የቁርዓኑ አላህ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ነውን?

Sam Shamoun

[ክፍል አንድክፍል ሁለት [ክፍል ሦስት] [ክፍል አራት]

በአዘጋጁ የተቀናበረ

አላህ የስጋዊ ደስታ ፈጣሪ ነው፡፡

የቁርዓን ፓራዳይዝ ወይንም መንግስተ ሰማይ ከመጽሐፍ ቅዱሱ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡ በአላህ ፓራዳይዝ ውስጥ የእስልምና አማኞች  በግብረ ስጋ ግንኙነትና በስጋዊ ደስታ ለዘላለም እንደሚያሳልፉ በቁርዓን ውስጥ ተገልጧል፡፡ የሚከተሉት የቁርዓን ጥቅሶችም ይህንን በትክክል የሚያሳዩ ናቸው፡-

‹እነዚያን ያመኑትን መልካሞችንም የሠሩትን ለነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መኾኑን አብስራቸው ከርሷ ከፍሬ (ዓይነት) ሲሳይን በተመገቡ ቁጥር (ፍሬዎቿ ስለሚመሳሰሉ) ይህ ያ ከአሁን በፊት የተመገብነው ነው ይላሉ፡፡ እርሱንም ተመሳሳይ ኾኖ ተሰጡት ለነሱም በውስጧ ንጹሕ የተደረጉ ሚስቶች አሏቸው እነሱም በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው› 2.25፡፡ እንደዚሁም በተጨማሪ ‹እነዚያንም ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን ከስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘለዓለም በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በእርግጥ እናገባቸዋለን ለነሱ በውስጥዋ ንጹሕ ሚስቶች አሉዋቸው የምታስጠልልን ጥላም እናገባቸዋለን› 4.57፡፡ ቀጥሎም ‹እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለነሱ) ፈጠርናቸው፡፡ ደናግሎችም አደረግናቸው፡፡ ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎች እኩያዎች (አደረግናቸው)፡፡ ለቀኝ ጓዶች (አዘጋጀናቸው)› 56.35-38፡፡ ሌላም ‹ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አላቸው፡፡ አትክልቶችና ወይኖችም፡፡ እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡ የተሞሉ ብርጭቆዎችም› 78.31-34፡፡

ስለዚህም በቁርዓናዊ የእስልምና ትምህርት መረዳት መሰረት ሙስሊም ወንዶች ሁሉ በፓራዳይዝ ውስጥ የሚጠብቃቸው ነገር ግብረ ስጋ ግንኙነትን እንዲፈፅሙ ጡታቸው ጉች ያለ ሴቶች እንደሆኑ ነው እነሱም ደግሞ ወደ ድንግልና እንደገና የሚመለሱ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ፓራዳይዝ ግን ከእንደዚህ ዓይነት ስጋዊነት ፍፁም የፀዳ ሲሆን የተሞላውም በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ፍቅርና ደስታ ነው፡፡ ስለዚህም የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር አማኞች ሽልማት የሚሆነው ከእግዚአብሔር ጋር በዘላለም ክብር አብረው መኖራቸው ነው፡፡ ‹ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። የዚህ ዓለም ልጆች ያገባሉ ይጋባሉም፥ ያን ዓለምና ከሙታን ትንሣኤ ሊያገኙ የሚገባቸው እነዚያ ግን አያገቡም አይጋቡምም፥ እንደ መላእክት ናቸውና፥ ሊሞቱም ወደ ፊት አይቻላቸውም፥ የትንሣኤም ልጆች ስለ ሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።› ሉቃስ 20.34-36፡፡ እንዲሁም ደግሞ ተመሳሳይን ቃል በሮሜ 14.17 ላይ እናገኛለን፤ ‹የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።› ቀጥሎም በራዕይ 21.3-4 ላይ ደግሞ የእግዚአብሔር መንግስተ ሰማይ የተገለጠችው እንደሚከተለው ነው፡ ‹ታላቅም ድምፅ ከሰማይ። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤ እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።›

አላህና መሐላዎቹ

በአላህና በያህዌ (እግዚአብሔር) መካከል ካሉት ግልፅ ልዩነቶች ውስጥ አንዱ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር የሚታየው በራሱ ሲምል ነው፤ ምክንያቱም ከእሱ የሚበልጥና የሚምልበት ምንም ሌላ ነገር የለም፡፡

‹እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ። በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ እያበዛሁም አበዛሃለሁ ብሎ፥ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ፥ በራሱ ማለ፤› ዕብራውያን 6.13:: ‹ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው ይምላሉና፥ ለማስረዳትም የሆነው መሐላ የሙግት ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል፤› ዕብራውያን 6.16:: ስለዚህም እግዚአብሔር ቃል ኪዳንን በሚገባበት ጊዜ የማረጋገጫ መሐላን ሲምል በራሱ ነው የማለው፡፡

‹ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፥ አትመለስም። ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፥ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።› ኢሳያስ 45.23፡፡ ‹ነገር ግን ይህን ቃል ባትሰሙ፥ ይህ ቤት ወና እንዲሆን በራሴ ምያለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።› ኤርምያስ 22.5፡፡

ነገር ግን አላህ በቁርዓን ውስጥ የሚታየው ከእሱ ባነሱት ነገሮች ሲምል ነው

አንደኛ፡ በቁርዓን ይምላል፡-

‹ጥበብ በተሞላበት ቁርዓን እምላለሁ› 36.2፡፡ ‹ጸ. (ሷድ)፤ የክብር ባለቤት በሆነው ቁርዓን እምላለሁ (ብዙ አማልክት እንደሚሉት አይደለም)› 38.1፡፡

ሁለተኛ፡- በሰማይና በከዋክብት ይምላል፡-

‹በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ› 86.1፡፡ ‹ከክህደት ይከልከሉ በጨረቃ እምላለሁ› 74.32፡፡ ‹በኮከብ እምላለሁ በወደቀ (በገባ) ጊዜ› 53.1፡፡

ሦስተኛ፡ በብዕር ይምላል፡-

‹ነ. (ኑን) በብርዕ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት› 68.1፡፡

አራተኛ፡ በከተማ ይምላል፡-

‹በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ› 90.1፡፡

አምስተኛ፡ በፍጥረት ይምላል፡-

‹በሌሊቱ እምላለሁ (በጨለማው) በሚሸፍን ጊዜ፤ በቀኑም በተገለጸ ጊዜ፤ ወንድንና ሴትን በፈጠረውም (አምላክ እምላለሁ)፡፡› 92.1-3፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡-

መንግስተ ሰማይን በተመለከተ የቀረቡት ንፅፅሮች እንደሚያሳዩት በአላህና በመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር መካከል ትልቅ ልዩነት እንዳለ ነው፡፡ እግዚአብሔር ቅዱስና ንፁህ ነው የእሱም መንግስተ ሰማይ ያንኑ ነው የምታንፀባረቀው፡፡ የአላህ መንግስተ ሰማይ ግን መጠጥ መብልና ግብረ ስጋ ግንኙነት ነው፡፡ ልዩነት አይደለምን?

እንደዚሁም ደግሞ ከቁርአን ውስጥ የተጠቀሱትና አላህ በማንኛውም ነገር የሚምል መሆኑን በግልጥ የሚያሳዩት ክፍሎች አስገራሚ ናቸው፡፡ የሚጠቁሙትም የሙስሊሞች አምላክ ‹አላህ› ፈጣሪ አለመሆኑን ነው፡፡ በተጨማሪም የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር በራሱ ብቻ ሲምል አላህ ግን በሌሎች ነገሮች መማሉ በሁለቱ መካከል ትልቅ ልዩነት ያለ መሆኑን እንደገና በግልጥ ያሳያል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔርና የቁርኣኑ አላህ አንድ እንዴት ሊሆኑ ይችላሉ? በፍፁም አንድ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

አንባቢ ሆይ! ከዚህ በላይ ያሉት ሁለት ዓይነት ንፅፅሮች የተመሠረቱት በማስረጃ ላይ መሆኑን በጥንቃቄ አስተውል፡፡ ከዚያም ምን ዓይነት አምላክ እንደምትከተል እራስህን ጠይቅ፡፡ በሕይወት ውስጥ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ መጠየቅ አስፈላጊና ማስተዋልም ነው ምክንያቱም የዘላለምን ሕይወት የት ማሳለፍ እንደምትችል እንድታስብ ይረዳሃልና፡፡

 ስለዚህም ወደ እውነተኛውና ወደ ቅዱሱ የመጽሐፍ ቅዱስ አምላክ እንድትመጣ እንመክርሃለን፡፡ ወደ እሱ እንዴት መምጣት ይቻላል? ወደ እሱ መምጣት የሚቻለው በአንድ መንገድ ብቻ ነው እሱም ‹መንገድ እውነትና ሕይወት› በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ነው፡፡ ስለ ጌታ ኢየሱስ የበለጠ ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስን አግኝተህ አንብቡ፡፡ በዚህም ገፅ ላይ በተከታታይ የሚወጡትን ትምህርቶች ተከታተል እግዚአብሔር በፀጋው ይርዳህ፡፡

ወደ ክፍል ሦስት ይቀጥሉ::

 

 የትርጉም ምንጭ: IS ALLAH THE GOD OF BIBLE?

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ