መሐመድ እውነተኛ የእግዚአብሔር ነቢይ ነውን?

Sam Shamoun

ክፍል አንድ [ክፍል ሁለት]

በአዘጋጁ የተቀናበረ

የሚከተለው ጽሑፍ ሙስሊሞች መሐመድ የእግዚአብሔር ነቢይ ነው በማለት የሚያምኑት እምነት ትክክል አለመሆኑን የሚያሳዩ ስድስት ሐሳቦችን ይዟል፡፡ እኛ ይህንን የሚያነቡ ሙስሊሞች ሁሉንም የምንጠይቀው እነዚህን ሐሳቦች በጥንቃቄና ልባዊ በሆነ ፀሎት እንዲያነቧቸው ነው እናም ለእራሳቸው እነዚህ እውነት መሆን አለመሆናቸውን እንዲመለከቱና እንዲያስተወሉ ነው፡፡

በዚህም ጽሑፍ እውነታ መሠረት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙስሊሞችን ከጨለማ ወደ ከበረው የወንጌል ብርሃኑ እንዲያመጣቸው እንፀልያለን፡፡

ዋና ሐሳብ አንድ

መሐመድ የነቢያትን ፈለግ እንደሚከተል ተናግሯል፡-

‹እላንት ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልእክተኛው በዚያም በመልእክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ በዚያም ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ በአላህና በመላእክቱም በመጽሐፎቹም በመልክተኞቹም በመጨረሻውም ቀን የካደ ሰው (ከውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ› 4.136፡፡

‹መልክተኛው ከጌታው ወደርሱ በተወረደው አመነ ምእምኖቹም (እንደዚሁ) ሁሉም በአላህ በመላእክቱም በመጻሕፍቱም በመልክተኞቹም ከመልክተኞቹም በአንድም መካከል አንለይም (የሚሉ ሲኾኑ) አመኑ ሰማን ታዘዝንም ጌታችን ሆይ! ምሕረትህን (እንሻለን) መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው አሉም› 2.285፡፡

‹ከዚያም ወደ አንተ የኢብራሂምን ሃይማኖት ቀጥተኛ ሲኾን ተከተል ከአጋሪዎቹም አልነበረም ማለትን አወረድን› 16.123፡፡

ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና፣ እርሱም (ቁርዓን) ለአንተ ለሕዝቦችህም ታላቅ ክብር ነው ወደ ፊትም (ከርሱ) ትጠየቃላችሁ፡፡ ከመልእክተኞቻችንም ካንተ በፊት የላክናቸው (ተከታዮቻቸውን) ከአልረሕማን፤ ሌላ የሚገዙአቸው የኾኑን አማልክት አድርገን እንደ ኾነ ጠይቃቸው›፡፡ 43.43-45፡፡

‹ለዚህም (ድንጋጌ ሰዎችን) ጥራ እንደታዘዝከውም ቀጥ በል ዝንባሌዎቻቸውንም አትከተል በላቸውም ከመጽሐፍ አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ በመካከላችሁም ላስተካክል ታዘዝኩ አላህ ጌታችን ጌታችሁም ነው ለእኛ ሥራዎቻችን አልሉን ለናንተም ሥራዎቻችሁ አሏችሁ በኛና በናንተ መካከል ክርክር የለም አላህ በመካከላችን ይሰበሰባል፡፡ መመለሻም ወደ እርሱ ብቻ ነው፡፡› 42.15፡፡

 ‹እነዚህ እነዚያ መጻሕፍትንና ጥበብን ነቢይነትንም የሰጠናቸው ናቸው እነዚህ (የመካ ከሓዲዎች) በርሷ የማይክዱን ሕዝቦች ለርሷ በእርግጥ አዘጋጅተናል፡፡ እነዚህ (ነቢያት) እነዚያ አላህ የመራቸው ናቸው፤ በመንገዳቸውም ተከተል፡- በርሱ (በቁርዓን) ላይ ምንም ዋጋ አልጠየቃችሁም እርሱ ለዓለማት ግሣጼ እንጂ ሌላ አይደለም በላቸው› 6.89-90፡፡

‹ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾን እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል ከተጠራጣሪዎቹም አትኹን› 10.94-95፡፡

(ከዚህ በላይ በተጠቀሱት የቁርአን ጥቅሶች መሠረት ግልፅ እንደሆነው ሁሉ) መሐመድ ተመክሮ የነበረው ከእሱ በፊት የነበረውን ምሪት እንዲከተልና መልእክቱንም ከበፊቱ ቅዱስ መጽሐፍት ጋር እንዲያረጋግጥ ነበር፡፡

ይህም ማለት የእሱ መልክት ከእሱ በፊት ከመጡት ነቢያት መልክት ጋር ተመሳሳይ (ምንም ልዩነት እንዳይኖረው) ነው ማለት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ኢየሱስ የመገለጦቸ ሁሉ መደምደሚያ ነው፣ በመሆኑም ከእሱ በኋላ የመጡ ነቢያት ሁሉ በእሱ ስልጣን ወይንም ስም ነው መናገር ያለባቸው እንዲሁም የእሱን ዘላለማዊ ወንጌል ነው መስበክ ያለባቸው፡፡

‹ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።› ዮሐንስ 6.27፡፡

‹እናንተ ዕውሮች መሪዎች፥ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ።› ማቴ. 23.24፡፡ ‹በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥› ዕብራውያን 13.20፡፡

‹በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤› ራዕይ 14.6፡፡

‹ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፡- እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።› ራዕይ 19.10፡፡

መሐመድ የክርስቶስን መልክእት ሰለተቃረነው የመለኮት ልጅነቱንም ስለካደው፣ የእሱ መልክት የመጣው ከእውነተኛው እግዚአብሔር አይደለም፡

‹ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው። ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው።› 1ዮሐንስ 2.22-23፡፡

(ከዚህ በላይ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እንዳየነው) በእርግጥ እሱ (መሐመድ) በመጨረሻ ላይ የደረሰበት ደረጃ እግዚአብሔርን ዋሾ በማድረግ ላይ ነው፡

‹የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና። በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል። እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።› 1ዮሐንስ 5.9-13፡፡

መደምደሚያ፡- መሐመድ እውነተኛውን አምላክ ወደ ሐሰተኛ ስለቀየረው እውነተኛ ነቢይ ሊሆን አይችልም፡፡

ዋና ሐሳብ ሁለት

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው አስማትና ድግምት በእውነተኛው እግዚአብሔር አማኝ በሆኑ አማኞች ላይ ምንም ተፅዕኖ እንደማያመጣ ነው፡፡

‹በያዕቆብ ላይ አስማት የለም፥ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤ በጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል። እግዚአብሔር ምን አደረገ! ይባላል።› ዘኁልቁ 23.23፡፡ ‹ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው። ጌታ ሆይ፥ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት። እንዲህም አላቸው ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ። እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ሰለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።› ሉቃስ 10.17-20፡፡

መሐመድ ይህንን ፈተና አላለፈም ምክንያቱም አንድ አይሁዳዊ አስማተኛ አስማት አድርጎበታልና፡፡ በእርግጥ ሙስሊሞች የቁርዓን ምዕራፎች 113 እና 114 ‹የተገለጡት› መሐመድን ከዚህ እርግማን ነፃ ለማውጣት ነው ይላሉ፡፡ ይህንን በተመለከተ ሐዲት የመዘገበው ግን፡-

አይሻ የተናገረችው፡- በአላህ ሐዋርያ ላይ አስማት ተሰርቶ ነበር ስለዚህም ከሚስቶቹ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነትን ሳያደርግ ልክ እንዳደረገ አድርጎ ይቆጥር ነበር (ሱፊያን ደግሞ የተናገረው እንዲህ ዓይነትን ውጤት በማምጣቱ እጅግ ከባድ የሆነ አስማት ነበር ማለት ነው)፡፡ ከዚያም አንድ ቀን እሱ እንዲህ አለ ‹ኦ አይሻ ስለጠየቅሁት ነገር አላህ እንዳስተማረኝ ታውቂያለሽን? ሁለት ሰዎች ወደ እኔ መጡ አንደኛው በራሴ አጠገብ ሌላው ደግሞ በእግሬ አጠገብ ተቀመጡ፡፡ በእራሴ አጠገብ የተቀመጠው በእግሬ ስር ለተቀመጠው ‹ይህንን ሰው ምን ነካው?› በማለት ጠየቀው፤ ሁለተኛውም ‹እሱ በአስማት ቁጥጥር ውስጥ ነው ያለው› አለው፡፡

የመጀመሪያውም ሰው ‹በእሱ ላይ አስማትን የሰራው ማን ነው?› አለ፤ ሁለተኛውም መልሶ ‹ላቢድ ቢን አል-አሳም፤ ከባኒ ዙራይክ የሆነው ሰው ነው እሱም የአይሁዶች አጋዥ እና ግብዝ ነው› በማለት መለሰ፡፡ የመጀመሪያው ‹እሱ (አስማቱን ለማድረግ) ምን ነገርን ነው የተጠቀመው?› አለ፡፡ ሁለተኛውም ‹ማበጠሪያና በውስጡ ፀጉር የተጣበቀበት ነው› በማለት መለሰ፡፡ የመጀመሪያውም ጠየቀ ‹እሱ (ነገሩ ወይንም ማበጠሪያው) የት ነው በማለት ጠየቀ› ሌላውም የመለሰው፡ ‹በወንዴ ተምር ዛፍ የአበባው ሽፋን ውስጥ ሆኖ በዳርዋን ጉድጓድ ውስጥ በድንጋይ ስር ተቀምጧል› በማለት መለሰ፡፡ ስለዚህም ነቢዩ ወደዚያ ጉድጓድ ሄዶ እነዚህን ነገሮች አወጣቸው እና እንደሚከተለው ተናገረ ‹ያየሁት (በሕልሜ) ጉድጓድ ያ ነበር ውሃው የሚመስል የነበረው የሄና ቅጠሎች የተረጩበትና የተምር ዛፎቹ ደግሞ የሰይጣን እራስን ይመስሉ ነበር›፡፡ ከዚያም ነቢዩ በመጨመር የተናገረው ነገር፡- ‹ከዚያም ያ ነገር ከውስጥ ተወሰደ› እኔም ለነቢዩ አልኩኝ ‹ለምንድነው እራስህን በናሽራ የማትንከባከበው (የማትታከመው)?› እሱም ‹አላህ ፈውሶኛል፤ ክፉ በሕዝቤ መካከል መሰራጨቱን አልወደውም› አለ፡፡ (Sahih al-Bukhari, Volume 7, Book 71, Number 660; see also number 661)

አይሻም እንደሚከተለው ተናገረች፡- ነቢዩ አንድ ጊዜ አስማት ተደርጎበት ነበር ስለዚህም እሱ ያላደረገውን ነገር እንዳደረገው በማድረግ ማሰብንና መገመትን ጀምሮ ነበር፡፡ (Sahih al-Bukhari, Volume 4, Book 53, Number 400)::

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡-

የሕይወትን ጉዳይ ከምር ልናስብበት ይገባል፣ የምንከተለውንም ሃይማኖት ትክክለኛነት መመርመር ይኖርብናል፡፡ የእስልምና እምነት ጀማሪው ነቢይ በእርግጥ እውነተኛ ነቢይ ነበር ወይ? ብለን ለመጠየቅ ማፈር እና መፍራትም የለብንም፡፡ ከዚህ በላይ ያለው ጽሑፍና ቀጣዮች ክፍሎች መሐመድ የእውነተኛው ፈጣሪ ነቢይ መሆንና አለመሆኑን ያሳያሉ፡፡ በልበ ሰፊነት አንብቡት፣ የእውነተኛውን ፈጣሪ እምነት እየተከተላችሁ ነውን? ካልሆነ ደግሞ አሳሳቢ ነው፤ አዘጋጁ የሚመክረውና የሚያሳስበው በጥልቅና በእውነት እንድታስቡበት ነው፡፡ እግዚአብሔር መንፈሳዊውንና እውተኛ የሆነውን የራሱን መንገድ ይገልጥላችሁ ዘንድ ፀሎታችን ነው፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ አሜን፡፡


ወደ ክፍል ሁለት ይቀጥሉ።

 

የትርጉም ምንጭ: Is Muhammad a true Prophet of God?

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ