ቁርአን ባጠቃላይ ምን ያሳያል?

 M.J Fisher, M.DIV

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

መግቢያና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ንፅፅር

ከዚህ በፊት በዝርዝር እንደተገለፀው መሐመድ ከመዲና ካመለጠ በኋላ ሰዎች ለቁርአን ያላቸው አክብሮት በጣም እያደገ መጣ፡፡ የእሱም ተከታዮች ያምኑ የነበረው መሐመድ ታማኝነቱን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እየገነባው እንደመጣ አድርገው ነበር፡፡ እሱንም ያከብሩት የነበረው ልክ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ነቢይ፤ ማለትም ልክ እንደ አብርሃም እንደ ሙሴና እንደ ዳዊት እኩል አድርገው ነበር፡፡ እነሱም ያምኑ የነበረው የቁርአን ህግጋቶቹ ይዘት በጣም ከፍተኛና ግጥሙም ውብ እንደነበሩ አድርገው ሲሆን ይህም በጊዜው ከነበሩት ከጣዖት አምላኪዎች ግጥም በጣም የላቀ አድርገው በመቁጠር ነበር፡፡

መሐመድ ከሞተ ከአስርት ዓመታት በኋላ እሱ በቃል ለተናገራቸው ጥቅሶች እራሳቸውን ሰጥተው የነበሩት እንዲሁም በቃላቸው አጥንተው የነበሩት ብዙዎቹ ለእስልምና እምነት ያደርጉት በነበረው ጦርነት ላይ ሞቱ፡፡ በመሆኑም በቃል ይነገሩ የነበሩት ጥቅሶች ይጠፋሉ በሚል አስተሳሰብና ስጋት ኮሚቴ ተቋቋመና የመጀመሪያውን ቁርአን አሰባሰቡትና ታትሞ ተሰራጨ፡፡ ይሁን እንጂ ችግሮች ተፈጠሩ፡፡ የመሐመድ ተከታይ ካሊፍ ኡትማን (ኡስማን) የቁርአኖቹ ቅጅዎች እርስ በእርስ የማይማሙ መሆናቸውን አረጋገጠ፡፡ የተሰራጩት ጽሑፎችም አለመስማማት ግልጥ መሆን ለእስልምና ትልቅ እንቅፋት ነበር፡፡ ስለዚህም ኡስማን ጥቂት መሪዎች ያሉበትና ቅጂዎቹን የሚያመሳስል ኮሚቴ መሠረተና ቅጅዎቹ እንዲስማሙ ከተደረገ በኋላ፤ ሌሎቹ ቅጂዎች በሙሉ ተሰብስበው እንዲቃጠሉ አደረገ፡፡

በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያለው የስድሳ አንድ ጥቅሶች እውነታ ብዙ ነገሮችን ይገልጣል፡፡ እነዚህ በመሐመድ በቃል የተነገሩት ጥቅሶች ስለ ቁርአን እጅግ ታላቅ ምስጢርን ይገልጣሉ፡፡ ቁርአን እራሱ ከመጻፉ በፊት ከተጻፈውና ከተጠናቀቀው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንደሚስማማ ይናገራል እንዲሁም እስላሞች በመጽሐፍ ቅዱስም በቁርአንም እንዲያምኑ ያዛቸዋል፡፡ እንዲሁም ፍፁም የሆነ በሰማይ ካለው ማኅደር (ታብሌት) ላይ የተቀዳ የአረብኛ ትክክለኛ ቅጂም እንደሆነ እና በሥነ ጽሑፍ ይዘቱም ምንም ተወዳዳሪ የሌለውና ስህተትም እንደሌለበት ቁርአን ስለራሱ ይናገራል፡፡ ቁርአን የሰዎች ልጆችን ለማስደነቅም ድብቅ ነገሮችን እንደሚገልጥም ይናገራል፡፡ ለምሳሌም ያህል 19 መላእክት ሲዖልን እንደሚጠብቁት ቁርአን ይናገራል 74.26-31፡፡ ስለዚህም ዜና ክርስትያኖች ተደንቀው በቁርአን እንዲያምኑ በከፍተኛ ደረጃ ይጠብቃል፡፡

የመሐመድ ጊዜ የነበሩ ሰዎች በቁርአን ያለማመናቸው ምክንያት የሚገኘው በራሱ በቁርአን አንቀፆች ውስጥ ነው፡፡ ለምሳሌም ያህል አንዳንድ "መገለጦች" በሚቀየሩበት ጊዜ ቁጥሮቹ መገለጡ ከእግዚአብሔር የመነጩ ያለመሆናቸውን ጥርጥርን ያስከትል ነበር፡፡ የፀሎት አቅጣጫ ከኢየሩሳሌም ወደ መካ ተቀየረ ለዚህም የተሰጠው መግለጫ አላህ ይህንን መቀየር የሰጠው በቁርአን ላይ ለተሰጠው የእግዚአብሔር ቃል ማን ያምን እንደሆነ ለመፈተን እንደሆነ ተነገረ ስለዚህም ያ መለወጥ አስፈለገ ይላል፡፡ ሌላው ምሳሌ ደግሞ መሐመድ ስለ አላህ ሴቶች ልጆች መከበር የተቀበለውና የተናገረው ጥቅስ አለበት፡፡ እነዚህ ጥቅሶች ተደምስሰው መሐመድ የተቀበለው ሰይጣናዊ ጥቅሶች ናቸው በሚል ሌላ ጥቅሶች እንዲተኩ ተደረገ እና ቆይቶ ተቀየረ፡፡ ለስልታዊ ወቅታዊ ንግግር እነዚህ ሰይጣናዊ የተባሉት ጥቅሶች የጣዖት አምላኪዎችን አስደስተው ነበር፡፡

ቁርአን በመሐመድ ጊዜ የነበሩ ሰዎች ለምን እንዳልተቀበሉት እጅግ ብዙ ምክንያቶችን ይደረድራል፡፡ አንዳንዶች እስልምናን ያልተቀበሉት መሐመድ ጥቅሶችን ተቀብሎ ይናገር በነበረበት የአነጋገር መንገድ ምክንያት ነበር፡፡ ማለትም እሱ እጅግ በጣም የሰይጣን ልክፍት እንደያዘው ሰው ይመስል ስለነበር ነው፡፡ ሌሎቹ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያውቁትና ያስተዋሉት ደግሞ መሐመድ የአረብን የአይሁድን እና የክርስትናን ተረቶች (ልማዳዊ ንግግሮች) ልክ ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን አድርጎ ይናገራቸው እንደነበረ ነው፡፡ ከነዚህም ነገሮች የተነሳ ማለትም ቁርአን ካለው ይዘት የተነሳ በጊዜው የነበሩ ብዙዎች አልተቀበሉትም ነበር፡፡ እስኪ ከዚህ ቀጥሎ ቁርአን ስለዚህ የሚናገረውን ከራሱ እንመልከት፡-

ቁርአን የሚከተለውን ይናገራል

ሰይጣናዊ ጥቅሶች፡- መሐመድ አንዳንድ ከሰይጣን በትክክል የመጡ ጥቅሶች የቁርአን ክፍሎች እንደሆኑ ይናገራል ነገር ግን ከእሱ በፊት የመጡ ሁሉ ነቢያት ችግር ስለነበረባቸው ይህ ምንም ችግር የሚፈጥር ነገር አይደለም፡፡ ስለዚህም ሰይጣናዊ ጥቅሶቹ ተወግደዋል፡፡ የሰይጣናዊ ጥቅሶች ዓላማ የማያምኑትን ለመፈተንና በመካከላቸውም መከፋፈልን መፍጠር ሲሆን ይህም ቁርአን ለአማኞቹ ትክክል የመሆኑ ምልክት ነው (22፡52፣ 53)፡፡ ‹ከመልክተኛና ከነቢይም በፊት አንድንም አልላክንም ባነበበ(ና ዝም ባለ) ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ላይ (ማጥመሚያን ቃል የሚጥል ቢኾን እንጅ ወዲያውም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል ከዚያም አላህ አንቀፆቹን ያጠነክራል አላህም ዐዋቂም ጥበበኛ ነው፣ ሰይጣን የሚጥለውን ነገር ለነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሺታ ላለባቸው ልቦቻቸውም ደረቆች ለኾኑት ፈተና ሊያደርግ (ይጥላል) በዳዮችም ከውነት በራቀ ጭቅጭቅ ውስጥ ናቸው›፡፡ ሰይጣናዊ ጥቅሶቹ ተወግደዋል (ተሰርዘዋል) እናም በተሻለ ጥቅስ ወይንም ደግሞ በተመሳሳይ ጥቅስ ተተክተዋል ‹ከአንቀፅ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን አላህ በነገሩ ሁሉ ከሃሊ (ቻይ) መኾኑን አታውቅምን?› 2.106፡፡

የቁርአን እርግጠኝነት ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፡- ከቁርአን አንዱ እንዲሆን መሐመድ ከሰጠው ከጥቅሶች አንዱ በሌላ ጥቅስ ሲተካ ሙስሊም ያልሆኑት ይወስኑ የነበረው እሱ ነቢይ ነኝ ይል የነበረ አታላይ እንደሆነ ነበር (16፡101) ‹በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ነገር ዐዋቂ ነው፤ አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም ይላሉ በውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም›፡፡

ለውጥ ጥርጥርን አስከትሎ ነበር፡- ሞኝ የሆነ ሰው የመሐመድ የቀደመ ትምህርቱ ለምን በአዲስና በሌላ ተቀየረ በሚለው ይደነቅ ይሆናል (የስግደትን አቅጣጫ አንድ ሙስሊም ሲሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም ቀጥሎም ወደ መካ መቀየሩን በተመለከተ ጊዜ)፡፡ ለእንደዚህ አይነት ሞኝ ተጠራጣሪዎች መልሱ የመጀመሪያው ቃል የተገለጠው ከፍተኛ (ከባድ) መፈተኛ እንዲሆን ነበር፡፡ ይህ ለውጥ (በቁርአን ውስጥ) የተደረገው ሙስሊም ሆነው የሚቀሩትን ሰዎች እና ከዚህ የተነሳ ከእስልምና የሚወጡትን ለመለየት ነበር፡፡ እሱም እውነተኛ እስላሞች ይቆሙበት ዘንድ ታላቅ መፈተኛ ነበር 2.142፣143›፡፡

የተነገሩና የተረሱ ጥቅሶች፡- በመሐመድ የተነገሩት ጥቅሶች በሙስሊሞች መደገም ነበረባቸው ይህም እነሱ ማናቸውንም (አንዳቸውንም) እንዳይረሱዋቸው ለማድረግ ነው፡፡፤ ይህም አላህ እንዲረሱዋቸው ከሚፈልገው ጥቅሶች በስተቀር ነው (87፡6፣7)፡፡

የሰማዩ የመጽሐፍት እናት (ማኅደር)- ቁርአን በሰማይ ላይ ባለ የተጠበቀ ገበታ (ምናልባትም ጽሑፍ ያለበት ድንጋይ በሰማይ) 85.21፣22 ነው፡፡

ዝርዝር ማብራሪያ፡- መጽሐፍ ቅዱስ የታሪክን ሁሉ ዝርዝር ክስተት ይናገራል በማለት ቁርአን ይመስክራል (በታሪክ የሆነውን ነገር ሁሉ) ወይንም የሁሉንም ነገር ገለጣ ይሰጣል 12.111፡፡

ትምህርት ተሰጠው፡- የማያምን ሰው መሐመድን ቁርአንን እንዲያደራጅ እየረዳው ነው ተብሎ ተከሶ ነበር 16.103፡፡

በአጋንንት ተይዟል፡- ሙስሊም ያልሆኑቱ በዓይናቸው በመሐመድ ላይ በማሾፍ (በመጣቀስ) ‹ምንም አያጠያይቅም እሱ በአጋንንት ተይዟል ብለዋል› 68፡51፣ 25፡8፡፡

የሃሰት ነቢይ፡- ሙስሊም ያልሆኑት የተናገሩት መሐመድ እራሱ ነው እነዚህን ቃላት እራሱ ያመነጫቸው ይህንንም ያደረገው በሌሎች እርዳታ ጭምር ነው ብለው ነበር 46.8፣ 52.33፣ 25.4፡፡

እብድ ነው፡- ሙስሊም ያልሆኑት መሐመድ እብድ ነው ይሉ ነበር 68.2፡፡ የጣዖት አምላኪዎችም መሐመድ ምንም ተዓምራትን ስላላደረገ በመሐመድ ቃል ብቻ በማመን ጣዖት አምልኮአቸውን እንደማይተዉ ተናግረዋል፡፡ እነሱም የወሰኑት የእነሱ አማልክት እብድ እንዲሆን እንደረገሙት አድርገው ነው (በዕብድነት እንደረገሙት ነው) 11.53-54፡፡

ተረቶች፡- ሙስሊም ያልሆኑት የቁርአንን ይዘት የተቃወሙት በአገሪቱ ውስጥ የተለመዱትን አሮጌ ተረቶ በቁርአን ውስጥ እንደታሪክ ሆነው ተጽፈው (ቀርበው) ስላገኟቸው ነው፡፡ አንድ ሰው ረጅም ጊዜ ወስዶ መሐመድ እነዚህን እንዲያጠናቸው እረድቶታል እነዚህንም ተረቶች አስተምሮታል ብለውም ያምኑ ነበር 83.13፡፡

አስራ ዘጠኝ መላእክት፡- አስራ ዘጠኝ መላእክት ሲዖልን ይጠብቃሉ! ይህ አስደናቂ የሆነ መገለጥ ነው ስለዚህም እነዚያ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምኑት አሁን በቁርአን ያምኑ ይሆናል ስለዚህም የእስላሞች እምነት ይጠናከራል፡፡ (በእምነታቸው ይጠናከራሉ)፡፡ በተመሳሳይም መንገድ የመላእክት ቆጠራ ለማያምኑት የማሾፊያ ነጥብ ይሆንላቸዋል፡፡ ለማያምኑት ሞኝነት ይመስላቸዋል ይህም አላህ አንዳንዶችን የሚያሳስትና አንዳንዶችን ደግሞ የሚመራ ነውና፡፡ 74.26-31፡፡

የጣዖት አምላኪዎች ፈተና፡- ጣዖት አምላኪዎች የሚሉት ቁርአን የሰው ፈጠራ መሆኑን ነው፡፡ እነሱንም የምንጠይቃቸው በአምላኮቻቸው እርዳታ የእሱን የመሰለ አንድ ምዕራፍን እንዲያመጡ ነው 10.38፡፡

የመሐመድ ዘመን ብዙ ገጣሚዎች፡- በዘመኑ ልዩ፣ ልዩ ግጥም ገጣሚዎች ያለምንም ዓላማ በየሸለቆው ውስጥ ይዘዋወሩ ነበር፡፡ እነሱም ስህተትን ሊያምኑ የሚችሉ ተከታዮችን ይሰበስቡ ነበር፡፡ ገጣሚዎቹም የማያደርጉትን (እራሳቸው የማይለማመዱትን) ነገር ያስተምሩ ነበር፡፡ 26.224-226፡፡

የማይለወጥ ነው፡- የአላህን ቃል ማንም መለወጥ አይችልም 18.27፡፡

መጽሐፍ ቅዱስን ያረጋግጣል፡- በአረብኛ ቋንቋ የተጻፈው ቁርxን ከእሱ በፊት ከተጻፈውና ለሰዎች ሁሉ መመሪያና በረከት ይሆን ዘንድ ከተሰጠው የሙሴ መጽሐፍ ጋር ይስማማል እንዲሁም እርሱን ያረጋግጣል 46.12፡፡ በቁርxን ውስጥ ያሉት ታሪኮች ሁሉ በሰው የተፈጠሩ ተረቶች ሳይሆኑ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያረጋግጡና ትክክል ነው የሚሉ ናቸው 12.111፡፡ ቁርxን ከአላህ ዘንድ የተሰጠ ነው ስለዚህም ነው ከእሱ በፊት የመጣውን መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ የሚገልፀው 10.37፡፡ አንተ መሐመድ የቁርxንን ታማኝነት የምትጠራጠር ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡትን ሰዎች መጠየቅ ይኖርብሃል ማለትም ከአንተ ሕይወት በፊት የተገለጠውን ነው 10.94፡፡ ከዚህ በፊት በነበሩት ሐዋርያት ያልተገለጠ ምንም አዲስ ነገር በቁርxን ውስጥ አይኖርም 41.43፡፡

ቁርአን በሰማይ፡- ቁርአን የተሰጠው በአረብኛ ነው ስለዚህም በቀላሉ ሰዎች በትክክል እንዲረዱት ነው እንዲሁም የእሱ እናት መጽሐፍ በአላህ ፊት ነው ያለው እሱም በጣም የከበረና በጥበብም የሞላ ነው 43.4፡፡

በፍፁም አላለቀም፡- የአላህ ቃል መጽሐፍ መጻፍ በፍፁም ሊያልቅ አይችልም ይህም የምድር ዛፎች ሁሉ ብዕር ቢሆኑና ባህር በሙሉ ቀለም ሆኖ ሌሎች ሰባት ባህሮች እሱን ቢተኩትም እንኳን ነው 31.27፡፡

ጅኒዎች በሩቅ ተጠብቀዋል፡- ቁርአን ሲነበብ እንዳይሰሙ ጅኒዎች በሩቅ ተጠብቀዋል፡፡ እነሱም ቁርአን ሲነበብ በፍፁም ሊሰሙ አይችሉም 26.212፡፡

ጅኒዎች ተለውጠዋል፡- አንዳንድ ጅኒዎች ወደ ሰማይ በርረው በመሄድ ቁርአን የሚነበብበት ቦታ ተገኝተዋል፡፡ እነሱም በእነሱ ላይ የሚወረወረውን የሚንበለበለውን ፍላፃና እና በራሪ ኮከብ አይተዋል በሰማይ የሚደረገውን የቁርአን ንባብ እንዳይሰሙ ለመጠበቅ፡፡ እነሱም የሰሙት መልክት አላህ አንድ እንደሆነና ሚስትም ልጆችም የሉትም የሚል ሲሆን በመልእክቱ እንዳመኑበት ነው፡፡ እነሱም ሙስሊሞች ሆነዋል፡፡ ስለዚህም አንዳንድ ጅኒዎች በእስልምና አማኞች ሆነዋል፡፡ ሌሎችም ደግሞ ለሲዖል እሳት ነዳጅ ሆነዋል 72.1-15፡፡

የመርፌ ዓይን፡- ቁርአንን የሚክዱት እነዚያ ወደ ገነት ደጃፍ ሊደርሱ አይችሉም ይህም ግመል በመርፌ ዓይን ውስጥ እስከምታልፍ ድረስ ነው 7.40፡፡

ምንም ስህተት የለበትም፡- ቁርአን ብቻ ነው ከቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ምንም ስህተት የሌለበት 39.23፡፡ እሱም የተጻፈው በአረብኛ ሲሆን ከማንኛውም ስህተት ነፃ ነው 39.28፡፡ እሱም ከማንኛውም እርስ በእርስ ቅራኔ ነፃ ነው 4.82፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስና በቁርአን ማመን፡- እውነተኛ አማኞች ማለት በቁርአንና በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምኑት ናቸው 2.4፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡-

ከዚህ በላይ ስለቁርአን ያየናቸው ነገሮች አስገራሚዎች ናቸው፡፡ ስለ ቁርአን ማወቅ የሚገባንን በመጠኑ እንድናውቅ ይረዱናል፡፡ ቁርአን ስለ እራሱ ሲናገር ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ መጽሐፍ እንደሆነና ደግሞም ምንም ቅራኔ እንደሌለበት ነው፡፡ ቁርአን ከእግዚአብሔር ከመጣ ማለትም የእግዚአብሔር እውነተኛ መልእክት ከሆነ አንድ አንባቢ ምን መጠበቅ ይኖርበታል? እንደ አንድ አንባቢ ሁላችንም ልንጠብቅ የሚገባን ስለ እግዚአብሔር ትክክለኛ ባህርይ እንዲሁም የሰው ልጆች ከእሱ ጋር እንዴት ሊታረቁ እንደሚችሉ በእውነት ማስረዳትን ነው፡፡

ይሁን እንጂ ቁርአን ይህንን አያደርገውም፣ የሰው ልጆች እጅግ በጣም የሚያስፈልጋቸውን የዘላለም ሕይወትን መንገድ በግልጥ አያሳይም፣ ከዚህም የተነሳ ብዙዎች ከእግዚአብሔር መንገድ እንዲስቱ ምክንያት ሆኗል፡፡

የዚህ ድረ ገፅ አገልጋዮች ለሙስሊሞች ወገኖቻቸው ጥሪ የሚያቀርቡት ስለ ግል ሕይወታቸው በጣም እንዲያስቡበት ነው፡፡ ሃይማኖተኛ መሆን አንድ ሰው ዘላለማዊ የሆነ የሕይወትን ለውጥና የመንግስተ ሰማያትን ሕይወት እንዲያገኝ አይረዳውም፡፡ የመንግስተ ሰማይ ሕይወት ሊገኝ የሚችለው ምንም ቅራኔ በሌለው በቅዱስ እግዚአብሔር ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት፣ እራሱ እግዚአብሔር ወደ ገለጠው እውነት በመምጣት ነው፡፡

ስለዚህም የጌታን ቃል መጽሐፍ ቅዱስን እንድታገኙና እንድታነቡ በትህትና እንጋብዛችኋለን፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት በጥሞና አስቡበት ከዚያም ወደ እውነተኛው እግዚአብሔር በፀሎት ቀርባችሁ ንስሐ በመግባት በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል እንዲቀበላችሁ ለምኑት ይቅር ይላችኋል በመንፈስ ቅዱስም አማካኝነት ሕይወታችሁን እርሱ እራሱ ይለውጠዋል በውስጣችሁም በትክክል መለወጣችሁን ያረጋግጥላችኋል የዘላለም መንግስቱንም ወራሾች ያደርጋችኋል፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ አሜን፡፡

 

የትርጉም ምንጭ: The Qur'an,  Chapter 17 of "A Topical Study of the Qur'an From a Christian Perspective" by M.J Fisher, M.Div

ሙሉ መጽሐፉ በአማርኛ: ርእሳዊ የቁርአን ጥናት በክርስትና አይን ሲመረመር

 

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ