መስጊድ እና በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው ሚና

በባልታዛር እና አብደናጎ

ክፍል ስድስት

የመስጊድ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ሙስሊም ባልሆነ ሰው አማካይነት

ፋትዋ ቁጥር 26159፣ በረመዳን 17፣ 1421 ከሂጅራ በኋላ (ኤፕሪል 5፣ 2000)

መስጊዱን የገነባነው ከእርዳታ በተገኘ ገንዘብ ሲሆን አብዛኛው የመጣው ከአካባቢው ባለ ሥልጣን ነው። ስለዚህ አሁን የመክፈቻውን ስነ-ስርዓት እንዲያከናውን ከንቲባውን ጠርተነዋል። ሸሪዓ እንዲህ እንድናደርግ ይፈቅዳል?

ፋትዋ፦ ለአላሕ ምስጋና፣ ለአላሕ መልዕክተኛና ለአጋሮቹም ፀሎትና ሰላም ይሁን። መላው የነብያችን ሕይወት ትምህርታችን ስለሆነ እንደ ብርሃን ምንጭነቱ እና እንደ መገለጥ እንጠብቀዋለን፣ መርሆዎቹን እንወስዳለን፣ አካሄዱንም እንከተላለን። ምክንያቱም እርሱ እጅግ የተከበረና በሁሉም አቅጣጫ ከፍተኛ የሆነ ሰው ነው። ለዚህ ሁኔታ ምሳሌ የምንወስደው “ከሁዳይቢያ” ክስተት ነው። “የሁዳይቢያ” ደንብ የሚያተኩረው በስምምነት እና ሚዛንን በመጠበቅ ላይ ነው። እንዴትና መቼ መሆን ይችላል? ለእስልምና እና ለሙስሊሞች ጥቅም የሚያስገኘውን ተገቢ ፖለቲካዊ ውሳኔ የማሳለፍ ጉዳይ ነው።

የአላሕን ፈቃድ ለማድረግ በሚሻና በሸሪዓ እንደተገለጠው አድርጎ ሊታዘዘው በሚፈልግ አንድ አካል እና ሌላኛው ደግሞ ካፊር በሆነና ከአላሕ ጋር ጠላት በሆነ ሰው መካከል ያለውን ታማኝነት እና ኅብረትን አሽቀንጥሮ መጣል ለመረዳት “ከሁዳይቢያ” ደንብ የተሻለ ምሳሌ የለንም። የአላሕ መልዕክተኛን ብልሀት የተሞላበት የዕቅድ ስኬት እና ጠላቶቹን በገዛ መንገዳቸው ሳሉ በልጦ መገኘቱን እናይበታለን።

“የሁዲቢያን” ዘመቻ ሊያከናውን በተነሳ ጊዜ አረቦች እና ሰራዊቶቻቸው ወደ መካ ከእርሱ ጋር እንዲሄዱ ጥሪ አቀረበላቸው። ከሰዎቹ መካከል በዚህ ዓለም ጉዳይ የተጠላለፉት እነርሱ እስከሚዘጋጁ ድረስ እንደሚጠብቃቸው ያሰቡ ቢሆንም ትቷቸው ለመሄድ ዝግጁ ከነበሩት ከአንሳር፣ ሙሃጀሩን እና ከተከተሉት ሁሉ ጋር ተጓዘ።

የአላሕ መልዕክተኛ መብቶቻቸውን ይተዉለት ዘንድ ሙስሊሞችን ብቻ ሳይሆን ሃይማኖት የለሾቹን ካፊሮች ጭምር አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ስምምነት አሳይቷቸዋል።

ስለዚህ ከጠላት ጋር የሚደረጉ ስምምነቶች ሁሉ ተቀባይነት ማጣት አይኖርባቸውም። ጠላት የሚያቀርበውን ጥያቄ እና መደራደሪያ መቀበልም እንደዚሁ መጥፎ አይደለም። ይህንን በማድረጉ ውስጥ ያለው ጥበብ በካፊሮች ብልሹነት ላይ የእስልምናን ድል እያወጁ እጅግ ጥቂት ነገር ሰጥቶ ከፍተኛውን ነገር መቀበል ነው። ሃይማኖት የለሾች ሰዎች ሙስሊሞች ስምምነቱን “ቢስሚላህ አል ራህማን ራሂም”/ “እጅግ ሩሕሩሕ እና መሀሪ በሆነው በአላህ ስም” ብለው እንዲጀምሩት ባለ መፍቀድ እጅግ አንገፍጋፊ የልዩነት መጋረጃ ይጋርዳሉ። ሙስሊሞች ያንን ለማድረግ ባይፈቅዱም የአላህ መልዕክተኛ በጥበቡ ይህንን ፈተና በእሺታ ተወጥቶታል። የተለመደውን ነገር ግን እጅግ የተከበረውን የአላህ መልዕክተኛ የሚል ማዕረጉን እንኳ ሊቀበሉለት ስላልወደዱ “መሐመድ ቢን አብደል አላህ” ብሎ ጽፏል።

ደንዳናነት ወይም ጭካኔ፣ ጥቃት እና አመፀኝነት ሁል ጊዜም የኃይል መንገዶች አይደሉም፤ መቻቻል እና መቀባበል፣ ጥበብ እና እንደየሁኔታው አካሄድን መለወጥም የድክመት ምልክቶች አይደሉም። “ሁዲባያን” የሚያስተውለውና የሚያሰላስለው ሰው ሁሉ የአላህ መልዕክተኛ ድል የነሳው በመገንዘብ፣ ታጋሽ በመሆን፣ በመደራደር እና ከእነርሱ ልቆ በመገኘት እንደ ሆነ ሊረዳ ይችላል። ይህንንም ሲያደርግ የነበረው ሙስሊሞች በድካምም ሆነ በብርታት ላይ በነበሩ  ጊዜ ሁሉ ነው።

“ከሁዲባያ” ብልሃት በመነሳት አንድ ካፊር የመስጊድን መክፈቻ ስነ-ስርዓት ማከናወኑ ለሙስሊሞች እና ለእስልምና ጥቅም የሚያስገኝ ሊሆን ይችላል። እጅግ ጠቃሚው ክፍል ደግሞ እስልምና እና ሥልጣኑ በሕዝብ ዘንድ መታወቁና ዕውቅና ማግኘቱ ነው። ምክንያቱም መስጊድ የእስልምና በአካባቢው መኖር ምልክት፣ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ የልብ ምት፣ ማኅበረሰቡ ክፋትን፣ ቸልተኝነትን እና ከሀዲነትን ስለ መዋጋት የሚማርበት ስፍራ ነው። የአላህ ሕግጋት የሚተገበሩበት ዩኒቨርሲቲ እና ፍርድ ቤት ስለሆነ የአላህ መልዕክትና እስልምና ከፍ ከፍ እንደሚልና ከእርሱም የሚልቅ ምንም እንደማይኖር በተናገሩት መሠረት በማኅበረሰቡና በመጨረሻም በግዛቱ እንዲሁም ከዚያ አልፎ የሥልጣን ምልክት ነው።

ራሳቸው ለራሳቸው ከሚያሳዩት ይልቅ በባሪያዎቹ ላይ እጅግ መሐሪ የሆነው አላህ በሙስሊሞች ላይ ካለው ርህራሄ የተነሳ፣ ቀንበራቸውን ለማለዘብና ሸክማቸውን ለማቅለል የሚበጁ ሕጎችን አዘጋጅቶላቸዋል። ስለዚህ በሁዲቢያ ውስጥ በሁዲቢያ ለነበሩ ሙስሊሞች እና ከዚያም በኋላ ላሉ ሙስሊሞች ምህረቱን የሚያሳይ ነገር አስፍሮላቸዋል።

በመደምደሚያው ይህ ክስተት እና ክስተቱን መረዳታችን የሚያስተምረን ነገር አላህን የሚፈሩ እና ለእርሱ ታማኝ የሆኑት በትዕግስት ውስጥ የሚያገኙትን ድል ነው። ኢ-ፍትሐዊ የሆኑት የእነርሱ ዙፋን ይገለበጥና ይጠፋል። የቸልተኝነት ምክንያት አልባነት ጠፍቶ ደካሞች ትዕግስትን የተላበሱ እንደ ሆነ ጥንካሬን ያገኛሉ። ሁዲቢያ የሚያስተምረን የአላህን ሃይማኖት ለማወጅና ለማስፋፋት የሚጠቅሙንን አጋጣሚዎች ሁሉ አጥብቀን እንድንይዝ ነው። የእውነት ድል በሀሰት ሁሉ ላይ፣ ሽንፈት ለእስልምና ጠላቶች፣ ፀሎትና የአላህ በረከት በነብያችን በመሐመድ ላይ ይሁን።

እስልምና ከሁሉም ልቆ ከፍ ይላል

የሙስሊም ምሁራን ሁሉም ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ አብዛኛዎቹ ሙስሊሞች በዚህ መርህ ተስማምተው በዝርዝር ያብራሩታል። በቅርቡ በመካ የሚገኘው የኡም ኢል ቁራ የኒቨርሲቲ ዶ/ር አቢድ ቢን መሐመድ ሱፍያኒ ከላይ በሰፈረው ዓረፍተ ነገር ላይ ጥናት አድርጎ በሰፊው ጽፎበታል። አብዛኛዎቹን ታዋቂ የእስልምና ምሁራን በመጥቀስ “እስልምና ከሁሉም በላይ ከፍ ማለቱ” ሁሉንም የእስልምና ሕግጋት የሚገዛው የእስላማዊ ሸሪዓ ዋነኛ መርህ እንደ ሆነ ገልጿል። ይህንን ውስብስብ ጉዳይ ለመረዳት ለሚፈልጉ ሁሉ የእርሱ እጅግ ዝርዝር እና ሁሉን አቀፍ ጥናት ጠቃሚ ነው። በተጨማሪም በተለይ መስጊድና ህንፃዎቹ ላይ ተፅዕኖ የሚያደርጉ ጉዳዮችን በተናጠል አንስቶ የራሱን መደምደሚያ አስፍሯል።

ላነሳነው ጉዳይ በሚጠቅም ሁኔታ የሌላ ሃይማኖት ህንፃዎችን፣ በተለይም ደግሞ  የአብያተ ክርስቲያናትን ህንፃ በተመለከተ - ለምን ግንባታቸው እንደማይፈቀድ፣ በዓለም ላይ ጥፋትን የሚያስከትሉ የኑፋቄ ማዕከሎች ስለ ሆኑ፣ ከአላህ እና ከመልዕክተኛውም ጋር ጠላቶች የሆኑ ባለቤቶች ስላሏቸው እድሳትና ጥገናቸውም መፈቀድ እንደሌለበት - እስልምና ያለውን ደንብ አስፍሯል።

ከላይ በተጠቀሰው መርህ እና ጠቃሚ ከሆኑት ቁርአናዊ ጥቅሶች የተነሳ መስጊዶች በቁመታቸው ብቻ ሳይሆን በትልቀትና በስፋታቸውም ከሌሎቹ የማያምኑ ሰዎች ህንፃዎች መብለጥ አለባቸው፤ በሌላ አነጋገር በሁሉም አቅጣጫ ምርጥ መሆን አለባቸው ማለት ነው።

በተለይ በማያምኑ ሰዎች መካከል ሆነው እና ባለማመን በተከበቡበት ጊዜ ታላቅነቱ ተብራርቶ ይታይ ዘንድ መስጊድ  ረዥሙ፣ ትልቁ እና ሰፊው፣ ባጠቃላይ በሁሉም ነገር የተመረጠው ሆኖ ይታይ ዘንድ በርዝመቱ እጅግ ከፍ ማለት አለበት።

ለዚያ ነው የኒውሃም መስጊድ የተገለፀውን ዓይነት ግዝፈት እና ውበት እንዲኖረው የታቀደው። በመቀጠል በማንችስተር እና ሌሎቹም ታላላቅ የብሪታኒያ ከተማዎችና በዩናይትድ ኪንግደም ብቻ ሳይሆን በመላው ምዕራባዊ ዓለም ውስጥ መስጊዶች ታላላቆቹ እና እጅግ አስደናቂዎቹ ህንፃዎች እንዲሆኑ ይፈለጋል።

ማጠቃለያ

እስካሁን ድረስ ያየናቸው ነጥቦች መስጊድ ከሃይማኖታዊ ስፍራ የላቀ ሚና እንዳለው በግልፅ ያሳያሉ። እስልምና ራሱን እንደሚያየው እና ሰዎችን ከፋፍሎ እንደሚያስቀምጠው ሙስሊሞች ንፁህ ሲሆኑ ከሀዲዎች ደግሞ የተቀደሱ አይደሉም፦

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው። ከዚህም ዓመታቸው በኋላ የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ። ድኽነትንም ብትፈሩ አላህ ቢሻ ከችሮታው በእርግጥ ያከብራችኋል። አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና። (ቁርአን 9.28)

የእሳት ጓዶችና የገነት ጓዶች አይተካከሉም። የገነት ጓዶች እነርሱ ምኞታቸውን አግኚዎች ናቸው። (ቁርአን 59.20)

«ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም። ሩቅንም አላውቅም። ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም። ወደእኔ የሚወርድልኝን እንጅ ሌላን አልከተልም» በላቸው። «ዕውርና የሚያይ ይስተካከላሉን አታስተነትኑምን» በላቸው። (ቁርአን 6.50)

አማኝ የሆነ ሰው አመፀኛ እንደ ሆነ ሰው ነውን? አይስተካከሉም። (ቁርአን 32.18)

ለሰዎች ከተገለፀች ሕዝብ ሁሉ በላጭ ኾናችሁ በፅድቅ ነገር ታዛላችሁ፤ ከመጥፎም ነገር ታዛላችሁ፤ በአላህም (አንድነት) ታምናላችሁ። የመጽሐፉም ሰዎች ባመኑ ኖሮ ለነርሱ የተሻለ በኾነ ነበር። ከነርሱ አማኞች አሉ። አብዛኞቻቸው ግን አመፀኞች ናቸው። (ቁርአን 3.110)

ከምእመናን የጉዳት ባለቤት ከኾኑት በቀር ተቀማጮቹና በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የሚታገሉት አይተካከሉም። በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የሚታገሉትን አላህ በተቀማጮቹ ላይ በደረጃ አበለጠ። ለሁሉም አላህ መልካሚቱን (ገነት) ተስፋ ሰጠ። ታጋዮቹንም በተቀማጮቹ ላይ አላህ በታላቅ ምንዳ አበለጠ። (ቁርአን 4.95)

እስልምና ያመጣው መለያየትና የሰላም ቤት እና የጦርነት ቤት የሚለው ፅንሰ-ሀሳብ መለያየትን እና ከሌሎች ጋር ለመስማማት እና አብሮ ለመሥራት አለመፈለጋቸው ጉዳዩን መከፋፈል እና መድልዎ የሞላበት ስለሚያደርገው ቢያንስ ከለዘብተኛ የዴሞክራሲ አተያይ አንፃር ተቀባይነት አይኖረውም።

ምንም ተጨማሪ ማብራሪያ ባናደርግበትም ይህ ጠባብ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች መስጊድን የሚያዩበት አተያይ እንዳልሆነ በኅብረተሰቡ መካከል ያለው ሚና ራሱ ይናገራል። በሁሉም ትምህርት ቤቶች እና የእስልምና ቅርንጫፎች ሁሉ በግልፅ ይታያል።

በመጨረሻም፣ ሁሉን አቀፍ ስልት (ማኅበራዊ-ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ-ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ-ሕጋዊ፣ ሕግ አስፈጻሚ፣ ወታደራዊ) እንደ ሆነ ስለሚያወሳ በየትኛውም የእስልምና እንቅስቃሴ ውስጥ ቢሆን ፖለቲካ እንደማይታጣ ግልፅ ነው።

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ

እስልምና እምነት ብቻ ነውን? መስጊድስ በህብረተሰቡ ዘንድ ሚናው ምንድነው? ለሚሉት ጥያቄዎች መጠነኛ መልስ ተሰጥቷል፡፡ ይሁን እንጂ በዓለማችን ላይ አሁን ከምናየውና ከምንሰማው እኛም የየራሳችን ግንዛቤና ሚዛናዊ የሆነ መደምደሚያ ላይ ልንመጣ ይገባናል፡፡ በተለይም ከሃይማኖት ልናገኝ የሚገባንን ጥቅም ማግኘት አለብን፡፡

የአንድ ሃይማኖት ተከታዮች ከሃይማኖታቸው ማግኘት የሚገባቸው ዋናውና ትልቁ ነገር ከአምላካቸው ጋር መታረቅ መቻላቸውና ዘላለምን ከእርሱ ጋር መሆናቸው ነው፡፡ ይህ ትልቅና ዋና ትኩረት ሃይማኖትን ከፖለቲከኛነት ትስስር ውስጥ በቅፅበት ያወጣውና የትኩረት አቅጣጫውን ይቀይረዋል፡፡

ስለዚህም እግዚአብሔራዊ የሆነ ሃይማኖት ዓላማው ሰዎችን ለመቆጣጠርና የበላይነቱን ለማሳየት ሳይሆን ሰዎቸ ስለራሳቸው ሕይወትና፣ ስለዚች ዓለም አጠቃላይ ሁኔታ እንዲሁም ስለ እግዚአብሔር እውነቱን እንዲገነዘቡና በእውነት ላይ ተመስርተው ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ ትምህርትንም ምክርንም መስጠት ነው፡፡

የምንከተለው ሃይማኖት ዘላለማዊ ለሆነው የነፍሳችን ጥልቅ ጥያቄ ማለትም የመሰረታዊውን መንፈሳዊ ፍላጎታችንን ጥያቄ የማይመልስ ከሆነ፤ አንደኛ እራሱን ሃይማኖቱን ልንጠይቀው፣ ሁለተኛ የጥያቄያችን መልስ የሚገኝበትን እምነት በቅንነት እና በእውነት ልንፈልግ፣ ይገባናል፡፡

ለዚህ የእውነት ፍለጋ ጉዞ በትክክል ሊረዳን የሚችለው መጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና ብቻ ነውና ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና በመምጣት እውነትን ተረዱ እግዚአብሔርም ይርዳችሁ፡፡

 

ወደ ማውጫው መመለሻ

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ