5. ኢየሱስ የህማም ሰው

ምዕራፍ 5

ኢየሱስ የህማም ሰው

የህማም ሰው

የኢየሱስ ህይወት ከመሐመድ የሚያንስ አይደለም፡፡ በመገፋትና ተቀባይነትን በማጣት የተሞላ ነው፡፡ የተደመደመው ደግሞ በመስቀል ነው፡፡ መሐመድ ለደረሰበት ስደት የሰጠው ምላሽ ቢኖር ተገቢ የሆነን ቅጣት በጠላቶቹ ላይ መፈጸም ነበር፡፡ የክርስቶስ ምላሽ ደግሞ ከዚህ ፍጹም የተለየ ነው፡፡

ልክ እንደ መሐመድ የኢየሱስ የቤተሰብ ሁኔታ ስንመለከተ በአመለካከት የተራራቁ ነበሩ፡፡ በወላጆቹ ህጋዊ ጋብቻ ባለመወለዱም ከህብረተሰቡ እንዲገለልም ተደርጎ ነበር (ማቴ 118-25)፡፡ የተወለደው ውርደት በሚመስል ሁኔታ ውስጥ ነው (ሉቃ 27)፡፡ ከውልደቱ በኋላ ሄሮድስ ሊገድለው ፈልጎ ነበር፡፡ ከዚህም የተነሳ መሸሸጊያ ፍለጋ ወደ ግብፅ ሸሸ (ማቴ 213-18)፡፡

ኢየሱስ ጥያቄ ቀረበበት

ኢየሱስ 30 ዓመቱ አካባቢ የማስተማር አገልግሎቱን በጀመረ ጊዜ፤ ትልቅ የሆነ ተቃውሞ በህይወቱ አጋጥሞት ነበር፡፡ መሐመድ እንደተጠየቀው ሁሉ የአይሁዳውያን የኃይማኖት መሪዎች ያለውን ስልጣን ዝቅ ለማድረግና በጥያቄ ለመሞገት-ጥረት-አድርገው-ነበር፡፡  

“...ኢየሱስ ከዚህ ከወጣ በኋላ፣ ጸሐፊትና ፈሪሳውያን ክፉኛ ይቃወሙትና በጥያቄም ያዋክቡት ጀመር ከአፉ በሚወጣውም ቃል ሊያጠምዱት ያደቡ ነበር፡፡ ሉቃ 1153-54

ጥያቄዎቹም በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ ነበሩ

§  ኢየሱስ ለምንድን ነው በሰንበት የሚፈውሰው? ይሄ ጥያቄ የተጠየቀው የሰንበትን ህግ ሽሯል የሚለውን ለማሳየት ነው፡፡ (ማር 32 ማቴ 1210)

§  በምን ስልጣን ነው ነገሮችን የሚያደርገው? (ማር 1128 ማቴ 2123 ሉቃ 202)

§  ለሰው ሚስቱን መፍታት ህጋዊነት ነውን? ( ማር 102 ማቴ 193)

§  ለቄሳር ግብርን መክፈል ተገቢ ነውን? ( ማር 12:15 ማቴ 2217 ሉቃ 2022)

§  ታላቂቱ ትእዛዝ የትኛዋ ነችን? (ማቴ 2236)

§  መሲሁ የማን ልጅ ነው? (ማቴ2242)

§  ስለ ኢየሱስ አባትነት (ዮሐ 819)

§  ስለ ትንሳኤ ሙታን (ማቴ 22 23-28፣ሉቃ 20 27-33)

§  ምልክትን ስለማድረግ መጠየቅ (ማር 811 ማቴ 1238 161)

ከነዚህም በተጨማሪ ኢየሱስ ክስ ቀርቦበት ነበር

§  በአጋንንት ተይዟል፡፡በአጋንንት ኃይል አጋንንንትን ያስወጣል፡፡ (ማር 322 ማቴ 1224፣ዮሐ 852 ዮሐ 1020)

§  ሰንበትን የማይጠብቁ ደቀመዛሙርት አሉት (ማቴ 122) ወይንም የማንጻት ስርአት (ማር 72 ማቴ 15 1-2 ሉቃ 1138) እና

§  ተቀባይነት የሌለው ምስክርነት መስጠት (ዮሐ 813)

 

አውጋዦቹ

የኢየሱስን ህይወትና አስተምህሮ በምንመለከትበት ጊዜ ከብዙ ግለሰቦችና ቡድኖች ውግዘት ደርሶበተ ነበር፡፡

§  ንጉስ ሄሮድስ ገና ህፃን ሳለ ሊገድለው ሙከራ አድርጎ ነበር፡፡ (ማቴ216)

§  በናዝሬት የሚኖሩ የራሱ ሰዎች ስሜቱን ጎድተውታል፡፡ (ማር 63 ማቴ 13 5358) ከገደል ላይ ጥለውት ሊገድሉት ጥረት አድርገዋል፡፡ (ሉቃ 4 28-30)

§  የገዛ ቤተሰቡ አባላት አዕምሮውን አጥቷል በማለት ከሰውታል፡፡ (ማር 321)

§  ብዙ ተከታዮቹ በምድረበዳ ጥለውት ሄደዋል፡፡ (ዮሐ 660)

§  ሕዝቡ በድንጋይ ሊወግሩት ሞክረዋል፡፡ (ዮሐ 1031).

§  የኃይማኖት መሪዎች ሊገድሉት ተማክረዋል፡፡(ዮሐ 1150)

§  በውስጥ ካሉት መካከል በይሁዳ ተከድቷል፡፡ (ማር 1443 ማቴ 26 14-16 ሉቃ 22 1-6

 ዮሐ 182-3)

§   አዕማድ ደቀመዝሙሩ በነበረው ጴጥሮስ ሦስት ጊዜ ተከድቷል፡፡ (ማር 14 66-72 ማቴ 26 69-75 ሉቃ 2254-62 ዮሐ 18)

§  በመስቀል ላይ እንዲሞት የተደረገው ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበባት በኢየሩሳሌም ነበር፡፡ ይሄ የሆነው ደግሞ ከጥቂት ቀናት በፊት እንደ መሲህ በደስታ በተቀበሉበት ከተማ ውስጥ ነበር፡፡ (ማር 1512-15 ሉቃ 23 18-23 ዮሐ 1915).

§  በጥፊ ተመትቷል፣ ተፍተውበታል፣ የኃይማኖት መሪዎችም ተሳልቀውበታል፡፡ (ማር 1465 ማቴ 26 67-68)

§  በሮማውያን ወታደሮች ጸያፍ ስድብና መሳለቅ ደርሶበታል፡፡ (ማር 1516-20 ማቴ 2727-31 ሉቃ 2263-65 ሉቃ2311)

§  በአይሁዳውያንና በሮማውያን ልዩ ፍርድ ቤቶች የሀሰት ክስ ቀርቦበታል፡፡ የሞት ፍርድም ተፈርዶበታል፡፡( ማር 1453-65 ማቴ 26 57-67 ዮሐ 18 28)

§  ሮማውያን ከፍተኛ ወንጀል የሰሩ ሰዎችን በሚገድሉበት የመስቀል ሞት እንዲሞት ተደርጓል፡፡ ይሄ ደግሞ እንደ እርግማን መቆጠሩ አይሁዶች ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉት አድርጓል፡፡ (ዘዳ 2133)

§  በሁለት ወንጀለኞች መካከል ተሰቀለ፡፡ የደረሰበትን ስቃይ በመስቀል ላይ ታግሶ ሳለ አብዝቶ ተነቀፈ፡፡(ማር 15 21-32፣ማቴ 2732-44 ሉቃ 2332-36 የዮሐ 19 23-30)

ተቀባይነትን ስላጣበት ሁኔታ የኢየሱስ ምላሽ

እነዚህን ሁሉ ውግዘቶች በምንመለከትበት ጊዜ ኢየሱስ ሲቆጣና በአመጽ ሲመልስ አናይም፡፡ መበቀልንም አልፈለገም፡፡ አንዳንድ ጊዜም ከመሰቀሉ በፊት በእርሱ ላይ ለሚቀርቡ ክሶች መልስ ከመስጠት ተቆጥቦ ነበር፡፡ (ማቴ 2714) ይሄንን ሐሳብ ቤተክርስቲያን ስለ መሲሁ የተነገረ ትንቢት ፍፃሜ እንደሆነ ታስተምራለች፡፡

ተጨነቀ ተሰቃየም፣ ነገር ግን አፉን አልከፈተም፣ እንደ ጠቦትም ለዕርድ ተነዳ በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም፤ (ኢሳ 537)

አንዳንድ ጊዜ ኢየሱስ ማን እንደሆነ ስለራሱ እንዲናገር በተጠየቀ ጊዜ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ዝምታን ይመርጥ ነበር፡፡ ይልቁንም መልሶ ጥያቄ የሚጠይቃቸው ጊዜ ነበር (ማቴ 2124 2215)፡፡  የቱንም ያህል ሰዎች ከእርሱ ጋር ጦርነትን መግጠም ቢፈልጉም አይጨቃጨቅም ነበር፡፡

በእርሱም ደስ የሚለኝ ምርጤ ይህ ነው፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ድምፁን በመንገድ ላይ በኀይል አያሰማም የተቀጠቀጠ ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስም የጥዋፍ ክር አያጠፋም፤ ፍትህን በታማኝነት ያመጣል ፍትህን በምድር እስኪያመጣ ድረስ፤ አይደክምም፤ ተስፋም አይቆርጥም፤ ደሴቶች በህጉ ይታመናሉ፡፡(ማቴ 1219-20 ከኢሳ 421-4 የተወሰደ)

ሰዎች ኢየሱስን በድንጋይ መውገር ወይም መግደል በፈለጉ ጊዜ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ዞር ይል ነበር፡፡ (ሉቃ 430) ወደ መስቀል ሞት ሲሄድ ግን በዓላማና አስቦበት ነበር፡፡

እነዚህ ምላሽ የሚያሻቸው ነጥቦች ኢየሱስን በውግዘት ልምምድ ውስጥ እንዲያልፍ ፈተና ሆነውበት ነበር፡፡ ፈተናውንም አሸነፈ፡፡ ለተደረገበትም ውግዘት አልተሸነፈም፡፡ የዕብራውያኑ ጸሐፊ ምላሹን እንዲህ አድርጎ አስቀምጦታል፡

በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንምና፤ ነገር ግን እንደ እኛ በማንኛውም ነገር የተፈተነ ሊቀ ካህናት አለን ይሁን እንጂ ምንም ኀጢአት አልሰራም፡፡ እንግዲህ ምህረትን እንድንቀበልና እንድናገኝ፣ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቀርብ (ዕብ 415-16)

በወንጌላት ላይ ስለ ኢየሱስ ተገልፆ የምናየው ሐሳብ የሚያመለክተው በታላቅ ጥበቃና እረፍት ውስጥ ያለ፤ በእርሱ ላይ የተነሱትን የማጥፋት ፍላጎት  እንዳልነበረው ያሳያል፡፡  ኢየሱስ ለነበረበት ውግዝና ምላሽ አለመስጠት ብቻ ሳይሆን  ደቀመዛሙርቱም በሚወገዙበት ጊዜ ሊኖራቸው ስለሚገባ ምላሽ ስነመለኮታዊ ማዕቀፍ አሳይቷቸዋል፡፡  ቁልፍ የሆኑት ስነመለኮታዊ ጉዳዮች ከዚህ በታች ተገልጸዋል፡፡

የኢየሱስ የውግዘት ስነ መለኮት

ውግዘትን መቀበል

ኢየሱስ እንደ እግዚአብሔር መሲህ ውግዘት እንዲደርስበት መሆኑ አግባብ ያለው ነገር መሆኑን ግልፅ አድርጎ ተናግሯል፡፡ የእግዚአብሔር ሐሳብ የተወገዙትን እንደ ቁልፍ ድንጋይ አድርጎ ህንጸው እንዲገነባና ጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡

ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ (ማር 1211 ከመዝ 118 22-23 የተወሰደ) በማቴ 21 42 ላይም ይገኛል፡፡

ኢየሱስ እንደ ተወገዘ፣ እንደ ተሰቃየ ባርያ መሆኑን ኢሳይያስ ትንቢታዊ መልዕክት ተናግሯል፡፡ በእርሱ ስቃይ አህዛብ ሁሉ ሰላምና የኃጢአት ስርየትን ያገኛሉ፡፡

በሰዎች  የተናቀና የተጠላ፣ የህማም ሰውና ስቃይ

ያልተለየው ነበር፡፡ ሰዎች ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት ዐይነት፣ የተናቀ ነበር፣ እኛም አላከበርነውም፡፡ በእርግጥ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕመማችንንም ተሸከመ እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደተመታ እንደተቀሰፈ፣ እንደተሰቃየም ቆጠርነው፣ ነገር ግን ስለ መተላለፋችን ተወጋ ስለበደላችንም ደቀቀ፤ በእርሱ ላይ የወደቀ ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፣ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን (ኢሳ 533-5)

የዚህ ዕቅድ ማእከላዊ ሀሳቡ መስቀል ነው፡፡ ኢየሱስ በተደጋጋሚ ወደ ሞት እንደሚሄድ የሚያመላክት ነው፡፡

ከዚያም የሰው ልጅ ብዙ መከራ እንደሚቀበል፣ በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት እንደሚናቅ፣ እንደሚገደል፣ ከሦስት ቀንም በኋላ እንደሚነሳ ያስተምራቸው ጀመር፡፡ እነርሱም ይህን በግልጽ ነገራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን ለብቻው ወስዶ ይገስጸው ጀመር፡፡ (ማር 831-32 እንደዚሁም ማር 1032-34 ማቴ 1621 2017-19 262 ሉቃ 1831 ዮሐ 1223)

አመጽን አለመቀበል

ኢየሱስ ግቡን ከማሳካት አንጻር በግልጽና በተደጋጋሚ ኃይል መጠቀምን አውግዟል፡፡ በመስቀል ላይ ሆኖ እንኳን በዚህ አቋሙ ጸንቶ ነበር፡፡ ኢየሱስም እንዲህ አለውሰይፍን የሚመዝዙ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ፡፡ ማቴ 26-52 ኢየሱስ ወደ መስቀል እየሄደ ሳለ ኃይልን መጠቀምን በፈቃዱ ተወ ይሄንንም ያደረገው የመጣበትን ተልዕኮ ለመወጣት ነው፡፡ ይሄውም የሞትን ዋጋ እስከመክፈል ድረስ ነው፡፡

 

ኢየሱስም፣ የእኔ መንግስት ከዚህ ዓለም አይደለም፤ ቢሆንም ኖሮ አይሁድ እንዳይዙኝ ሎሌዎቼ በተከላከሉልኝ ነበር፣ አሁን ግን መንግስቴ ከዚህ አይደለም አለው፡፡ ዮሃ 18-36

ሰይፍየሚመጣበት ጊዜ እንዳለ አመላካች ነገር በወንጌል ላይ ተጠቅሶ እናያለን፡፡ ይሄንንም የምናገኘው ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ወደፊት ሊያገኛት የሚችለውን  መከራ ለማሳየት ነው፡፡

እኔ የመጣሁት ሰላምን በምድር ለማስፈን አይምሰላችሁ፡ ሰይፍን እንጂማቴ 10-34

የቱንም ያህል ይሄኛው ጥቅስ ኢየሱስ አመጽን እንደሚፈቅድ ተደርጎ እንደማስረጃ ሲቀርብ ብናይም እውነታው ግን ክርስቲያኖች በክርስቶስ ባላቸው እምነት የተነሳ ቤተሰቦቻቸው በሚያገሏቸው ጊዜ ሊፈጠር የሚችለውን መከፋፈል ለማሳየት ነው፡፡

በሉቃስ ወንጌል ላይ ተመሳሳይ የሆነው ምንባብ ሰይፍ በሚለው ቃል ምትክ መከፋፈል የሚል ቃል ተጠቅሶ እናገኛለን ሉቃስ 12-51፡፡ ስለሆነም በዚህ ክፍል ላይ ሰይፍ የሚለው ቃል እንደምሳሌ ሆኖ የሚያመለክተው  መከፋፈልን፣ የአንድ ቤተሰብ አባላት ከሌሎች የቤተሰብ አባላት መለያየትን  ነው፡፡ ሊሆን ይችላል ተብሎ የሚታሰበው ሌላኛው አተረጓጎም ደግሞሰይፍየሚለው የክርስቲያኖችን ስደት ይወክላል የሚል ነው፡፡ ማለትም ሰይፉ የሚነሳው በክርስቲያኖች ላይ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ምስክርነታቸው ነው፡፡

የኢየሱስ የኃይል አካሄድን አለመቀበሉ መሲሁ ሲመጣ ያደርገዋል ተብሎ ከሚጠበቀው አስተሳሰብ የተቃረነ ነበር፡፡ ይሄውም ህዝቡን ይታደጋቸዋል የሚለው ነው፡፡ የሚታደጋቸው ደግሞ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ አንደዚሁም መንፈሳዊ ከሆነ ሁኔታ ነው ተብሎ ይታመን ነበር፡፡  ኢየሱስ ደግሞ ወታደራዊ የሆነውን አካሄድ ተቃውሞታል፡፡ መንግስቱ ፖለቲካዊ፣ የዚህ ዓለምም አለመሆኗንም ግልጽ አድርጎላቸዋል፡፡ 

ሰዎች የቄሳር የሆነውን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር የግድ መስጠት እንዳለባቸውም አስተምሯቸዋል፡፡ (ማቴ 22-21) የእግዚአብሔር መንግስት በአንድ ስፍራ ተወስናለች የሚለውን አተያይ አስተባብሏል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የምትገኘው በሰዎች መካከል ሰለሆነ ነው(ሉቃ 1721)፡፡ በእግዚአብሔር መንግስት የተሻለውን ቦታ የሚይዘው ማነው? የሚል ጥያቄ ይዘው ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን የሞገቱበት ምክንያት የእግዚአብሔር መንግስት እነርሱ በሚቀመጡበት ስፍራ የምትገኝ ነች ብለው አምነው ስለነበር ነው፡፡ ኢየሱስ ድግሞ የእግዚአብሔር መንግስት እነርሱ እንደተለማመዱት እንደ ፖለቲካ መንግስት ሰዎች ሰዎችን ጌታ ሆነው የሚገዙባት አለመሆኗን አሳይቷቸዋል፡፡ ፊተኛ ለመሆን ኋለኛ መሆን እንደሚኖር አስተምሯል፡፡ (ማቴ 20- 1627) የኢየሱስ ተከታዮች መገልገልን ሳይሆን ማገልገልን መፈለግ አለባቸው፡፡ (ማር 10- 43 ማቴ 10-27)

የጥንቷ ቤተክርስቲያን የኢየሱስን አስተምህሮ ከልቧ ተቀብላው ነበር፡፡ እንደ ምሳሌ ያህል በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ከተከለከሉ የስራ ዘርፎች መካከል አንዱ ውትድርና ነበር፡፡ ክርስቲያን ወታደር የሚሆን ከሆን ከመግደል ይታቀብ ነበር፡፡

ጠላትህን ውደድ

ሌላውን አለመቀበልና ማውገዝ ጠብ ያለበት ምላሽ ከሌላኛው ወገን እንዲነሳ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ኢየሱስ መቼም ቢሆን ክፉ ያደረጉብንን ሰዎች መቅጣት ተቀባይነት አለው አላለም፡፡ ይልቁንም ክፉ ለሚያደርጉባችሁ በክፉ ፈንታ መልካም አድርጉ ብሏል፡፡ (ማቴ 5- 38-42) በሌላው ላይ መፍረድ ስህተት ነው፡፡ (ማቴ 7- 1-5) ጠላታችንን መጥላት ሳይሆን መውደድ አለብን፡፡ (ማቴ 5-43) የዋሆች ምድርን ይወርሳሉ፡፡ (ማቴ 5-5) የሚያስተራርቁ ብጹአን ናቸው የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና፡፡ (ማቴ 5- 9)

እነዚህ አስተምህሮቶች ደቀመዛሙርት ሰምተው እንዲረሱአቸው የሚገቡ ተራ ቃላት አልነበሩም፡፡ የኢየሱስ ደቀመዛሙርት መልዕክቶቻቸው በአዲስ ኪዳን ተመዝግቦ የተቀመጠ ሲሆን በታላቅ መከራና ተቃውሞም ጊዜ  ጭምር በእነዚህ መርሆዎች ተመርተዋል፡፡

እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፣ እንጠማለን፣ እንራቆታለን፣ እንጎሰማለን፣ እንከራተታለን፣ በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲሰድቡን እንመርቃለን፣ ሲያሳድዱን እንታገሳለን፣ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን እስከ አሁን ድረስ የዓለም ጥራጊ የሁሉም ጉድፍ ሆነናል፡፡ (1ቆሮ 4-11-13 1ጴጥ 3-10 ቲቶ 3-1-2 ሮሜ 12- 14-21)

ሐዋርያት በአማኞች ፊት የኢየሱስን ምሳሌ ይዘው ተመላልሰዋል፡፡ (1ጴጥ 2-21-25) ጠላትህን ውደድ የሚለው በማቴ 5 የተጠቀሰው ክፍል የጥንቷ ቤተክርስቲያን በተደጋጋሚ ከመጽሐፍ ቅዱስ በመውሰድ በጽሑፎቻቸው ይጠቀሙባቸው ነበር፡፡

ስደትን ለመቀበል የተዘጋጀህ ሁን

ኢየሱስ ለተከታዮቹ ያስተማረው ስደት የማይቀር መሆኑን ነው፡፡ መመታት፣ መጠላት፣ መሰደድና ለሞት ታልፎ መሰጠት እንደሚያጋጥማቸው ነግሯቸዋል፡፡ (ማር 13 9-13 ሉክ 2112-19 ማቴ 10 17-23)

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን በሚያሰለጥናቸው ጊዜ የተቀበሉትን መልዕክት ለሌሎች እንዴት ማድረስ እንዳለባቸው መመርያ ሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህም ደግሞ የመገፋትን ህይወት ይለማመዳሉ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የመሐመድን  አስተምህሮቶች በምንመለከትበት ጊዜ ሙስሊሞች ለሚደርስባቸው ማንኛውም ስቃይ የኃይል ጥቃት ሰውን በማረድም ጭምር ምላሽ እንዲሰጡ ያበረታታቸዋል፡፡

ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ያስተማራቸው በቀላሉየእግራችሁን ትቢያ አራግፋችሁ ሂዱየሚል ነው፡፡ በሌላ አነጋገር  ለተቃዋሚዎቻቸው አንዳችም ክፉ ምላሽ ሳይሰጡ እንዲሄዱ ነበር ያስተማራቸው፡፡ (ማር 611 ማቴ 1014) “ወደ ቤትም ስትገቡ ሰላምታ ስጡ ቤቱም የሚገባው ቢሆን ሰላማችሁ ይድረስለት፤ ባይገባው ግን ሰላማችሁ ይመለስላችሁ፡፡

ይሄንን አስተምህሮ ደግሞ ኢየሱስ ምሳሌ በመሆን አሳይቷል፡፡ ወደ ሳምራውያን መንደር በመጣ ጊዜ ሊቀበሉት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ በዚህ ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ከሰማይ እሳት አውርዶ እንድትበላቸው እንዲያደርግ ጠየቁት፡፡ ኢየሱስ ግን ገሰፃቸውና እልፍ ብሎ ሄደ፡፡ (ሉቃ 954-56)

ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ያስተማራቸው ነገር ቢኖር ስደት ሲያጋጥማቸው ወደሌላ ከተማ እንዲሸሹ የሚያስገነዝብ ነበር፡፡ (ማቴ 1023) በሚሰደዱ ጊዜ ምን መናገር እንዳለባቸው መንፈስ ቅዱስ ስለሚያሳያቸው አንዳች መጨነቅ የለባቸውም፡፡ (ማር 10 19-20 ሉቃ 1211-12 2114-15) እንዲፈሩም አይገባም፡፡ (ማር 1031 ማቴ 1026)

ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው ለየት ያለ አስተምህሮ ቢኖር ተከታዮቹ በሚሰደዱበት ጊዜ የግድ መደሰት እንዳለባቸው ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከነብያቶቹ ጋር እነርሱም የታወቁ ስለሆኑ ነው፡፡

ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ ብፁዓን ናችሁ፡፡ እነሆ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና” (ሉቃ 622-23 ማቴ 511-12)

ይሄ መልዕክት የጥንቷ ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ ከነበራት መሰጠት የተነሳ ሙሉ በሙሉ በፍርሃት ውስጥ ስለማለፏ  በርካታ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡

ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳን መከራን ብትቀበሉ ብጹአን ናችሁ” (1ጴጥ 314 1ቆሮ 15 ፊሊ 2 17-18 1ጴጥ 4 12-14)፡፡

ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ከስደት ባሻገር የዘላለምን ህይወት ወደፊት እንደሚቀበሉ ተስፋ ሰጥቷቸዋል፡፡የተሻለው ነገር ወደ ፊት የሚሆን ነው የተስፋ ቃል ለመውረስ ደግሞ በህይወት ታማኝ ሆኖ መቀጠል ይገባል (ማር 1029-30 ማር 1313)፡፡