7. ዲህማን እንዴት መካድ ይቻላል?

ምዕራፍ 7

ዲህማን እንዴት መካድ ይቻላል?

በዚህ ምዕራፍ  ከዲህማ የጭቆና አገዛዝ ነፃ ስለሚወጣበት መንገድ ስለሚናገረው የክርስቲያኖች ጸሎት ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡

የመሐመድን ሕይወት በጥልቀት በምንመለከትበት ጊዜ ሌሎችን በመጉዳት ልምምድ ውስጥ ያለፈ ነው፡፡ በሚያቆስል፣ ሌሎች ላይ የኃይል ጥቃት በመፈጸም፣ የአዕምሮ ጉዳት ሰለባ በሚያደርግ መንፈስ በመመራት ሌሎችን በኃይል መቆጣጠር ችሏል፡፡ በሌሎች ላይ ጂሃድ በማወጅም ጭምር በጭቆና ውስጥ እንዲገቡና ዝቅተኛ ሆነው እንዲታዩ አድርጓል፡፡

በተቃራኒው ደግሞ ክርስቶስ በሰዎች የተወገዘ ሲሆን ጥቃትን ለመፈጸም ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ሌሎችንም የበታች አድርጎ አላየም፡፡ ሰዎችን የሚያቆስለውን መንፈስ ተቃውሟል፡፡ መስቀሉና ትንሳኤው ተቀባይነት ማጣትንና የጨለማ ኃይላትን አሸንፏል፡፡

ጸሎት ለምን አስፈለገ?

እነዚህን ጸሎቶች ለተለያዩ ምክንያቶች የመጸለይ ፍላጎት ሊኖርህ ይችላል፡፡

§  አንተ ወይንም ዘሮችህ በእስልምና አስተዳደር ስር ሙስሊም እንዳልሆኑ ሰዎች በመኖር የዲህሚን ውል ተቀብላችሁት ሊሆን ይችላል ወይንም ደግሞ የጂሃድ እና የዲህሚ መርሆች ተፅዕኖ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ኖራችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ያህል የጂሃድ እና የአሸባሪዎችን ጥቃት ትፈራ ይሆናል፡፡

§  ያንተና የቤተሰቦችህ ታሪክ ሽብርን በመሳሰሉ ከጂሃድ ጋር በተያያዙ በዲህማ ስር በሚከሰቱ ጥቃቶች ተፅዕኖ የደረሰበት ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲህ ዓይነት ክስተቶች ስለመከሰታቸው ሰምተህ አታውቅ ይሆናል ነገር ግን የቤተሰብህ ታሪክ አካል ስለመሆኑ ጥርጣሬ ሊኖርህ ይችላል፡፡

§  አንተ ወይንም ዘሮችህ በእስላማዊ ጂሃድ ማስፈራርያ ደርሶባችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባትም ደግሞ በእስልምና ስር የኖርክበት አጋጣሚ ባይኖርም ነገር ግን ከፍርሃት እና ከስጋት ነፃ መሆን ትፈልግ ይሆናል፡፡

§  አንተ ወይንም ዘሮችህ እንደ ሙስሊሞች ኖራችሁ ሊሆን ይችላል ስለዚህ የዲህማ ውል እና ተያያዥ የሆኑ ነገሮች አካል መሆንህንም መካድ ትፈልግ ይሆናል፡፡

እነዚህ ጸሎቶች በህይወትህ ላይ ዳግመኛ ተፅዕኖ እንዳይኖረው የዲህማን ውል ከነትርጉሞቹ ለመሰረዝ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ በእስልምና ግዛት ውስጥ እንደ ዲህሚ በመኖራችሁ ምክንያት ባንተና በዘሮችህ ላይ የተደረጉትን እርግማኖች ሁሉ ለመስበር የተዘጋጁ ናቸው፡፡

ባለፉት ዘመናት ዕውቀት በማጣትህ ምክንያት እየተጸጸትክ እና ከንግዲህ በኋላ እንደ እግዚአብሔር ቃል ለመኖር እየወሰንክ ይህንን ጸሎት ልትጸልይ ትችላለህ፡፡ እነዚህ ጸሎቶች የሚከተሉትን የመሳሰሉ የዲህሚ አሉታዊ መንፈሳዊ ተፅዕኖዎችን ለመቀልበስ የተዘጋጁ ናቸው፡

§  ውስጣዊ ጉዳት

§  ፍርሃት

§  እፍረት

§  ማስፈራራት

§  የህሊና ክስ

§  የበታችነት ስሜት

§  ራስን መጥላት እና ራስን አለመቀበል

§  ሌሎችን መጥላት

§  ድብርት

§  ማታለል

§  ውርደት

§  መገለል እና ብቸኝነት

§  ዝምታ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ለነዚህ ጸሎቶች ራስን ለማዘጋጀት የመጀመርያው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማንበብ ነው፡፡ ይህም ለዚህ ጸሎት መሰረት የሆኑትን እውነቶች ለማረጋገጥ ነው፡፡ እነዚህን ጸሎቶች መጸለይህን መመስከር ከሚችል አንድ ሰው ጋር ብትጸልይ ይመከራል፡፡

የእግዚአብሔር ፍቅር መገለልን ያሸንፋል

እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።” (1ዮሃ 416)

“[ኢየሱስም አለ] በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሃ 316)

እድል ፈንታችን ፍርሃት አይደለም፤ በእግዚአብሔር ነው

እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።” (2ጢሞ 17)

አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።” (ሮሜ 815-16)

በነፃነት እንድንኖር ተጠርተናል

“[ኢየሱስም አለ] እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል።” (ዮሃ 832)

በነፃነት ልንኖር ክርስቶስ ነፃነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።” (ገላ 51)

ሰውነታችን የእግዚአብሔር እንጂ የጭቆና አይደለም፡ የደማችን ዋጋ ተከፍሏል

ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።” (1ቆሮ 619-20)

እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት...” (ራዕ 1211)

ወንዶችና ሴቶች በእግዚአብሔር ፊት እኩል ናቸው፣ አንዱ ቡድን በሌላው ላይ የበላይ አይደለም

አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።” (ገላ 328)

ልዩ መለያችን ውርደት እና የበታችነት አይደለም ነገር ግን የክርስቶስ ድል፣ በክርስቶስ ያለው የአንድነት ፍቅር እና የክርስቶስ መስቀል ናቸው

ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን” (2ቆሮ 214)

በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል።” (ዮሃ 1723)

ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።” (ሉቃ 923)

እውነትን የሚገልጥልን የመንፈስ ቅዱስ ኃይል አለን

እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።” (ዮሃ 167-8)

ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ ዓይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።

እፍረትን ለማሸነፍ በክርስቶስ ስልጣን ተሰቶናል

የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።” (ዕብ 122)

ራሳችንንና ልጆቻችንን መንፈሳዊ ነገሮችን የማስተማር መብት አለን፤ ኃላፊነትም አለብን

እግዚአብሔር፦ ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ፥ በምድርም በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩ ዘንድ፥ ልጆቻቸውንም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን አሰማቸዋለሁ ብሎ በተናገረኝ ጊዜ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት በኮሬብ በቆምህበት ቀን ዓይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይወድቅ ተጠንቀቅ፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አስታውቀው።” (ዘጸ 49)

እውነትን በፍቅር በድፍረት ለመናገር በክርስቶስ ስልጣን አለን

ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ።” (ምሳ 1821)

አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ወደ ዛቻቸው ተመልከት፤ ለመፈወስም እጅህን ስትዘረጋ በቅዱስ ብላቴናህም በኢየሱስ ስም ምልክትና ድንቅ ሲደረግ፥ ባሪያዎችህ በፍጹም ግልጥነት ቃልህን እንዲናገሩ ስጣቸው።” (ሐዋ 429)

ፍቅር ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም” (1ቆሮ 136)

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።” (1ዮሃ 415)

እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ።” (ዕብ 1035)

በእውነት ቃል መተማመን አለን

የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና።” (1ዮሃ 59)

እነርሱም...ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት” (ራዕ 1211)

እኛ መከላከያ የሌለን ወይንም መሳርያ የሌለን አይደለንም ነገር ግን በመንፈስ የታጠቅን ነን

በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።” (ኤፌ 610)

በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም ዕውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥ መታዘዛችሁም በተፈጸመች ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉ ልንበቀል ተዘጋጅተናል።” (2ቆሮ 103-4)

 

በክርስቶስ ስም መከራ መቀበልን እንደ ደስታ ልንቆጥር ይገባናል

ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት” (ያዕ 12)

መስቀሉ የዲህማን ውል ያፈርሳል ኃይሉንም ይደመስሳል

እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ። በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ። በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል። አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው።” (ቆላ 213)

ስትጸልይ ሳለ ያንተ ጸሎት እና እወጃ ኃይል ያላቸውና ውጤታማ እንደሆኑ ተረዳ፡፡ እግዚአብሔር አንተን ወደ ሙሉ አርነት ሊያመጣህ ፍቃዱ ስለሆነ ከርሱ ጋር ተስማማ፡፡ ክርስቶስ እንደተቀበለህ እና ከየትኛውም የክፉ ወጥመድ ሊያላቅቅህ እንደሚፈልግ በመንፈስህ ውስጥ ተቀበል፡፡ የዲህማ ውል ሙስሊም ባልሆኑ ሰዎች ላይ የጫነውን ውሸት ለመጣል ወስን፡፡

 

 

ጸሎቶች እና እወጃዎች

የኑዛዜ ጸሎት

አፍቃሪ እግዚአብሔር ሆይ ኃጢአትን በመስራት ካንተ ዘወር ማለቴን እናዘዛለሁ፡፡ ሌሎች ሰዎችን ያስፈራራሁበትን እና በሰዎች ላይ የበታችነትን እንዲሁም ውርደትን የጫንኩበትን በደሌን ይቅር በለኝ፡፡ ስለ ትዕቢቴ ይቅር በለኝ፡፡ ሌሎችን የጎዳሁበትን እና የጨቆንኩበትን በደሌን ይቅር በለኝ፡፡ እነዚህን ሁሉ ነገሮች በኢየሱስ ስም ክጄያቸዋለሁ፡፡

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ሆይ በከርስቶስ በመስቀል ላይ ስለተገኘው የይቅርታ ስጦታ አመሰግንሃለሁ፡፡ አንተ እንደተቀበልከኝ ዕውቅና እሰጣለሁ፡፡ በመስቀል በኩል ካንተ ጋር እና ከሌሎች ጋር መታረቅ ስለሆነልን አመሰግንሃለሁ፡፡ ልጅህ መሆኔን እና የእግዚአብሔር መንግስት ወራሽ መሆኔን  ዛሬ አውጃለሁ፡፡

እወጃዎችና ክህደቶች

አባት ሆይ የፍርሃት ተገዢ አለመሆኔን ነገር ግን የፍቅርህ ልጅ መሆኔን ካንተ ጋር እስማማለሁ፡፡ መሐመድ ያስተማረውን የእስልምና ፍላጎቶች ሁሉ እቃወማለሁ እክዳለሁ፡፡ በማንኛውም መንገድ ለቁርአኑ አላህ የሚሆነውን መገዛትን እክዳለሁ፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ የሆነውን እርሱን ብቻ እንደማመልክ አውጃለሁ፡፡

ለዲህማ ውል እና መርሆች ለመገዛት በመስማማት አባቶቻችን ለሰሩት ኃጢአት ንስሃ እንገባለን የኃጢአታቸውንም ይቅርታ እንጠይቅሃለን፡፡

ለእስልምና ማህበረሰብ እና መርሆች ለመገዛት በኔም ሆነ በዘሮቼ የተደረጉትን ውሎች ሁሉ እክዳለሁ፡፡

ዲህማንና አኳሆኖቹን ሁሉ ሙሉ በሙሉ እቃወማለሁ፡፡ በጂዝያ ክፍያ ጊዜ አንገት ላይ የሚደረገውን ምልክት ከነትርጉሙ እክዳለሁ፡፡ በተለይ በዚህ ስርአት የተመሰለውን የእርድ እና የሞት እርግማን እክዳለሁ፡፡

የዲህማ ውል በክርስቶስ መስቀል ላይ መቸንከሩን አውጃለሁ፡፡ ዲህማ በአደባባይ ስለተዋረደ በኔ ላይ ስልጣን የለውም፡፡ የዲህማ ውል መንፈሳዊ መርሆች በክርስቶስ መስቀል መጋለጡን፣ እርቃኑን መቅረቱን እና መዋረዱን አውጃለሁ፡፡

ለእስልምና ያለኝን የውሸት ክብር ስሜት እክዳለሁ፡፡

የውሸት የህሊና ክስን እክዳለሁ፡፡

በክርስቶስ ያለኝን እምነት ላለመናገር የገባሁትን ውል ሁሉ እክዳለሁ፡፡

ስለ ዲህማ ወይንም ኢስላም ላለመናገር የገባሁትን ውል ሁሉ እክዳለሁ፡፡

እናገራለሁ ዝምም አልልም፡፡

እውነት አርነት እንደሚያወጣኝ አውጃለሁ (ዮሃ 832) በክርስቶስ ኢየሱስ ነፃ እንደወጣ ሰው መኖር ምርጫዬ ነው፡፡

በኢስላም ስም በኔና በቤተሰቦቼ ላይ የተነገሩትን እርግማኖች ሁሉ እክዳለሁ አመክናለሁ፡፡ በዘሮቼ ላይ የተነገሩትን እርግማኖች ሁሉ እክዳለሁ አመክናለሁ፡፡

በተለይ የሞትን እርግማን እሰብራለሁ፡፡ ሞት ሆይ በኔ ላይ ስልጣን የለህም!

እነዚህ እርማኖች በኔ ላይ ስልጣን እንደሌላቸው አውጃለሁ፡፡

የክርስቶስን በረከቶች እንደመንፈሳዊ ውርሶቼ አድርጌ አውጃለሁ፡፡

ፍርሃትን እክዳለሁ፡፡ በክርስቶስ ደፋር መሆን ምርጫዬ ነው፡፡

የሰዎች መጠቀሚያ መሆንንና በቁጥጥራቸው ስር መሆንን እክዳለሁ፡፡

ጭቆናና የኃይል ጥቃትን እክዳለሁ፡፡

ፍርሃትን እክዳለሁ፡፡ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት የማጣት ፍርሃትን እክዳለሁ፡፡ የድህነትን ፍርሃት እክዳለሁ፡፡ ባርያ የመሆን ፍርሃትን እክዳለሁ፡፡ ተገዶ የመደፈርን ፍርሃት እክዳለሁ፡፡ ብቸኛ የመሆንን ፍርሃት እክዳለሁ፡፡ ቤተሰቦቼን የማጣት ፍርሃትን እክዳለሁ፡፡ የመገደልን እና የሞትን ፍርሃት እክዳለሁ፡፡

እስልምናን መፍራትን እክዳለሁ፡፡ ሙስሊሞችን መፍራትን እክዳለሁ፡፡

በሕዝባዊ ወይንም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የመሳተፍ ፍርሃትን እክዳለሁ፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉ ጌታ መሆኑን አውጃለሁ፡፡

ኢየሱስን በሁሉም የህይወቴ ክፍሎች ላይ ጌታ አድርጌ ራሴን እሰጠዋለሁ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የቤቴ ጌታ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የሃገሬ ጌታ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ሃገር ውስጥ ባሉ ሰዎች ሁሉ ላይ ጌታ ነው፡፡ ኢየሱስን እንደ ጌታዬ አድርጌ ራሴን እሰጠዋለሁ፡፡

ውርደትን እክዳለሁ፡፡ ክርስቶስ እንደተቀበለኝ አውጃለሁ፡፡ እርሱንና እርሱን ብቻ አገለግላለሁ፡፡

እፍረትን እክዳለሁ፡፡ በመስቀሉ በኩል ከሁሉም ኃጢኣት መንጻቴን አውጃለሁ፡፡ እፍረት በኔ ላይ መብት የለውም፡፡ ከክርስቶስ ጋር በክብር እነግሳለሁ፡፡

ጌታ ሆይ ሙስሊሞችን ስለመጥላታችን እኔንና ዘሮቼን ሁሉ ይቅር በለን፡፡ ሙስሊሞችንና ሌሎችን መጥላትን እክዳለሁ፡፡ የክርስቶስን ፍቅር በዚህ ምድር ላይ ላሉ ሰዎች ሁሉ አውጃለሁ፡፡

ስለቤተ ክርስቲያን ኃጢኣትና መሪዎች በተሳሳተ መንገድ ስለመገዛታቸው ንስሃ እገባለሁ፡፡

ማግለልን እክዳለሁ፡፡ በክርስቶስ በኩል ይቅርታን ማግኘቴን እና በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቴን አውጃለሁ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቄአለሁ፡፡ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት በሰማይም ሆነ በምድር ውስጥ ያለ ኃይል ለውጥ ሊያደርግብኝ አይችልም፡፡

ምስጋናዬን ወደ አባታችን እግዚአብሔር፣ ብቸኛ አዳኜ ወደሆነው ወደ ክርስቶስ፣ ብቻውን ህይወትን ወደሚሰጠኝ ወደ መንፈስ ቅዱስ ከፍ አድርጌ አነሳለሁ፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስን ጌታ መሆኑን ህያው ምስክር ለመሆን ራሴን አሳልፌ እሰጠዋለሁ፡፡ በመስቀሉ አላፍርም፡፡ በትንሳኤው አላፍርም፡፡

የአብርሃም የይስሃቅ የያዕቆብ አምላክ በሆነው የህያው እግዚአብሔር ልጅ መሆኔን አውጃለሁ፡፡

የእግዚአብሔርንና የመሲሁን ድል አውጃለሁ፡፡ ጉልበት ሁሉ እንደሚንበረከክ እና ምላስም ሁሉ ኢየሱስ ጌታ መሆኑን ለእግዚአብሔር ክብር እንደሚመሰከር አውጃለሁ፡፡

በዲህሚ ስርኣት ውስጥ በመሳተፋቸው ለሙስሊሞች ይቅርታን አውጃለሁ፡፡

አባቴ እግዚአብሔር ሆይ እባክህን ከዲህማ፤ ከዲህሚ መንፈስ እና እግዚአብሔራዊ ካልሆነ ከዲህማ ጋር ከተያያዘ መርህ ሁሉ ነፃ አውጣኝ፡፡

አሁን በቅዱስ መንፈስህ እንድትሞላኝ እና የኢየሱስ ክርስቶስን መንግስት በረከቶች ሁሉ በኔ ላይ ታፈስ ዘንድ እጠይቅሃለሁ፡፡ የቃልህን እውነት አጥርቼ መረዳት እችል ዘንድ እና በእያንዳንዱ የህይወቴ ገጽታ ላይ ተግባራዊ ማድረግ እችል ዘንድ ጸጋህን ስጠኝ፡፡ የህይወትንና የተስፋን ቃሎች አደርጋለሁ ብለህ ቃል በገባኸው መሰረት ትሰጠኝ ዘንድ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በስልጣንና በኃይል መናገር እችል ዘንድ ከናፍርቴን ትባርክ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ ለክርስቶስ ታማኝ ምስክር እሆን ዘንድ ድፍረትን ስጠኝ፡፡ ለሙስሊሞች ጥልቅ ፍቅርንና የክርስቶስን ፍቅር ከነርሱ ጋር መካፈል እችል ዘንድ ሸክምን እንድትሰጠኝ እለምንሃለሁ፡፡

እነዚህን ነገሮች አዳኝና ጌታ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውጃለሁ እጠይቃለሁ፡፡ አሜን፡፡