የቁርአን እርስ በእርስ ተቃርኖ

ከማርያም ጋር የተነጋገሩት መላእክት ስንት ናቸው?

Jochen Katz

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ እውነታና ክስተት ለእውነተኛ አምላክነቱ ትክክለኛና ዋና ማስረጃ ነው ነገር ግን ብዙዎች በክስተቱ ሁኔታ ላይ ቅራኔ የሚመስሉ ነገሮችን በመፈላለግ የእሱን አምላክነት ትክክል አይደለም ለማለት ብዙ ጥረቶችን ያደርጋሉ፡፡ ሙስሊሞች የጌታን ስቅለት ስለሚክዱ የጌታንም ትንሳኤ በትክክል ይክዳሉ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅራኔዎች ተብለው ከተያዙትና ተወዳጅ ከሆኑት ውስጥ እና በሙስሊሞችም በከሃዲዎችም የሚቀርቡት የማርቆስ ወንጌል 16 እና ማቴዎስ 28 ይገኙባቸዋል፡፡ ሴቶቹ በጌታ ኢየሱስ መቃብር አጠገብ አንድን መልአክ አገኙና አነጋገሩ በክፍሉ የምናነበውም አንድ ብቻ መልአክን እንዳገኙ ነው፡፡ ነገር ግን በሉቃስ ወንጌል 24 እና በዮሐንስ 20 መሠረት ደግሞ በግልፅ ተጽፎ የምናገኘው እነሱ ሁለት መላእክትን እንዳነጋገሩ ነው፡፡ እዚህ ላይ በእግዚአብሔር ስለማያምኑት (ከሐዲዎች) አባባል ምንም ባያሳስበንም ይህንን ጥያቄ ሙስሊሞች እያነሱ መጮኻቸው ግን እጅግ የሚያስገርም ነገር ነው፡፡ የሚገርመውም ነገር በቁርአናቸው ውስጥ ያለውንና ምንም መልስ ሊሰጡበት የማይችሉትን የእርስ በእርስ ተቃርኖዎች አለማወቃቸው ነው፡፡

ማርያም ጌታ ኢየሱስን ስትወልድ በመልአክ ለእርስዋ መልክት የተነገረባቸው ቢያንስ ሁለት ቦታዎች በቁርአን ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነዚህም፡-

አንደኛ ‹መላእክትም ያሉትን (አስታውስ)፡- መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ አነጻሽም በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሸ› ቁርዓን 3.42. እንዲሁም ‹መላእክት ያሉትን (አስታውስ) ... ...› 3.45፡፡

ሁለተኛ ‹ከእነሱም መጋረጃን አደረገች መንፈሳችንንም (ጂብሪልን) ወደ እርሷ ላክን ለርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት፡፡ .... .... እኔ ንፁህን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ የጌታሽ መልክተኛ ነኝ አላት›፡፡ ቁርአን 19.17-19 የሚሉት ናቸው፡፡

በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት ምን ያህል መላእክት ናቸው ወደ ማርያም የመጡት? በ3.42 እና 45 መሠረት መላእክቶቹ በብዙ ቁጥር ነው የተጻፉት ማለትም በአረብኛ ቋንቋ የብዙ ቁጥር አተረጓጎም ከሦስት ያላነሱ መላእክት እንደነበሩ ነው፣ ነገር ግን አሁንም በአረብኛ አካሄድ አራት መላእክት ወይንም ሺ ወይንም ሚሊዮንም ማለትም እንኳን ሊሆን ይችላል፡፡ በ19.18 ላይ እንደተገፀው ማርያም ከአንድ መልአክ ጥበቃን የፈለገችው ለምንድነው? ከአንድ መልአክ ጋር ብቻ የተነጋገረችው ለምንድነው? ሌሎቹ ልክ እንደ ሰዎች ስለነበሩና ምንም ስላላስፈሯት ነበርን?

በእርግጥ ይህ የቁርአን ችግር ክርስትያኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አላቸው ከሚባለው ችግር ለመፍታት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ማርያም ያነጋገረችው አንድ መልአክን ስለነበርና  በዙሪያዋ እጅግ ብዙ ኖረው ከአንድ ጋር ብቻ መነጋገሯ ግራ የሚያጋባ ስለሚሆን ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መላአክቱ በቀጥታ በሴቶቹ ሲጠሩ አንመለከትም፡፡ ስለዚህም አንድ ብቻ መልአክ ነበር የነበረው ለማለት ማስረጃ ሊኖረን አይችልም፡፡ ማርቆስና ማቴዎስ አንድ መልአክ አድርገው የተናገሩት ምናልባትም ዋነኛው አንዱ መልአክ ስለሚሆን ሲሆን ዮሐንስና ሉቃስ ግን ሁለት በማለት ተጨማሪ ግልጥነት የሰጡት መሆኑን ነው፡፡

ይህም ልክ አንድ ሰው አንድ ፕሬዜዳንትን ወይንም ምክትል ፕሬዜዳንትን ካገኘ በኋላ እቤት መጥቶ ዛሬ ፕሬዜዳንቱን አየሁ እንደሚለው ነው፡፡ በዚህ ሰው ንግግር ውስጥ ብዙ ሰዎችንና ምክትል ፕሬዜዳንቱን አልተገናኘም የሚል ምንም ነገር የለም፡፡

እንደዚህ ዓይነት ሎጂካዊ መግለጫዎችን ስለ ቁርአን ለመቀበል ደስተኛ ነው የምሆነው ነገር ግን የቁርአኑ ምንም ሎጂካዊ የሆነና ሊያሳምን የሚችል አይደለም፡፡ ማርያም ሁለቴ ባደረገችው ንግግር ውስጥ በቁርአን ለምን ሁለቴም አንዱን መልአክ ብቻ አነጋገረች ሌሎቹንስ ለምን አልፈራቻቸውም ለምንስ አላነጋገረቻቸውም የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ሙስሊሞች መሞከር ይኖርባቸዋል፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

በጌታ በኢየሱስ ትንሳኤ ዙሪያ የሚነገሩት የሙስሊሞች ልዩ ልዩ ገለጣዎች ታሪካዊም ሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ የሌላቸው ናቸው፡፡ የጌታ ኢየሱስ ትንሳኤ በትክክል የሆነ የታሪክ መሠረታዊ ክስተት እንዲሁም ለሰዎች ልጆች መዳን የተከናወነ አስፈላጊ የእግዚአብሔር ስራ ነው፡፡ አንድ ሰው የጌታ የኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ ትክክለኛ ምክንያት ሊገባው የሚችለው መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ሲያነብና ሲረዳ ነው፡፡ ክርስትያኖች ከሞት በኋላ ትንሳኤ አለ የሚሉት እና በትክክልም በትንሳኤ የሚያምኑት ጌታቸው ከሞት መነሳቱ እርግጠኛ በመሆኑ ነው፡፡ አንባቢዎች ከሞት በኋላ ሕይወት አለ በማለት የምታምኑ ከሆነ ምክንያታችሁና ማስረጃችሁ ምንድነው?

ጌታ ኢየሱስ እኛ በኃጢአታችን መቀጣት የነበረብንን ቅጣት ተቀብሎ በመስቀል ላይ ዋጋን በመክፈሉ ያመኑና ንስሐ ገብተው በእሱ በኩል ወደ ሕያውና ቅዱስ እግዚአብሔር የሚመጡት ተቀባይነትን በማግኘት የትንሳኤን ሕይወት አግኝተው በመንግስተ ሰማይ ውስጥ ይገባሉ፡፡ እግዚአብሔር ወደዚህ እውነት እንድትመጡ ይርዳችሁ፡፡ 

 

የትርጉም ምንጭ: Qur'an Contradiction:How many angels were talking to Mary?

 

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ