እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ

[ክፍል ሁለት] ክፍል ሦስት [ክፍል አራት]
ቅንብር በአዘጋጁ

 

የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ የወሰደው እርምጃ ተያይዞም የተነሳሳው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ የተቃውሞው ሰልፍ አንቀሳቃሾች ልዩ ልዩ አሳማኝ የሚመስሉና የሌላውን ድጋፍ ሊያስገኙ የሚችሉ ጥረቶች ያሉባቸው ትንተናዎችን በተከታታይና በሚችሉት መንገድ ሁሉ ሰጥተዋል፡፡ አብደላ አደም ተኪ የተባለው ጸሐፊ “በኢትዮጵያ እስልምና ላይ የተቃጣው የኢህአዴግ ዘመቻ፡ መንስኤዎቹ፤ ተጽእኖዎቹና ቀጣይ ሁኔታዎች” በሚል ርዕስ የጻፈው ባለ 73 ገፅ ትንተና በቀላሉ ይህንን የሚያመላክት ነው፡፡ አብደላ አደም ተኪ ከህዳር 1989 እስከ ታህሳስ 2004 ድረስ የኢህአዴግ አባል እንደነበር ጠቅሶ፣ ኢህአዴግ አሁን በእስልምና ላይ የያዘው አቋም ልክ እንዳይደለ፣ ኢህአዴግ ከብዙው ሙስሊም ይልቅ አል-አሕባሽን እንደሚደግፍ እንዲያውም በአል-አሕባሽ የተቀነባበሩ ስልጠናዎች እንደተሰጡ በዝርዝር የተሳታፊ ስሞችንና ዋና ዋና ሰዎችን ጠቅሶ አስቀምጧል፡፡

አብደላህ አደም ተኪ በጽሑፉ ውስጥ ኢህአዴግ በእስልምና ላይ የተሳሳተ አመለካከት እንዳለውና ይህንን አመለካከቱን ለማስረፅ መንግስት አል-አሕበሽን እንደተጠቀመበት አስቀምጧል፡፡ የብዙውን ሙስሊም ማለትም የዋሃቢያንን እንቅስቃሴ መንግስት የሚወነጅለው ያለምንም መረጃ እንደሆነ አቅርቧል፡፡ በጽሑፉ ውስጥ እስልምና ሰላማዊ እንደሆነ በተለይም ቃሉን እራሱን እስላምን ጠቅሶና ለሰላም ለፍትህ ለነፃነት የቆመ እምነት እንደሆነም ነግሮናል፡፡

https://docs.google.com/file/d/0ByxJ0rgpLftXM3lDR0h4MU1ZVEU/edit?pli=1

ቢሆን በጣም ጥሩ ነበር በዓለም ታሪክና አሁንም በተለያዩ አገሮች ላይ በተግባር የሚታየው ግን የተቃራኒውና ኢትዮጵያም የሚጠብቃት የወደፊት ዕጣ ከዚያ ያለፈ እንደማይሆን ነው፡፡

የቴዎሎጂካል ክርክሮች ነጥቦች

እነፕሮፌሰር ኤርሊች በበሰለ ነገር ግን ማንንም ባልወገነ ታሪካዊ አቀራረባቸው ያስቀመጡት ስረ መሰረታዊውን የአመለካከት ልዩነትና የሚያመጣውን የወደፊት ውጤት ጭምር ነው፡፡ በእርግጥ እውነተኛ ታሪክ ሊቀለበስ ወይንም የሆነ ቡድንን ሊወግን አይገባውም፣ እውነተኛ ታሪክ የነበረውን የተደረገውን ወይንም ያለውን እውነታ ያቀርባል፡፡ አንዳንዶች የራሳቸውን ዓላማ ለማራመድ ብቻ ሲሉ ያልነበረ ወይንም በማስረጃ ሊረጋገጥ የማይችል ታሪክን እንደሚጽፉ እንደሚያስጽፉም የታወቀ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የፈጠራ ታሪክ ቆይቶ በእውነተኛ ታሪክ መጋለጡ አይቀርም፣ ይህ እስከሚሆን ብዙዎች እውነት ለመሰላቸው ነገር ግን ፈጠራ ለሆነ ታሪክ ጊዜያቸውንና ሕይወታችን ያበላሻሉ አገራቸውንም ጭምር፡፡

እነ ፕሮፌሰር ኤርሊች ባደረጉት ጥልቅ ጥናት በአል-አሕበሽና በዋሃቢያ መካከል ያሉትን የመረሩ ልዩነቶች ስረ መሰረቶቻቸው በእስላማዊ ትምህርታቸው ላይ ይሁን እንጂ ከዚያም ያለፈ ነው ይላሉ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በአንድ በኩል የሙስሊሞች አንድነትና ልዩነት ላይ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሙስሊሞች ክርስትያኖችንና አይሁዶችን እንዴት እንደሚመለከቷቸው ስለሚያካትትም ነው ይላሉ፡፡ በእርግጥም ከተለያዩ ክሶችና አንዱ ሌላውን ከሚመለከትበት አመለካከት በላይ በጣም ጥልቅ የሆነ የእስላማዊ ማንነትም እንዳለበት ይናገራሉ፡፡ በታሪክ ምርምር የተገኙትና አሁንም ገሃድ የሆኑት ዋና ዋናዎቹ የቲዎሎጂካል ነጥቦች ከዚህ ቀጥሎ ይቀርባሉ፡- 

1. የእግዚአብሔር ስብዕና እና ችሎታው፡

የዋሃቢያ ማዕከላዊ መሰረታዊ ትምህርት ታውሂድ ነው፣ በመሰረቱም እግዚአብሔር ልዩ፣ አንድ፤ ሃያል በሁሉ ቦታ የሚገኝ፤ ሁልጊዜ የሚሳተፍ አምላክ ነው፡፡ (በእርግጥ ዋሃቢዎች እራሳቸውን የሚጠሩት ሙዋሂዱን በማለት ነው)፡፡ ኢትዮጵያኖቹ ማለትም አል-አሕበሾቹ ለዋሃቢዎቹ እንዲሁም ለሁሉም የሳላፊ እንቅስቃሴ ትምህርትና አመለካከት የሚሰጡት ስያሜ እነርሱ እግዚአብሔርን እንደሰው በእርግጥ ቆጥረውታል በማለት ነው፡፡ ስለዚህም እነርሱን “ሙሻቢሁን” በማለት ይጠሯቸዋል፣ ማለትም እግዚአብሔርን እንደዚህ ዓይነት ምሳሌነትና ስብዕና ሰጡት ብለው ነው ስለዚህም በእርግጥ እነርሱ እያደረጉ ያሉት እንደ ሙሽሪኩን ፓጋኖች ነው እንደሚሉ የነፕሮሴፈር ኤርሊች ጽሑፍ ያሳያል፡፡

አንደኛው ታዋቂ ጉዳይ እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረ በኋላ በዙፋኑ ላይ ተቀምጧል የሚለውን የቁርአንን አረፍተ ነገር መተርጎም በተመለከተ ያለው ነው፡፡ በዋሃቢ ጽሑፎች መሰረት የዚህ ትርጉም እርሱ ዓለምን ተቆጣጠረ ማለት ነው፡፡  እግዚአብሔር በየትም ቦታ የሚገኝ ነው በማለት ዋሃቢዎች የሚናገሩትን ነገር ሼክ አብደላ በዚህ ነጥብ ላይ ተመስርቶ ለማጣጣል ይሞክራል፡፡ እርሱም ለተከታዮቹ የነገራቸው “እነርሱ እግዚአብሔር የትም ቦታ ነው፣ በተወሰነ ቦታ ላይ አይደለም ያለው ይላሉ፣ እርሱ በዙፋኑ ላይ ስላለና ይህ ደግሞ በቦታ መወሰን  አይደለምና፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ባዶ (ቫኪዩም) እራሱን የቻለ ውሱን የሆነ ቦታ አለው፣ ስለዚህም በዋሃቢዎች አባባል እግዚአብሔር ያለበት ቮሊም የሚወሰን ነገር ማለት ነው፣ በመሆኑም እርሱም ጅማሬም መጨረሻም አለው” ይህ ዋሃቢዎች የሚናገሩት ነገር ከሼክ አብደላ የራሱ ትርጉም ጋር በጣም የተለየ ነው፤ የእርሱም ትርጉም፡

“በዚህ ዓለም ላይ ያው ማንኛውም ነገር እዚህ ለዘላለም አልነበረም፡፡ እርሱን የፈጠረው ኃይል ነበር፡፡ ይህ ኃይል ለዘላለም ነበር፣ እርሱ ጅማሬ አልነበረውም፡፡ የእግዚአብሔር እውቀት እውነት ሊሆን አይችልም፣ ይህ ዓለም ምንም ነገርን የማይመስል ፈጣሪ አለው በሚል እምነት ላይ እውነት ሊሆን አይችልም፡፡ የእርሱ ቮሊዩም ቁሳዊ ወይንም ተጨባጭ ሊሆን አይችልም፡፡ እርሱም ትልቅ ወይንም ትንሽ አይደለም፣ እርሱም የማይንቀሳቀስ ወይንም ተንቀሳቃሽ አይደለም፡፡ እርሱ ከማንኛውም ቁሳዊ የቮሊዩም ፅንሰ ሐሳብ ውጭ ነው፡፡ ይህንን እውነታ የሚያውቅ ማንም እግዚአብሔርን ማወቅ ይችላል፡፡ ማንም ይህንን የማያውቅ ደግሞ ምንም አያውቅም እናም ደግሞ ሙስሊም አይደለም ወይንም አማኝ አይደለም” እርሱም በዚህ ነጥብ ላይ እንደሚከተለው ቀጠለ፡-

“ዋሃቢዎች እና የእነርሱ አባቶች ከሙሻቡሁን መካከል፣ የሚያስቡት እግዚአብሔር አካል እንዳለው ነው፡፡ እነርሱም የሚታመኑት ግልብ በሆነ ቁርአናዊ፣ ልማዳዊ  አረፍተ ነገሮች አተረጓጎም ላይ ነው፡፡ ይህ ግልብነት ደግሞ እግዚአብሔር አካል አለው፣ ተንቀሳቃሽ ነው፣ በአንድ ቦታ ላይ የሚገኝ ነው፣ እርሱ እጅ አለው እርሱ ይስቃል ወ.ዘ.ተ የሚለውን አስተሳሰብ አምጥቷል፡፡ እነዚህ አረፍተ ነገሮችና ልማዶች ሁሉ ከግልብና ላይ ላዩን ከሆነ አተረጓጎም ይልቅ ጥልቅ የሆነ ትርጉሞች አሏቸው፡፡”

ሼክ አብደላ በሌክቸሩ ውስጥ በዋሃቢዎች ላይ ብዙ ጊዜ ቀልድን ይጥላል፣ በዚህ ጉዳይ ላይ እና “እነሱ በእንደዚህ ዓይነት ቀላል ትርጉም በኑፋቄ ወጥመድ ውስጥ ወድቀዋል” ይላል፡፡

ኢትዮጵያውያኖቹ ዋሃቢስቶቹን እግዚአብሔርን ሰውነት በመስጠታቸው ቢከሷቸውም ዋሃቢዎች ደግሞ ኢትጵያውያኖቹን የእግዚአብሔርን ችሎታ ወስነዋል በማለት ይወነጅሏቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ እንደሆነ አጠቃላይ እስላማዊ ስምምነት ነው ማለትም (አላሁ ቃዲር አላ-ኩሊ ሻይ) ነገር ግን በዋሃቢ መጽሐፍ የሼክ አብደላን በመንቀፍ የተጻፈው መሰረት እርሱ እግዚአብሔር ጨቋኝ ወይንም ዲክታተር አይነት ገዢ ሊሆን አይችልም ሲል ከእውነት አፈንግጧል ይላል፣ ማለትም ከእግዚአብሔር ችሎታ በላይ የሆኑ ነገሮች አሉ የሚል ነው ይላል፡፡ ዋሃቢዎች አቀራረብ በጣም በታወቀው ልማዳዊ አነጋገር ማለትም “እግዚአብሔር ጨቋኝ ከመሆን እራሱን ከልክሏልን?” ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

2. የእግዚአብሔር ቃልና ዘላለማዊነቱ፡

የቁርአንን ምንጭ በተመለከተ የሚጠራጠሩ ጥቅሶችን አገላለጥ ዋሃቢዎች ለሼክ አብደላ ይሰጣሉ፡፡ እነርሱም የሚሉት እርሱ የሙታዚላ ክርክርን ይከተላል ያም ቁርአን እንደሌሎቹ ነገሮች ነው የተፈጠረው ይላል ስለዚህም እርሱ ቁርአን ዘላለማዊ አይደለም ይላል በማለት ይወነጅሉታል፡፡

ለዚህም ክስ በመመለስ ሼክ አብደላ የሙታዚላን አቀራረብ አይክድም፣ እንዲሁም የእርሱ ገለጣ ሙሉ በሙሉ ከአህል አል-ሱና ጋር የሚስማማም አይደለም፡ “የእግዚአብሔር ቃል ከእግዚአብሔር ከራሱ የተለየ ነገር አይደለም” ከሚለው አባባል ተነስቶ እርሱም የጻፈው፡ “እርሱ ጥንታዊና ዘላለማዊ ነው፣ ምንም የተወሰነ ጅማሬ የሌለው ቃል ነው፡፡ ማንኛውም ነገር የእግዚአብሔር ክፍል የሆነ የፊደልን ቃል ወይንም ድምፅን ለመውሰድ አይችልም” በማለት ነው፡፡

በሌላም ቦታ ላይ እርሱ በተጨማሪ የገለጠው ነገር፡ እጅግ በጣም የከበረው እግዚአብሔር ፍጡራኑን አይመስልም፡፡ ፍጡራኑ የሌላቸውን ችሎታዎች እርሱ አለው፣ እነርሱ የሌላቸውን ፈቃድ እርሱ አለው፣ እነርሱ የሌላቸውን እውቀት እርሱ አለው፣ እነርሱ የሌላቸውን ንግግር እርሱ አለው፡፡ እግዚአብሔር ቃላቶች ወይንም ድምፀ-ፊደላቶች የሌለውን ነገር ይናገራል፣ እርሱ እንደሰዎች አይናገርም፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር እንደዚያ (እንደሰዎች) መናገር ለእግዚአብሔርነቱ አይመጥንም የእርሱ ቃል ድምፅ ወይንም ፊደል አይደለም፡፡ ገብርኤል የእርሱን ቃል ሰምቶ ነበር የእርሱን ቃል ተረድቶት ነበር እርሱም እነዚያን ቃላት ወደ ነቢያትና ወደ መላእክት አስተላለፋቸው፡፡

3. የመቃብር ቦታዎችን መጎብኘትና ቅዱሳንን ማክበር

በሌክቸሩ እና በፋትዋው፣ ሼክ አብደላ የሚያበረታታው ተከታዮቹ ዚያራን እንዲያካሂዱ ነው፣ ይህም የአዎሊያን የቀድሞ የእስልምና ቅዱሳን ሰዎችን መቃብርን እንዲጎበኙ ነው፡፡ እግዚአብሔርን በማማለድ በኩል መድረስ (ታዋሱል) የሱፊዝም ዋና መለያ ሆኖ የዳበረ መርሆ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በሙስሊሞች ማንኛውም የሕይወት ጉዞ መካከል የታወቀ ባህል ነው፡፡ ነገር ግን ይህ በዋሃቢያዎች ዘንድ በጣም የተከለከለ ነው፣ ዋሃቢዎች ዚያራን የሺርክ መግለጫ ማለትም እንደ ፓጋኒዝም አድርገው ያዩታል፡፡ ኢብን ታይሚያ በጽሑፉ ውስጥ ብዙ ጊዜ ይህንን ልማድ የሚያያይዘው ከክርስትያን ኢትዮጵያ እንደ ምሳሌ የተወሰደና የኑፋቄ ሞዴል አድርጎ ነው፡፡ እርሱም አለ፡


“የነቢያቶቻቸውን መቃብር ወደ ፀሎት ቤታቸውነት የቀየሩት አይሁዶችና ክርስትያኖች ላይ የእግዚአብሔር እርግማን ይሁንባቸው፡፡ ይህ ተላልፎ የነበረው በአይሻ ነበር ያም ዑም ሃቢባ እና ዑም ሳለማ (ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው የነበሩት) ለነቢዩ ነገሩት በኢትዮጵያ ውስጥ ስዕሎች ስላሉበት ቤተክርስትያን በተመለከተ እርሱ (ነቢዩ) እንዲህ አላቸው፡ እነዚያ ሰዎች ከእነርሱ ፃድቃቸው አንዱ ቢሞት በእርሱ መቃብር ላይ የፀሎት ቤትን ይሰራሉ እንዲሁም እነዚያን ስዕሎች ይስሉበታል፡፡ በትንሳኤ ቀን እነዚህ በእግዚአብሔር ዓይን ፊት እጅግ በጣም የከፉ ሰዎች ናቸው፡፡

ሼክ አብደላ ኢብን ታይሚያን በመቃወም በመጽሐፉ ላይ የኢትዮጵያን ነጥብ ለማንሳት አልፈለገም (በኢትዮጵያ እስላሞች ዘንድ የመቃብር ቦታዎችን መጎብኘት በጣም የተስፋፋ ልማድ ነው) ነገር ግን ዋሃቢዎች ለሚሉት ክስ ለመመለስ፡


“ይህንን እወቁ ወደ ሞቱ ቅዱሳን እና ቅዱስ ሰዎች ለበረከት መሄድ እና መቃብራቸውን መጎብኘት የእነርሱን ምላሽ በማስተላለፉ ዕቅድ የጥንት እስላሞች የቆየ ባህል ነው፣ አል-ሳላፍ፡፡ አንዱም ማስረጃ ኢማም አህመድ ኢብ ሃንባል ነው (ዋሃቢዎች የሚከተሉት የሕግ ትምህርት ቤት መስራች) እርሱም ይህንን ደግፎታል፣ ይህም በኢብን ታይሚያ እና በተከታዮቹ የተፈጠረውን የስህተት ፈጠራ ይቃወማል፡፡ እኛ ማብራራት ያለብን እዚህ ላይ በሊቃውንቶቹ መካከል ያለው ስምምነት ያረጋገጠው ወደ ሞቱ ቅዱሳን መመለስ ሕጋዊ ወይንም ትክክል መሆኑን ነው፣ ስለዚህም የእነርሱን መቃብር መጎብኘት ሽርክ አይሆንም እንዲሁም ክልክል አይደለም፡፡”

ይህንን ጥቃት ለመቃወም በዋሃቢያ አክራሪዎች በአንዱ፣ በእነርሱ ፀረ-ሐበሻ ኮም ድረገፅ ላይ የመለሰው ኢማም አል-ሻፊ አል-አሕበሾች የሚከተሉትን የሕግ ትምህርት ቤት የመሰረተው እራሱም ይህንን ልማድ ክልክሏል የሚል ነበር፡፡ የኢትዮጵያውያኖቹ ሊቃውንት የመለሱት በአል ሻፊ የተጻፈውን ሌላ ጥቅስን በመጥቀስ ነበር በዚያም ላይ እርሱ እራሱን የገለጠው በየዕለቱ የቅዱሳንን መቃብር እንደሚጎበኝ ነበር፣ ለቅዱሳን በመፀለይ እንዲሁም ደግሞ ቅዱሳን እንደሚመልሱለትም ነበር፡፡ እንዲሁም ደግሞ እነርሱ ወዲያውኑ የጨመሩት ነገር ኢብን ሃንባል ዚያራን እንደተቀበለው የሚገልጥን ዓረፍተ ነገር ነበር፡፡

በኢትዮጵያኖቹ የሚጠቀሰው አንድ ምሳሌ ዚያራ በእስልምና ጅማሬ ላይ በእስልምና ቅዱስ ጊዜ በጣም ብዙ ይደረግ እንደነበር ነው ያም በቢላል ኢብን ራባህ ተጠቅሷል፡፡ ቢላል አል-ሐባሺ ኢትዮጵያዊው ባሪያ በአቡ በከር ነፃ የወጣው ነቢዩን ለመከተል አራተኛው ሰው ነበር (እንዲሁም የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ፍሬ)፡፡ እርሱም ቆይቶ የመጀመሪያው ሙ-ኣድሃዲን ነበር እንዲሁም ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሚጠቀስ የንፅህና ምልከት ሆነ፡፡ (በእርሱም በኩል ነበር የሚከተለው ልማዳዊ አባባል የተሰጠው “ካሊፍነት ወደ ኩዋርይሽ መሄድ አለበት ነገር ግን ሕግን የማስከበር ስልጣን ወደ ተከታዮች እንዲሁም ለፀሎት የመጥራት ሃላፊነት ወደ ኢትዮጵያውያን) በማለት የተናገረው የሚባለው እርሱ ነው፡፡ ከነቢዩ ሞት በኋላ ስለቢላል የተነገረው ነገር እርሱ መቃብሩን ይጎበኝ እንደነበረ ነው፣ ሰግዶም ድንጋዩን ይስምና ይፀልይ ነበር”፡፡

4. ገዢዎች እስልምናና ፖለቲካ

በመንግስትና በሃይማኖት መካከል ያለው ግንኙነት እንዲሁም በፖለቲካ ላይ ያለው አመለካከት በጣም ጠቃሚው ጥያቄ ነው በማለት የታሪክ ሊቃውንቱ ጆርናል ያስረዳል፡፡ ይህም ጥያቄ ያለምንም ጥርጥር በአል-አሕበሽና በዋሃቢዎች መካከል ከፍተኛውን ልዩነት እንደፈጠረ አቅርበዋል፡፡ ይህ ጥያቄ በሁለት ክፍሎች ሊከፈል ይችላል፣ የእነዚህ ግንኙነቶች ባህርይ “ከእስላም ምድር” ውጪ ባሉት አገሮችና፣ እንዲሁም በዚያ ውስጥ ባሉት አገሮች ውስጥ ነው፡፡

እስላማዊ ባልሆኑት አገሮች ውስጥ ዜግነት ላይ ሲመጣ አል-አሕበሾች የሚቀርቡት አቀራረብ በጣም ግልጥ ነው፡ ሙስሊሞች በአገሪቱ ሕግ መገዛት አለባቸው እናም በሚኖሩበት አገር ውስጥ ባለው ፖለቲካ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ አለባቸው፡፡ እነ ፕሮፌሰር ኤሪሊች የሚሉት ለዚህ መሰረታዊው ሞዴል በግልጥነት የነቢዩ የነጀሺ ታሪክ ነው፡፡ ለመጀመሪያዎቹ አማኞች ክርስትያን ነጃሺ ፃድቅ ንጉስ ነው በማለት የነገራቸው እራሱ ነቢዩ ነበር፡፡ እርሱም እራሱ ነበር ንጉሱ ጋ ጥገኝነትን እንዲጠይቁ ነግሯቸው የነበረው ክርስትያን ኢትዮጵያ ሄዳችሁ ኑሩ ይሳካላችሁም አላቸው፡፡ ጃፋር ቢን አቡ ታሊብ ነበር ከንጉሱ ጋር የተደራደረውና ለንጉሱም ወዳጅ ሆኖ የነበረው፡፡ ኢትጵያውያንን እስከተመለከትን ድረስ “እነርሱን ተዋቸው (ሙስሊሞችን)” እንደ ሙስሊሞች ይኖሩ ዘንድ፣ ሳሃባዎች የኢትዮጵያን ንጉስ ረድተዋል፡፡ በዚህ መሰረትና መንፈስ ሙስሊም ማህበሮች እስላማዊ ባልሆኑ ነገር ግን ጨቋኝ ባልሆኑ አገሮች ውስጥ በሕይወትና በፖለቲካ መሳተፍ አለባቸው፡፡ በሼክ አብደላ እይታ መሰረት ሁሉም እውነተኛ እና ፃድቅ የሆኑ የአንድ አምላክ አማኞች ሁሉ በእርግጥ ሙስሊሞች ናቸው፡፡ ስለዚህም የአይሁድ ሙስሊሞችና የክርስትያን ሙስሊሞች አሉ እናም እርሱ የሚገልጠው እንዲሁም ናጃሺ ለእነዚህ ለኋለኞቹ ሞዴል እንደነበረ ነው፡፡ ልክ እንደ ፃድቅ ንጉስ እርሱ ለእግዚአብሔር በጣም ቅርብ ነበር ስለዚህም ሙስሊሞች ሁሉ ስለ እርሱና ስለ ሰብዓዊነቱ መማር አለባቸው፡፡

የእስልምና አክራሪዎችና የዋሃቢዎች አቀራረብ ከእስልምና አገሮች ውጭ ላለው ሁኔታ እንደዚህ ዓይነት ማለትም “ሌሎችን ተቀባይ ዓይነት” አይደለም፡፡ እዚህ ላይ እንደገና መሰረታዊው ነገር ብዙውን ጊዜ ለውይይይት የሚቀርበው የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞችና ኢትዮጵያ ጉዳይ ነው፡፡ ከብዙዎችም አንድ ምሳሌ የሼክ ዩሱፍ አል-ቃራዳዊ ጉዳይ ነው፣ እርሱም ግብፃዊው የእስላም አክራሪና ስደተኛው ነው፣ እርሱም በስፋት የሚታወቀው እንደ ዋና የእስላም አክራሪነት ወቅታዊ ተደማጭነት ያለው ሆኖ ሲሆን በታህሳስ 2002 ፋትዋ ላይ የጻፈው “እስልምና ወደ ዩሮፕ እንደ ድል አድራጊ ሆኖ መመለስ አለበት በማለት ነው”፡፡ ቀጥሎም የተናገረው “እኔ የምናገረው ድሉ እና ውጊያው በአሁኑ ጊዜ መሆን ያለበት በጦር መሳሪያ ሳይሆን ርዕዮተ ዓለምን በመስበክ ነው” ብሏል፡፡ በሌላ ጎኑም አል-ቃራዳዊ በ1996 የእስራኤል የፓርላማ ምርጫ ጊዜ ሙስሊሞች እንዳይሳተፉ ከልክሎ ነበር፡፡ (ስለዚህም እርሱ በእስራኤል ውስጥ ባለው የእስልምና እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍፍልን ፈጥሮ ነበር፡፡ በእስራኤል በምርጫው ላይ የተሳተፈው ቡድን የተመሰረተው በእስላማዊ ኢትዮጵያ መሰረታዊ መርሆ “ርዕዮተ ዓለም” ላይ ነበር)፡፡ በሌላ በኩልም አል-ቃራዳዊ በአሜሪካ ምርጫ ላይ ሰዎች እንዲሳተፉ ፈቅዶ እንደነበር የታሪክ ሊቃውንቱ ዘገባ ጆርናል አቅርቧል፡፡ ቀጥሎም እርሱ በህዳር 2002 ፋትዋው ላይ፡


“አሜሪካ ከዓለም ሁሉ ውስጥ በተውጣጡ በስደተኞች የተመሰረተች አገር ናት ገና ወጣት አገር ናት፡፡ የእርሷም የባህል ሁኔታ በእስልምና ተፅዕኖ ሊደረግበት የሚችል አሁንም ክፍት ነው፡፡ እንዲሁም  ለእድገቷ አስተዋፅዖን እንዲያደርግ ለእስልምናም ዕድልን ሰጥታለች፡፡ የሁሉንም ሃይማኖት ነጻነት የምታከብር አገር ናት ካለባቸውም ችግር ውጭ እንዲኖሩ መብትን የሰጠች አገር ናት፡፡ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው መሰረት ለሙስሊሞች በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ በብቃት መሳተፋቸው አስፈላጊ ነው” ገልፆ እንደነበር አሳይተዋል፡፡

የኢትዮጵያ እስላማዊ መርሆ፣ ሼክ አል-ቃራዳዊ በመቀጠልም በጣም ጠቃሚ ትምህርት አለው በማለት የተናገረውንም እንደሚከተለው ጆርናሉ አቅርቦታል፡


“ለሙስሊሞች በዚህ አገር ውስጥ መብታቸውን ለማግኘት እንዲሁም በአገሪቱ ውስጥ ካሉት ተወላጆች ጋር ቅን የሆነ መግባባት፣ ከእኛ ዘንድ ምክክርና ስምምነት በዋና እስላማዊ መርሆዎች ላይ ሊኖረን ይገባል፣ እንዲሁም ለጥቃቅን ልዩነቶቻችን እርስ በእርስ ይቅር ልንባባል ይገባናል፡፡ የነቢዩ ፃድቃን ተከታዮች ለእኛ ከመቶ ዓመታት በፊት ምሳሌን አስቀምጠውልናል ወደ ኢትዮጵያ በተሰደዱበት ጊዜ ለመመካከር እራሳቸው ቁጭ ብለው በነበረበት ጊዜ እንዴት በጥሩ ሁኔታ መመለስ እንደሚችሉ ሲነጋገሩ፡፡ ልክ እንደ ጃፋር ቢን አቢ-ታሊብ በነጃሺ ፊት የእስልምናን መርሆዎች ሲናገር እንዲሁም በእስልምናና በጨለማ መካከል ልዩነት ሲያስረዳ እንዳደረገው ንግግር፡፡ ይህንን በማድረግ ሙስሊሞች ከሌሎች እርዳታና እርህራሄ ብቻ ሳይሆን የሚያገኙት ነገር ግን ሌሎች የእልምናን መንገድ ለመውሰድ በመምጣታቸውም መበረታታትን ያገኛሉ፡፡ በአሜሪካ ያሉ ሙስሊሞች እራሳቸውን ማስተዋወቅ ያለባቸው ከንግግር ችሎታና ከሕዝብ ግንኙነት ጋር ነው፡፡ እንደገናም ጃፋር ንግግሩን ሲያጠቃልል የኢትዮጵያወዊውን ንጉስ ከተናገረ በኋላ ያለው፡ “እኛ ወደ እናንተ አገር መጥተናል” ከነገስታቶች መካከል አንተን መርጠናል እኛ የአንተን ጉርብትና እንፈልጋለን እንዲሁም ያለግባብ ያለ ሕግ አንዳች እንዲደረግብን አንፈልግም”፡፡

አሕበሾች ትኩረትን የሚሰጡበት በነጃሺ የሰብዓዊ ወዳጅነት ላይ እንዲሁም ሌሎችም ሙስሊሞች ያልሆኑትም በሚኖራቸው ሰብዓዊ መብት ላይ ሲሆን አክራሪዎቹ ግን ትኩረትን የሚሰጡበት ነገር የእስልምናን ተግባራት በማስተባበር መብትን ማስከበር ላይ፤ እንዲሁም ተፅዕኖን ማስፋፋት እና ድልን ማግኘት ላይ ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱ ነገሮች በዓለም አቀፍ ውስጥ እየተፋተጉ እንዳሉት ሁሉ ኢትዮጵያውም ውስጥ እየተፋተጉ ነው፡፡

ልዩነቱ በጣም ከፍተኛ እንደሆነ የታሪክ ሊቃውንቱ ጆርናል ያሳያል፣ አል-አሕበሽ በሊባኖስ ፖለቲካው ውስጥ እንዲሁም ከሶርያ ባቲስቶችና ከአላዊ ግዛት ጋር ሲተባበሩ በተግባርም ታይተዋል ይላሉ፡፡ አል-አሕበሾችም የኋለኞቹን እንደ አረብ አገር አቀፋዊነት ሲያደንቋቸው የሊባኖሶቹን ደግሞ የሊባኖስ አርበኝነት ጠባቂዎች ብለዋቸዋል፡፡ ከዚያም የተነሳ አል-አሕበሾች ለዋሃቢዎች ጥቃት ተጋልጠዋል፣ ሙስሊም ያልሆኑ እና እስላማዊ ሕግን ለማስከበር ምንም ጥረት የማያደርጉትን ገዢዎችን የሚደግፉ ናቸውም ተብለው ተወንጅለዋል፡፡ (የአሁኑ ኢትዮጵያ የተቃውሞም እንቅስቃሴ ዋናው ምክንያት ይህ ብቻ ነው) የአል-አሕበሽ አቋም ግን ይህንን በማድረጋቸው እነርሱ በጥንታዊው እስልምና መንገድ እየሄዱ እንደሆነ ማለትም በ አህል አልሱና ዋልጃማ መሰረት እንደሆነና እንዲሁም የእነርሱ ሊቃውንቶች ሁልጊዜ ከእረብሻና ከዓመፅ ይልቅ በእስልምና ውስጥ የሚመርጡት መረጋጋትን እንደሆነ መግለጣቸውን የነፕሮፌሰር ኤልሪች የታሪክ ጥናት ይጠቁማል፡፡ ስለዚህም ሼክ አብደላ ይህንን አቀራረብ የገለፀው እንደሚከተለው እንደሆነ አቅርበዋል፡

“እኛም ገዢዎቻችንን እና መሪዎቻችንን ምንም እንኳን በጣም ጨቋኞች ቢሆኑ ልንንቃቸው አስፈላጊ ሆኖ አላገኘነውም፡፡ እነርሱን ከስልጣን ለማውረድና እነርሱንም አንታዘዝም ለማለት አንጣራም፡፡ እነርሱን መታዘዝ እግዚአብሔርን የመታዘዝ ዘርፍ እንደሆነ እንቆጥረዋለን፡፡ እነዚያ መሪዎች እግዚአብሔርን እንዳንታዘዝ እስካላስገደዱን ድረስ ይህንን የማድረግ ሃላፊነት አለብን”

ይህን አባባል ለማጠናከርም ሼኩ የጠቀሰው ነቢዩ ተናግሮታል የተባለውን እንደሆነ ጆርናሉ ይጠቁማል፡ “የገዢዎቹን ድርጊት የማይወድ ማንም ቢኖር እርሱ እራሱን ይግታ”፡፡ አማኞች ሊያደርጉ የሚገባቸው በጣም ጥሩው ነገር “መንገዳቸውን ለማስተካከል ወደ እግዚአብሔር መፀለይ ነው”፡፡

የዋሃቢዎች ትምህርት ግን ከዚህ የተለየ እንደሆነና በመንግስትና በሃይማኖት መካከል ምንም ልዩነት እንዲኖር እንደማይደግፍ የሊቃውነቱ ጆርናል ያሳያል፡፡ አቡ ታላል አል-ቃሲም ከዋሃቢ በጣም ጠቃሚ ሰባኪዎች አንዱ ኢትዮጵያውያኖችን በመቃወም ከብዙ ስብከቶች በአንዱ ውስጥ ያስተላለፈው ነገር እነርሱ እስልምናን እራሳቸው የተዉትን መሪዎች ይደግፋሉ በማለት ነበር፡፡ እርሱም የጠቀሰው ሼክ አህመድ ሻኪርን ነው እርሱም በጣም ታዋቂ ሙፍቲ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በብዙ እስላማዊ ማህበረ ሰቦች ውስጥ ከእስልምና ባፈነገጡና ለሻሪያ ሕግ ለማይታዘዙ በመሪዎቻቸው ላይ እምነት ያላቸው አሉ፡፡ እነዚህ መሪዎች የእስልምናን ሕግ ይንቃሉ እናም ዘመናዊነትንና ዕድገትን ይፈልጋሉ፡፡ ማንኛውም እውነተኛ ሙስሊም እንዲህ ዓይነት ተግባርን አይደግፍም እንዲሁም ደግሞ የእንደዚህ ዓይነት መሪዎች ተባባሪ ሆኖ መገኘት የለበትም፡፡ እንዲህ የሚያደርግ ማንም ቢኖር በግልፅ፣ በቀጥታ እና በጣም በግልፅ  እና በጣም ፍፁም በሆነ ሁኔታ የሚፈፅመው ነገር ቀጥተኛ የሆነ እና ፍፁም ኑፋቄ ነው” በማለት ነው፡፡

የነፕሮፌሰር ኤርሊች መደምደሚያ፡

ሊባኖስና ኢትዮጵያ አንዳንድ ታሪካዊ መመሳሰል አሏቸው በማለት የሚናገሩት የታሪክ ሊቃውንት፤ ሁለቱን አገሮች የሚያቀርቧቸው ክርስትያኖች ፖለቲካዊ መለያቸውን ለመጠበቅ የቻሉባቸው ተራራማ ምሽጎች ነበሩ፡፡ በመቀጠል የተናገሩት ሊባኖስና ኢትዮጵያ በ“እስላም ባህር” ውስጥ  “የክርስትያን ደሴቶች” ናቸው በማለት ነው፡፡ በሊባኖስ ውስጥ በ1981 እንደገና ተዘጋጅቶ እንደነበረው ክርስትያኖች በብዙ ሃይማኖታዊ አደረጃጀት ውስጥ የበላይነትን በማግኘት ተደስተዋል፡፡ ከመቶ ዓመታት በላይ ሊባኖስ የኖረችው እንደ ሃይማኖታዊ አብሮ መኖር ሞዴል ሆና ነበር፡፡ ይህ አወቃቀርና ሁኔታ በ1970ዎቹ ላይ ወደ ማብቂያው መጣ፡፡ በሃይማኖቶች መካከል ያለው የውስጥ ሚዛን እንዲሁም ደግፎ የያዘው የመመጣጠን መርሆ፣ ሁለቱም ተንኮታኮቱ፡፡ ለእስላማዊ-ክርስትያን ንግግሮች መነሳሻ የነበረችው ምድር እራሷ ለብዙ አክራሪዎች ያልተረጋጋች አገር ሆነች፡፡ “ኢትዮጵያውያኖቹ” ወይንም አል-አሕበሾች  አልፎ አልፎ ለእሳቱ ጭማሬ ሆነው ታይተዋል ወይንም እሳቱን አባብሰውታል በማለት ሊቃውንቱ ከጥልቅ የታሪክ ጥናታቸው ላይ ይጠቁማሉ፡፡ ይሁን እንጂ የእነርሱ መልእክት ለሌሎች ክፍት የሆነ እስልምና ነው፣ ይህም ብዙ ባህሎችን ለመተርጎም የሚችል፣ ማህበራዊ እና ቴዎሎጂካዊ ጉዳዮችን ለመተርጎም የሚችልና ሙስሊም ካልሆኑት ጋር በሰላም መኖር የሚችለውን እስልምና ማስፈን ነው፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የጠቀሱት በኢትዮጵያ ውስጥ የክርስትያን የበላይነት በጣም ጠንካራና በጣምም ጥንታዊ እንደነበር፡፡ ኢትዮጵያ ከአስራ ስድስት መቶ ዓመታት በላይ የክርስትያን መንግስት እንደነበረች፤ ምናልባትም የመጨረሻው የፖለቲካ ሁኔታ አጣምሮ ይዞ የነበረው መስቀልንና ዙፋንን አንድ ላይ እንደነበር፣ እንደምናውቀው ሁሉ ያ እውነታም እስከ 1974 ድረስ ቆይቶ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡ ሙስሊሞች ግማሽ የሚያክለውን የሕዝብ ቁጥር ይሆናሉ ይሉና ነገር ግን ማህበረሰቦቹ የተገለሉና በቋንቋ እና በጎሳ አንድነት እንዳልነበራቸው ይጠቁማሉ፡፡ በአገሪቱ ውስጥ እስልምና የፖለቲካ እርምጃን ለመውሰድ የተነሳሳው በጣም ጥቂት ጊዜዎች ሲሆን በክርስትና ላይ ድልን ለማግኘት የፈለገውም ብዙ ጊዜ አይደለም በማለት ይጠቁማሉ፡፡ የብዙዎችን ሙስሊሞችን አመለካከት ሲጠቅሱ “ብዙዎቹ ሙስሊሞች በተለይም ከ1880 ጀምሮ እራሳቸውን የሚመለከቱት በቅድሚያ ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ነው” ይላሉ፡፡ የእነርሱም እስልምና በእውነት የሱፊ ገፅታ ያለው ነው፡ በአብዛኛውም የተደባለቀው ክፍት ከሆነ ከሃይማኖቶች ጋር አብሮ መኖር በሚል ጥሩ አመለካከት (ጤነኛ) አመለካከት ጋር በተያያዘ የእስልምና መርሆ ነበር በማለት ጆርናላቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

እነፕሮፌሰር ኤርሊች የሚሉት የኢትዮጵያ የክርስትያን የአመራር የበላይነት የተንኮታኮተው ልክ የሊባኖሱ በተንኮታኮተበት ጊዜ ነበር፡፡ የመንግስቱ ኃይለማርያም የኮሙኒስት ግዛት 1974-1991 ስልታዊ በሆነ መንገድ የኢትዮጵያን ቤተክርስትያን ዝቅ አድርጎና አናንቆ ነበር፡፡ ምንም እንኳን የሃይማኖት እኩልነትን ቢያውጅም ሙስሊሞችን ግን አግልሏቸው እንደነበር ገልፀዋል፡፡

አዲሱ ማለትም የኢህአዴግ መንግስት ወደ አዲስ አበባ በስልጣን የመጣው በ1991 ሲሆን ኢትዮጵያን እንደ የብዙ ጎሳ ፌዴሬሽን አድርጎ ለኢትዮጵያ እንደገና አዲስን ትርጉም ሰጣት፣ በታሪክም ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙስሊሞችን በማህበረ ሰቡ ማዕከል ውስጥ እንዲገቡና በኢኮኖሚውና በፖለቲካው ወሳኝን ሚና እንዲጫወቱ የሚቹሉበትን ኃይል እንዲያዳብሩ አደረጋቸው በማለት ከታሪክ ውስጥ የሆነውን ነገር አስቀምጠዋል፡፡ በእርግጥ የኢህአዴግ መንግስት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ለሙስሊሞች ከፍተኛ ድጋፍን እና እገዛን በተለያየ መንገድ አድርጓል፡፡ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ያሉት ሙስሊሞች በአሁኑ ጊዜ ባገኙት ሁኔታዊ አዲስ ገጠመኝ በእርግጥ በጣም ተከፋፍለዋል፡፡ አብዛኛዎቹ እራሳቸውን ለማየት የቀጠሉት በቅድሚያ ኢትዮጵያዊ አድርገውና፤ በሊባኖስ እንዳሉት እንደ ሌሎቹ ኢትዮጵያውያኖች የሚመኙት ለውይይት ክፍት የሆነች፤ በእኩልነት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያን ነው ለማየት መናፈቅ እንደሆነ ይጠቅሳሉ፡፡

ሌሎቹ ደግሞ የዋሃቢያ እንቅስቃሴ አነሳሾች በመሆን የነጃሺን አገር የእስላም አገር አንድ ክፍል አድርገው ለመመልከት በጣም የሚነሳሱ እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ እነዚህ አብዛኛውን በተለይም ወጣቱን የያዙ ሲሆን የሚፈልጉት የእስልምናን ድል አድራጊነት ነው፡፡ የታሪክ ሊቃውንቱ እንደሚሉትም እነዚህ ቢያንስ በተዘዋዋሪ መንገድ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ወጣት የኢኮኖሚ ገበያ ላይ በጣም ኢንቨስት በሚደረገው የሳውዲ ኦኮኖሚ ተጠቃሚዎች ሆነዋል፡፡

ስለዚህም ይላሉ ፕሮፌሰሮቹ በሼክ ዩሱፍ አል-ሐራሪና በሼክ አብደላ አል-ሓራሪ በ1930 የተጀመረው ትግል ሙሉ ሽክርክሩን (ዙሪያውን) በመሙላት ከሐረር ጀምሮ በአረቢያ ቀጥሎ በሊባኖስ ዞሮ ወደ ኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ እየዞረ ነው ይላሉ፡፡ በእርግጥ በ2003 ሼክ ዩሱፍ ወደ ሐረር ተመልሶ ነበር፡፡ እነዚህ ሁለቱም ሽማግሌዎች የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው፡፡ በሐረር ውስጥ ያለውንና አሁንም የተጋጋለውን ትግል በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ባሉት ሙስሊሞች ዘንድ በጣም እየተዛመተ ነው፡፡ ይህም በ”ሐባሺ” እና በ”ዋሃቢ” መካከል ያለው ትንቅንቅ ነው፡፡ ሁለቱም አንዱ ሌላውን ታማኝ አይደሉም እያሉ እያጠቁና እየወነጀሉ ነው፡፡

የነፕሮፌሰር ኤርሊች ጆርናል በታሪካዊ እውነታ ላይ ተመስርቶ ያሳየው ነገር በዓለም አቀፍ እስልምና ውስጥ ያለው ትግል በትክክል የሚታየው አሁን ባለችው ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚሆነው ነገር አኳያ ነው ይላሉ፡፡ ኢትዮጵያ የሁለት እስላማዊ ርዕዮተ ዓለም መታገያ መድረክ ናት፣ አንዱ ጠላት ኢትዮጵያን እስላም ማድረግ አንደኛው ግን ኢትዮጵያ የመቻቻል ምሳሌ የምትሆን ወዳጅ ባለውለታ ኢትዮጵያ የሚል ነው፡፡

በቅርቡ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ደጋፊዎች የየትኛው ርዕዮተ ዓለም ተከታዮች ናቸው? መልሱ ግልፅ ነው፣ የዋሃቢዝምና ኢትዮጵያን እስላም ለማድረግ የሚታገለው ቡድን አባላት እንቅስቃሴ ነው፡፡ በዚህ “እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ” ዓምድ ስር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እስልምና ምን ይመስል እንደነበረ ከታሪክ ማህደር በተከታታይ ማቅረባችንን እንቀጥላለን፡፡

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ