አጫጭር ዜናዎች

 

እስልምና ስለምን መድበለ ፓርቲ ሊሆን አይችልም?

ለቱርክና ለአካባቢው እንደ ዋና የዜና ምንጭ የሚቆጠረው ሑሪያት ዴይሊ ኒውስ በ June/13/2012 (ሰኔ 6, 2004) ድህረ እትሙ ላይ  BURAK BEKDIL የጻፈውን እስልምና ለምን መድበለ ፓርቲ ሊሆን አይችልም? ሲል እንደሚከተለው አቅርቦአል።

እስልምና ስለምን መድበለ ፓርቲ ሊሆን አይችልም? ለሚለው ጥያቄ አጭሩ መልስ ሙስሊሞች መድበለ ፓርቲን መደገፍ ይችላሉ፤ የፖለቲካ እስልምና ግን - በእርግጥ ለጊዜውና ለማታለል ካልሆነ በስተቀር ፈጽሞ አያደርገውም። መድበለ ሀሳቦች በእስልምና ማለትም በሃይማኖቱ ውስጥ መንገድ ሲኖራቸው በፖለቲካ እስልምና ግን የመተናፈሺያ ያህል እንኳን ቦታ የላቸውም። በእስልምና አክራሪዎችና የሃይማኖት ነጻነት በሚሹ ሙስሊሞች መካከል ያለው ዋናው የፖለቲካው ሽኩቻ ማእከል ይህ ነው፡፡ ይህ ነው እምነታቸውን በሰላም በሚያካሂዱ ሙስሊሞችና፣ እምነታቸውን በሃይል ወይም በሌላ መንገድ በሌሎች ላይ ለመጫን በሚሹ አክራሪ ሙስሊሞች  መካከል ያለው የልዩነት አስኳል ያለው እዚህ ላይ ነው።

እንድ ሙስሊም፣ ሙስሊም ነው። የእስላም አክራሪ ግን ሙስሊም ሆኖ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በነጻ ምርጫም ሆነ ወይም በንጉሳዊ ትእዛዝ እርሱ ትክክል ነው ብሎ እንደሚያምነው (ሴቷን ብዙም አይመለከትም) ሎሎች በኃይል ተገድደው እንዲያደርጉ እንዲያመልኩ  የሚያስገደድ ነው። መልካምን መውደድ ክፉን መጥላት የሚለው የማይቻለው የትዕዛዝ ስሜታዊ መስህብ ነው ሰላማዊውን ሙስሊም ሰላማዊ ያልሆነ የእስላም አክራሪ የሚያደርገው፡፡

ባለፉት 10 አመታት በዚህ አምድ ላይ ዳጎስ ያሉ ምናአልባትም በጣም አሰልቺ  ጽሑፎችን ጽፌያለሁ፣ የገዢው የፍትህና የእድገት ፓርቲ ለምን «የሙስሊም ጥያቄ ለነጻነት» ሊሆን እንደማይችል ብዙውን ጊዜ ከአሃዛዊ ማስረጃዎች ጋር አቅርቤያለሁ፣ ተሳስቼም እንደነበር በቅንነት ተስፋ አድጌያለሁ፡፡ አሁንም እኔ ተሳስቻለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ከ10 አመታት በኋላ፣ በጣም አላስፈላጊ ዳጎስ እና በጣምም አሰልቺ ከሆነው ማስረጃ ከሚጠቁመው ባሻገር በጣም ባመዛኙ እኔ አልተሳሳትኩም፡፡

የቅርብ ጊዜ አካራካሪ ጉዳይ ውርጃን መከልከል ወይም ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ የሚለው ሲሆን እንደ እውነቱ  ከሆነ እስልምና በሌላ የተከለከለ የልማድ ሰንደቅ መልክ ማንሰራራቱ ብቻ ነው፡፡ የሚያሳይ ነው፡፡  የተከለከለ ልማድ እንደ አስከባሪ ሰንደቅ በማንገብ እያንሰራራ ነው። ለአያሌ ጊዚያት በዚህ አምድ ላይ እንደጻፍኩት ሁሉ በእውነተኛ ሙስሊምና በኢስላሚስት (በአክራሪ) መካከል ያለው ልዩነት እውነተኛው ሙስሊም ከአልኮልና ከአሳማ ስጋ እርሱ እራሱ ይታቀባል፣ እስላሚስቱ ግን ሌሎችን በሃይል ከአልኮልና ከአሳማ ስጋ እንዲታቀቡ ያስገድዳል።  ይህ ነው ግልፁ እውነታ።

አንድ ሙስሊም በረመዳን ጊዜ በሰላም ይፆማል፤ እስላሚስቱ (አክራሪው) ግን ሲጋራ አጫሾችን በረማዳን ጊዜ ያጠቃል። ስለዚህ ክርክሩ በጠቅላይ ሚኒስተር ርሲፕ ታይኢፕ እርዶጋን ውርጃ (ነፍስ ማጥፋት በሱ አመለካከት) የመከልከል አዲስ ሃሳብ በምንም መልኩ የሚያስደንቅ አይደለም ምክንያቱም ይህ በ2004 ዝሙትን እንደወንጀል እንዲቆጠር ያደረገው ሙከራ ነፀብራቅ ነውና።

የሁሪየት አምደኛ አህመት ሃካን እንዳስቀመጠው «ወሊድን ለሚደግፉ፣ ውርጃን ለሚቃወሙ አክራሪ ሙስሊሞች ውርጃን በቀላሉ መከልከል አይበቃቸውም፣ እነርሱ የሚፈልጉት ሌሎች ውርጃ እንዳያደርጉ በህግ እንዲከለከሉ ነው» ልክ እንደ አስካሪ መጠጥ። እዚህ ስለውርጃ ወይም ስለአልኮል አይደለም የምንወያየው፡፡ የምንወያያው አብዛኛው ሙስሊም በሆነ አገር ውስጥ አክራሪ ሙስሊሞች አጥባቂ ሙስሊም ባልሆነውና እስልምናና በማይከተል ህብረተሰብ ውስጥ የእስልምና እምነታቸውን በህግ የማስከበር መብት ሊኖራቸው ይገባል ወይስ አይገባም በሚለው ላይ ነው። እኔ ስለ አልኮል ያነሳሁት ስለ ራሱ ስለ አልኮል ለመነጋገር አይደለም፡፡ እንደዚሁም ውርጃን በተመለከተ ያነሳው የአቶ ሃካንም ጉዳይ ስለ ውርጃ የመደገፍ ጉዳይ አይደለም፡፡

በሁለቱም ጉዳዮች ውስጥ፣ አንዳቸውም ቢሆኑ «የሙስሊም ጥያቄ ለነጻነት»ን አያሳምኑም።   በጸረ-መድበለ አስተሳሰብ ዘንድ ያለው ዋናው አመለካከት እንደሚከተለው ነው፡ «እኛ ብዛት አለን፣ የእኛ እምነት ከሁሉ የበለጠ ነው፣ ስለዚህም እኛን እንደምናደርገው ማድረግ አለባችሁ» የሚለው ደበስበስ ከሚል መለያና፣ «አለዚያ ችግር ይገጥማችኋል» የሚለው ማስፈራሪያ ነው። እስላሚስቶች ዲሞክራስን የሚወዱበት ትክክለኛ ምክንያት ያ ነው፣ “የማያምኑትን” የእነርሱ የምርጫ ቁጥር ሲበልጥ፣ እነርሱ (አብዛኛዎቹን የሚደግፉትን) ዲሞክራሲን በቁጥር አናሳ በሆኑበት ጊዜ እየጠሉት እያሉ፡፡

ለምሳሌ እስላሚስቶች በቱርክ ለብዙ ሰው (ለሰው ብዛት) ዲሞክራሲን ያቀነቅናሉ ዳሩግን ሙስሊም ብዙ ባልሆኑባቸው አገራት እንደ ዩሮፕ፣ ቻይና ወይም አሜሪካ ባሉ አገሮች ውስጥ በቁጥር አናሳ  ለሆኑ ሙስሊሞች መብት ይሟገታሉ፡፡ ይህ ደግሞ ማንም እድሜው ከስድስት አመት በላይ የሆነና እስላሚስት ዝንባሌ የሌለው ሰው እንደሚረዳው የጨቅላነት ማለትም «የእኛን የእስላሚስት  እቅድ የሚደግፍ ከሆነ የአብላጫ ድምጽ ህግን እንወዳለን» ዲሞክራሲ ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ ዲሞክራሲ አይደለም።

አለበለዚያ ግን “እኛ እምነት የለሽ የሆነውን ጨምሮ እኛ ከሁሉም እምነቶች ጋር በእኩል ደረጃ ላይ ነን” የሚሉት ግብዝ የቱርክ ገዢዎች ማዘዝ የነበረባቸው የሙዚቃና የቲያትር አዳራሾችን፣ ትልልቅ የገባያ አዳራሾችን፣ ትምህት ቤቶችንና የዩኒቨርስቲ ማደሪያ ሕንፃዎችን መጠጥ ቤቶች፣ የአይሁድ ማምለኪያ ቦታዎች ቤተክርስትያኖች እና የፀሎት ክፍሎች በህንፃዎቻቸው ውስጥ ሁሉ ለሚፈልጉት እንዲኖራቸው ነበር፡፡ ይህም ለሱኒ ሙስሊሞች ከተሰጣቸው የመፀለያ ክፍሎች በተጨማሪ ነው፣ ይህ ደግሞ ሁሉም የቱርክ ዜጋ ያለምንም አድልዎ በአደባባይ እንክብካቤ እንዲደረግለት ከፈለጉ ነው፡፡

መድበለ እስላሚዝም የማይጥም ቅዥብርብር ነው፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ

ይህ በቱርክ ዋና ጋዜጣ ላይ የቀረበውና እራሱ ሙስሊም በሆነ አምደኛ የቀረበው የፖለቲካዊ እስልምና ትንተና ለብዙዎች ትምህርት የሚሰጥ ነው፡፡ አምደኛው BURAK BEKDİL ያሳየው እስልምና ፖለቲካዊ ከሆነና አመራርን ከያዘ መድበለ ፓርቲ ሊሆን በፍፁም አይችልም ነው፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ አክራሪዎች መድበለ ፓርቲ ሊሆን እንደሚችልና የሌሎችን እኩልነት እንደሚደግፍ ለጊዜው ማለትም ስልጣንን እስከሚይዙ ድረስ ሊናገሩ ይችላሉ ሲናገሩም ይሰማሉ፣ እውነቱ ግን ከንግግር የራቀ ነው የሚል ሆኖ BURAK BEKDİL የሰጠው የመደምደሚያ አጭር አረፍተ ነገር አስገራሚ ነው፡፡ መድበለ እስላሚዝም ካለ፣ ሊኖር አይችልም እንጂ፣ ነገር ግን ካለ ሊሆን የሚችለው ለማንም የማይጥም ደግሞም የማይጠቅም የእርስ በእርስ ተቃርኖ (ቅዥብርብር) ብቻ ነው፡፡

ከአጠቃላይ የዓለም ሁኔታ እንደምንረዳው ከሆነ የሃይማኖት ፖለቲካ ለሰዎች ውስጣዊ ሕይወት ችግርና ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ የሚያሳድረው ተፅዕኖ አደገኛ መሆኑን ነው፡፡ ታዲያ ምን ይሻላል? መልሱ ወደ እውነተኛው እግዚአብሔር መንገድ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መመለስና ለሰዎች ሰብዓዊ ጥቅምና ሰላም የሚሆነውን በግልም በጋራም ማራመድ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይርዳን አሜን፡፡

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ