስ እንደዚሁም መሐመድ የአላህ  መልዕክተኛ መሆኑን እስኪመሰክሩ ድረስ መዋጋት ነው፡፡ ይሄንን ማድረግ ከቻሉ እራሳቸውንም ንብረታቸውንም ከኔ ማዳን ይችላሉ፡፡

ነገር ግን ይህ አባባል እስልምናን ወይንም ሰይፍ ከመምረጥ፣ እጅ ከመስጠት እና ጀዝያን ከመክፈል በተጨማሪ መሐመድ በሰጠው ሌላ አማራጭ ተሻሽሏል፡፡

በአላህ ስምና አላህ በሚፈቅደው መንገድ ተዋጉዋቸው በአላህ በማያምኑት ላይ ቅዱስ ጦርነት ክፈቱባቸው፡፡ መድበለ አማልክት የሚያመልኩትን ጠላቶቻችሁን ስታገኙአቸው ወደ ሦስቱም ዓይነቶች ግብዣ ጋብዙዋቸው፡፡ እነርሱ ከነዚህ መካከል ለአንዱ ምላሽን ቢሰጡ እናንተም በመቀበል ክፉ ከማድረግ ተቆጠቡ፡፡ እስልምናን እንዲቀበሉ ጋብዟቸው፡፡ ምላሽን የሚሰጧችሁ ከሆነ ተቀበሏቸው፣ እነርሱንም ከመዋጋት ተቆጠቡ... እስልምናን ለመቀበል እምቢ ካሉ ጀዚያን ጠይቋቸው፡፡ ለመክፈል ከተስማሙ ተቀበሏቸውና እጃችሁን ከነርሱ ላይ ሰብስቡ፡፡ ግብሩን የማይከፍሉ ከሆነ የአላህን እርዳታ በመፈለግ ተዋጓቸው፡፡

ሦስተኛውን ምርጫ አስመልክቶ ዋና ሙፍቲ ደርሼበታለሁ የሚሉትእውነታእንደሚያሳየው የቁርአንና የመሐመድን ፈለግ በተመለከተ ታላላቅ የእስልምና ተንታኞች  ትርጓሜዎች  እንደሚገልጹት ከሆነ ሙስሊም ያልሆኑት ሰዎች እንኳን በታሪክ ውስጥ በሸሪኣ ህግ የተገዙበት ጊዜ ነበር፡፡

ኢስላማዊ ለሆነው አገዛዝ እጃቸውን የሰጡ ማኅበረሰቦች አስገዳጅ በሆነ የቃል ኪዳን ውል የዲህማን ውል እንደተቀበሉ ይቆጠራሉ፡፡ በዚህ ውል መሰረት ሙስሊም ያልሆኑት ማኅበረሰቦች  እጃቸውን በመስጠት የሚገቡት ግዳጅ ያለበት ቃልኪዳን  በዝቅተኝነት የተሸነፉ ከመሆናቸውም በተጨማሪም አመታዊ ግብር ለሙስሊሞች እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፡፡ እንደዚሁም ሙስሊም ያልሆኑት ድል ከመደረጋቸው በፊት የነበራቸውን እምነት እንዲከተሉ ይፈቀድላቸዋል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የሚያልፉ ሙስሊም ያልሆኑ ህዝቦች በግዳጅ የተጨቆኑ ይባላሉ፡፡

ይህ የማስገደድ ሥርአት ቁርአንን መሰረት ያደረጉ ሁለት መሰረታዊ ፖለቲካዊ መርህ ያላቸው መግለጫዎች አሏቸው፡፡ 

1)    እስልምና በሌሎች ኃይማኖቶች ላይ ድልን መቀዳጀት አለበት    (4828)

2)    እኩይና ሰናይ የሆነውን አስተምህሮ በተመለከተ ሙስሊሞች በኃይል የበላይ በመሆን ሊቆጣጠሩት ይገባል፡፡ (3110)

 

የጂዝያ አከፋፈል ስርኣት

የእስልምና ህግ  - የሸሪኣ ህግ  የዲህማ ውል እስልምናን ያልተቀበሉትን ሰዎች ሙስሊሞች ባይተውአቸው ኖሮ መሞት የሚገባቸው እንደሆኑ ይቆጥራቸዋል፡፡  ቀድሞ ከእስልምና በፊት የነበረውን  አስተሳሰብ በምንመለከትበት ጊዜ  ሰዎችን  ድል ማድረግ ከቻልክ እና  እንዲኖሩ ብትፈቅድላቸው  የአንተ ባለ እዳዎች ሆነው ይቀጥላሉ የሚል አንደምታ ነበረው፡፡ በዚህም ምክንያት  ተገደው የሚከፈለውን  አመታዊው የቀረጥ ሥርአት እንዲከፍሉ የሚደረጉት በእስልምና መንግስት ስር ያሉ አዋቂ ወንዶች  ናቸው፡፡

እንደ የእስልምና መዝገበ ቃላት አዘጋጆች ግላፄ ከሆነ ጂዝያ ማለት፡

...በእስልምና መንግስት አስተዳደር ስር ያሉ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች የስምምነት ውሉ እንዲጸድቅ ይስማማሉ (በማስገደድ የሚደረግ ውል)፡፡  ይሄ ደግሞ ጥበቃን ያረጋግጥላቸዋል፡፡  እንደዚህ የሚደረግላቸውም እንደ ካሳ ስለሚቆጠርላቸው ነው፡፡ (ሌን የአረቢኛ- እንግሊዘኛ መዝገበ ቃላት)

19ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩ አልጄሪያዊ ተንታኝ አት-ፋይሽ ይሄንን መርህ በማብራሪያ መፅሐፋቸው የአት ተውባህ 9 29 ሀሳብ እንደገለጹት

እንደዚህ ተብሎ ነበር፡ (ጂዝያ) ለደማቸው እርካታ የሚሰጥ ነው፡፡ እገሌ ላለመገደሉ የሚገባውን ሂሳብ ከፍሏል ይባላል፡፡ ዓላማውም የመግደልና ባሪያ የማድረግ ሥራቸውን ለማካካስ ነው፡፡ ይሄ የተደረገው ከሙስሊሞች ጥቅም አንፃር ነው፡፡

ወይንም ዊሊያም ኢቶን ከአንድ ክፍለ ዘመን ቀደም ብሎ አጭርና የተሟላ ማብራሪያ በሚሰጠው የቱርክ ግዛት አሰሳ በተሰኘ (1979 በታተመ) መጽሐፋቸው እንደተናገሩት

ቋሚ የሆነውን ቀረጥ (ጂዝያ) በሚከፍሉበት ወቅት ለክርስቲያን ተገዢዎች የተሰጠው ስያሜ በራሱ የሚያመለክተው የተከፈለው ገንዘብ በዚያ ዓመት ጭንቅላታቸው ከአንገታቸው ሳይለያይ እንዲሄዱ ስለተፈቀደላቸው የከፈሉት ማካካሻ እንደሆነ ነው፡፡

ሦስተኛው ምርጫ  የአመታዊው ጂዝያ የአከፋፈል ሥርአት ከበድ ያለ ትዕምርታዊ መልዕክት የተገለጸበት መንገድ ነው፡፡ ዲህሚ የሆኑ ወንዶች ይሄንን ሥርአት እስከ አሁኗ ሰአት ድረስ በመላው የእስልምና ሀገራት ሁሉ እንዲተገብሩ ይጠየቃሉ፡፡ አንገታቸው ላይ አንዴ ወይንም ሁለት ጊዜ እንዲመቱ ይደረጋል፡፡ በገመድ አንገት ላይ የመታሰር ሥርአትም ይደረጋል፡፡ ይሄ የሚያመለክተው  ሰው በእድሜ ዘመኑ ሁሉ ቀረጥ ለመክፈል ራሱን ማስገዛቱን ነው፡፡ ሥርአቱ የጂዝያ ክፍያን በተመለከተ የተደነገገ የሞት ቅጣትን በይቅርታ ያልፋል፡፡  ሦስተኛው ምርጫ ይሄንን የሰዎችን መሰዋት አስመልክቶ ደርዘን የሆኑ ማጣቀሻዎችን ያቀርባል፡፡ ይሄም ደግሞ ከሞሮኮ እስከ ቡካራ 9ኛው -20ኛው ክፍለ ዘመን ኢስላማዊና ኢስላማዊ ካልሆኑ ምንጮች የተወሰደ ነው፡፡  ይሄኛው ሥርአት በአንዳንድ የእስልምና አገራት ማለትም የመንና አፍጋኒስታን አይሁዶች ወደ አገራቸው እስከተመለሱበት 1940ዎቹ መጨረሻና 1950ዎቹ መጀመሪያ ቀጥሏል፡፡ በቅርብ ጊዜ ባሉት ዓመታት ወደ ድሮው አካሄድ ለመመለስ ብዙ ጥሪዎች እየተደረጉ ናቸው፡፡

ሙስሊም ያልሆኑትን ማንነት በተመለከተ ማንነታቸው የሚወሰነው ድል ባደረጓቸው ሙስሊሞች እጅ ስር ይሆናል ማለት ነው፡፡ የእስልምና ተንታኞች እነዚህ ሰዎች የማመስገንና  በትህትና ዝቅ የማለትን አመለካከትን ከራሳቸው ጋር ሊያዋህዱት ይገባል በሚለው እሳቤ ወጣ ያለ  አቋም አላቸው፡፡

አብዛኛዎቹ የሸሪኣ ህጎች የተቀረጹት ሙስሊም ያልሆኑት በበታችነት እንዲሸማቀቁና አደጋ የተጋረጠባቸው መሆኑን እንዲያውቁ በሚያስገነዝብ መልኩ ነው፡፡ እንደምሳሌ አድርገን ብንወስድ

§  በዲህሚ የጭቆና በደል ውስጥ ያሉት በሸሪኣ ፍርድ ቤት ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ይሄ ደግሞ በሁሉም አቅጣጫ አደጋ ላይ መሆናቸውን ጠቋሚ ነው፡፡

§  በዲህሚ የጭቆና አሰራር ስር ያሉት ቤታቸውን ከሙስሊሞች በላይ ከፍ አድርገው እንዲሰሩ አይፈቀድላቸውም፡፡

§  በዲህሚ የጭቆና አገዛዝ ስር ያሉት ፈረስ እንዲጋልቡና እራሳቸውን ከሙስሊሞች በላይ ከፍ አድርገው እንዲሄዱ አልተፈቀደላቸውም፡፡

§  በዲህሚ ባርነት ውስጥ ያሉት እራሳቸውን ከሙስሊሞች ጥቃት እንዲከላከሉ አልተፈቀደላቸውም፡፡ ይሄ ደግሞ ከሙስሊሞች ለሚሰነዘርባቸው ማንኛውም ዓይነት ጥቃት ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡

§  ማንኛውም ኃይማኖትን የሚያሳዩ ምልክቶች እንዲያስተዋውቁ አይፈቀድላቸውም፡፡

§  በእስልምና ላይ የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ትችት አይፈቀድም፡፡

§  በዲህሚ ጭቆና ውስጥ ያሉት ለየት ያለ አለባበስ መልበስ አለባቸው፡፡ የቀለም አመራረጣቸው ኢስላማዊ ቃና እንዲኖረው ይጠበቃል፡፡

§  ሙስሊም ያልሆኑትን ዝቅ ብለው እንዲገዙ የሚያስገድዱና ከሙስሊሞቹ የሚለዩ ብዙ ህጎች ተደንግገዋል፡፡

እነዚህ ህጎች በማኅበራዊና ህጋዊ አገላለፆችአናሳዎችናቸው የሚል አንድምታ ይሰጣሉ (929)፡፡

የዲህሚ ሥርአት ሙስሊም ያልሆኑትን ማኅበረሰቦች የበላይነት ለመቀነስ የተቀረጸ አካሄድ ነው፡፡ 18ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩት ሞሮኮዋዊው ተንታኝ ኢብን አቢጃ እንደ ገለጹት ዓላማው ምድራዊ ያልሆነ ምንባብ፣ የተተረጎመና ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስተኛው ምርጫ ተብሎ የታተመና ነፍስን የሚገድል ነው፡፡

የዲህማ ውልን አስመልክቶ ታዋቂ ምሳሌ የሚሆነው የዑመር ቃልኪዳን በመባል የሚታወቀው  ክርስቲያኖች ይሄ ቅጣት በራሳቸው ላይ እንዲሆን የሚለምኑበት አካሄድ ነው፡፡

እነዚህ ለደህንነታችን ስንል በራሳችንና የኛን እምነት በሚከተሉ ሰዎች ላይ የደነገግናቸው አኳሆኖች ናቸው፡፡ ለናንተ ጥቅም ስንል በራሳችን ላይ የደነገግናቸውን እነዚህን ደንቦች ጥሰን ብንገኝ የኛ ዲህማ ተሰብሯል ማለት ነው እናም በማይታዘዙ እና በአመጸኞች ሕዝቦች ላይ እንድታደርጓቸው የተፈቀዱትን ነገሮች ሁሉ በኛ ላይ ልታደርጉ ትችላላችሁ፡፡

በኢብን ቁዳማም ተመሳሳይ የሆነ ነጥብ ቀርቧል፡፡ የዲህማ ውሉን በተመለከተ የዲህማ ውሉ ሳይጠበቅ ቢቀር ዲህሚው ንብረቱንና ሕይወቱን ያጣል፡፡

በከለላ ውስጥ ያለ፣ ነገር ግን የከለላ ስምምነቱን ደንብ የጣሰ ሰው በግዳጅ የሚከፍለውን ቀረጥ (ጂዝያ) ባይከፍል ወይንም ለማኅበረሰቡ ህግ መገዛትን ባይወድ ራሱን እና ንብረቱን ሕገወጥ ያደርጋል (ሐላል - በሙስሊሞች ለመገደል ወይንም ለመያዝ ራሱን በነፃ ያቀርባል)፡፡

በቅጣት ምክንያት ራስን የመሰዋት ድንጋጌ ባለበት ስርአት የጂዝያ ክፍያ እንደየደም ውልወይንምየደም ቃልኪዳን”  ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ተሳታፊዎችም በራሳቸው ላይ ሞትን የሚቀሰቅሱና  የመሞቻ መንደጋቸውንም የሚጠርጉ ናቸው፡፡ ይህ የሚሆነው ደግሞ የገቡትን ውል መጠበቅ በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡

እንደዚህ ዓይነቱ ቃል ኪዳን ለምዕተ ዓመታት ሚስጥራዊ በሆኑ ማኅበረሰቦችና በጥንቆላ ቡድኖች ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን  ሰዎች እንዲገዙና እንዲታዘዙ  የስነልቦናና መንፈሳዊ ኃይልን ተጠቅሞ እንቅስቃሴያቸውን በማሰር  የበላይነትን የማግኛ መንገድ ነው፡፡

የጂዝያ ስርአት ምስሌያዊ በሆነ መልኩ የዲህሚን ፈቃድ ይጠይቃል፡፡  እንደዚህም ሲባል  የዲህሚን ህግ የሚተላለፍ የሚከፍለውን የቅጣት ካሳ የሚያሳይ ነው፡፡ ማለትም በእድሜ ዘመን ሁሉ የሚደረግ ቅጣት ነው፡፡ ይህ ማለት እራስን መርገም ማለት ነው፡፡ ሂደቱምከገባሁት ኪዳን አንዱን ብሰብር  ጭንቅላቴን(ራሴን) የመቁረጥ ሙሉ መብት አለህእንደማለት ነው፡፡ ስለሆነም አንድ ሰው የዲህሚን ህግ ቢተላለፍ በራሱ ላይ የሞት ቅጣት እንደወሰነ ይቆጠራል፡፡

ሦስተኛውን ምርጫ በተመለከተ የዲህሚ ማኅበረሰቦች በነሱ ላይ የሚታወጅባቸውን ጂሃድ እስከ ምን ድረስ እንደሚታገሱ አያሌ ምሳሌዎች አሉ፡፡ ሰዎቹ የዲህሚን ህግ ይጥሳሉ ወይንም እውነታውን ይገነዘባሉ፡፡ የአብዛኛዎቹን የዲህሚ ማኅበረሰብ  ታሪክ በምንመለከትበት ጊዜ እጅግ አሰቃቂ የሆኑ ታሪካዊ ድርጊቶች እንደተከናወኑ መመልከት እንችላለን፡፡ ለምሳሌ ያህል  ጭፍጨፋ፣ አስገድዶ መድፈር እና ንብረትን መዝረፍ የተደረገባቸው ሲሆን ሙስሊም ባለመሆናቸው ብቻ ወንጀል ተፈጽሞባቸው በዝቅተኝነትና በመንፈሳዊ  ቀንበር ውስጥ ገብተውና ስነልቦናቸው ተጎድቶ በኅብረተሰቡ ውስጥ እንዲመላለሱ ተደርጓል፡፡

ዲህማዊነት

ዲህማዊነት (ዲህሚቲውድ)  የሚለው ሀሳብ አጠቃላይ ሁኔታው  የዲህማ ቃልኪዳን የሚያስከትላቸውን አጠቃላይ አኳኋኖች ይገልጻል፡፡ ጾታዊነትና ዘረኝነትን መግለጽ እንደሚቻለው ዲህማዊነትን በህጋዊና ማህበራዊ መዋቅር  ብቻ መግለጽ አይበቃም ነገር ግን በበታችነት ስነ ልቦና እና የተጨቆነ ማህበረሰብ ነገን ለማየት ካለው ፍላጎት የተነሳ ራሱን ዝቅ አድርጎ ለማገልገል ባለው ፍቃደኝነትም ጭምር ነው፡፡

የመካከለኛው ዘመን ታዋቂው አይሁዳዊ ሊቅ ሜሞንዲስባናምንበትም አዋቂውንም ወጣቱንም ተቀብለናል የትህትናን ህይወት ራሳችንን አለማምደናልሲል ሀሳቡን ያስቀምጣል፡፡ 20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ይኖር የነበረው ጆቫኒ ሲቪልጂክ የተባለ ሰው እንደገለጸው የቱርኮችንና የአልባኒያ ሙስሊሞችን ገዢነትና የኃይል ጥቃትን መፍራት ለትውልድ እየተላለፈ መምጣት በባልካን አካባቢ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች የስነልቦና ተፅዕኖ ነበረው፡

የበታችነት ስሜት የሚሰማቸው፣ ባርያ ተብለው ስም የተሰጣቸው ዋና ስራቸውም በጌታቸው ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘት፣ በፊቱ ዝቅ ማለትና እርሱን ማስደሰት  ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች አፋቸው የሚዘጋ ሚስጥረኞች፣ ጮሌዎች፣ በሌሎች ላይ እምነት መጣል የማይችሉ ግብዞችና የማምለጫ መንገድ የሚቀይሱ ናቸው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ በሰላም ለመኖርና የሚደርስባቸውን ኃይለኛ ቅጣት ለማስወገድ ነው፡፡ ቀጥተኛ የሆነው ጭቆናና በኃይል ማጥቃት በሁሉም ክርስቲያኖች ዘንድ በሚባል መልኩ የፍርሃትና የጭንቀት ስሜት እንዲሰማቸው ትልቅ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ ጆቫኒ አያይዘው እንደሚናጉት  በሜቄዶኒያ በነበርኩ ጊዜ ሰዎች  “በህልማችን እንኳን ሳይቀር ቱርካውያንና አልባናዊያን ሲያባርሩን እናልማለን”  ብለው ሲናገሩ ሰምቻለሁ፡፡

በዲህሚ ህግ ሙስሊም ያልሆኑት በዝቅተኝነት ስሜት ውስጥ ሲገቡ ሙስሊም የሆኑት ደግሞ የበላይ እንደሆኑ ይታሰባል፡፡ ሙስሊሞቹ  ቸርነትን የሚያደርጉ እንደሆኑ ተደርጎም ይቆጠራል፡፡ ቀድሞ ሙስሊም የነበሩና ወደ ክርስትና የተለወጡ ኢራናዊ  ሰው ይህንን አስመልክቶ እንዲህ ነበር ያሉትአሁንም ክርስትና የሚታየው የበታች የሆኑ ሰዎች ኃይማኖት እንደሆነ ነው፡፡ እስልምና የጌቶችና የገዢዎች ኃይማኖት ነው፡፡ ክርስትና የባሪያዎች ኃይማኖት ነው፡፡

እስልምናን ያልተቀበሉትን መጨቆን የሚለው ንጽረተ ዓለም ሙስሊም ያልሆኑትን የበታች የሚያደርግ ጎጂ ልማድ ነው፡፡ ሙስሊሞች ተፎካካሪ ለመሆን የሚማሩበት ሁኔታ ካልተፈጠረ ራሳቸውን ይጎዳሉ፡፡ ይሄም ደግሞ መሰረታዊ ችግር ነው፡፡ በኃይማኖት ሰበብ ሀብትን የመቆጣጠር አካሄድና ጭቆናዊ አገዛዝ  ሙስሊሞችን ሀሰት ወደ ሆነ የበላይነት ስሜት ላይ እንዲታመኑ ከማድረጉም በተጨማሪ  ኋላ ላይ እያደከማቸው ይሄዳል፡፡ የሚያመጣውም ጥፋት እነርሱ ስለ ራሳቸውና ስለ ዓለም የሚኖራቸው መረዳት የተዛባ እንዲሆን ማድረጉ ነው፡፡

 

 

በምዕራቡ ዓለም ያለ ጭቆና

በሦስተኛው ምርጫ ላይ ከተደነገጉት ነጥቦች አንደኛው ምንድነው? ብለን የጠየቅን እንደሆነ የአመለካከት መዛባትን ጠብቆ የሚያስኬድ ሂደት ነው፡፡ የምዕራቡ ዓለም ህዝቦች የጭቆና አገዛዝን አስመልክቶ ያላቸው ንፅረተ ዓለም እየጨመረ እንደመጣ መመልከት ይቻላል፡፡ ይሄ ደግሞ የተገለጠበትን ሁኔታ እንደ ምሳሌ አድርገን ብንወስድ በምዕራቡ ዓለም የሚኖሩ መሪዎች እስልምናን ሲያሞጋግሱ ማየት የተለመደ መሆኑ ነው፡፡ ይሄ ብቻም ሳይሆን የሰላም ኃይማኖት እንደሆነም ያውጃሉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩም ለእስልምና ያላቸውን ምስጋናም ይገላጻሉ፡፡ ይሄንን ሀሳብ እንደ ማስረጃ ለማቅረብ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2009 .. የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በካይሮ ባደረጉት ንግግርየስልጣኔ ባለውለታው እስልምና ነውሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በዲህሚ የአገዛዝ ጭቆና ስር ያለ ሰው የሚሰማው ስሜት ቢኖር ድል ላደረጉት ሰዎች ህይወቱን  አሳልፎ መስጠት እንዳለበት ነው፡፡   እንግዲህ ከዚህ የጭቆና አገዛዝ ጋር የተያያዘው ስልጣኔ  የእስልምናን ባለውለታነት አመላካች ነው ተብሎ ታምኗል፡፡

የዚህ የጭቆና አገዛዝ ንጽረተ ዓለም የተገለጠበት ሌላው መልኩ ደግሞ በማያቋርጥ ሁኔታ ታሪካዊና ስነመለኮታዊ አካሄድን የሚክዱበት መንገድ ነው፡፡ ክህደቱ ደግሞ አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን የሚደመስስና ፖለቲካዊ ንግግር ያለው ነው፡፡

በምዕራቡ ዓለም ያለ የጭቆና አገዛዝ አዲስ የሚባል ክስተት አይደለም፡፡  በአውሮፓ ያሉትን አብዛኛዎቹን አገራት ስንመለከት ጂሃድ ታውጆባቸው ሲሰቃዩ መኖራቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ እንደ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ስፔይን፣ አየርላንድ እና እንግሊዝ ያሉ አገራት ህገ ወጥ የጂሃድ ጥቃት ሰላባዎች መሆናቸው እየታየ ነው፡፡

ምንም እንኳ የጂሃድን ሽብር መፍራት ለአውሮፓውያን አዲስ ክስተት ባይሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመረ ለመጣው የጂሃድ ሽብር ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ያለጥርጥር የሚታመነው በምዕራቡ ዓለም ያለው እስልምናን ባልተቀበሉት ላይ የተጣለው የጭቆና አካሄድ ነው፡፡  

ኃይማኖታዊ ስደትና የዲህማ መመለስ

19ኛውና 20ኛው ምዕተ ዓመታት የተለያዩ የአውሮፓ ኃይላት የሙስሊሙን ዓለም ዝቅ ለማድረግና ጨቁኖ የመግዛት ስርአታቸውንም ለማጥፋት ያላሰለሰ ጥረት አድርገዋል፡፡ ቢሆንም ተፅዕኖ ማድረግ፣ ዝቅ አድርጎ ማየትና የኃይማኖት አድሎ ማድረግ ሙስሊሞች በሚበዙበት አገራት እየጨመረ መቷል፡፡

በፓኪስታን፣ በኢራቅ፣ እንደዚሁም በግብፅ በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለውን  አደጋ  አይተው እንዳላዩ ሆነው ማለፋቸው ይሄ የጭቆና አካሄድ  ከእለት ወደ እለት እያደገ እንዲመጣና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ እንዲያሳድር ምክንያት ሆኗል፡፡