አስመሳይ ጥቅሶች

M. J. Fisher, M.Div.

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

በአሁኑ ጊዜ ሙስሊሞች የመጽሐፍ ቅዱስን ታማኝነት የሚቃወሙበት ምክንያት በአንድ በኩል በቁርአን ውስጥ ያሉትንና በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የተሰበሰቡትን ሃያ ሁለት ጥቅሶች በተሳሳተ መንገድ ስለተገነዘቧቸው ነው፡፡ እነሱም የሚያስቡትና የሚያስተምሩት አይሁዶችና ክርስትያኖች በእግዚአብሔር የተሰጠውን ቃል የራሳቸውን ፈጠራ የሆነን ቃልና ታሪክ ጨማምረውበት በመበረዝ አበላሽተውታል ብለው ነው፡፡ በትክክል ቢተረጎም እነዚህ በቁርአን ውስጥ ያሉት ጥቅሶች የመጽሐፍ ቅዱስን ታማኝነት ነው የሚናገሩት፡፡ ይህም ምዕራፍ በክርስትያንና በሙስሊሞች ሊኖር ስለሚችል ግንኙነት በጣም ጠቃሚ ምዕራፍ ነው፡፡

የነገሩም ዋና ቁልፍ ያለውአስመሳይ ጥቅሶችየሚለውን በመተርጎም ላይ ነው፡፡ የዚህም ምርመራ የሚጀምረው በመሐመድ ጊዜ ገናና ወደ ሆነው የፓጋን ልምምድ ላይ ነው፡፡ በእነዚያ ቀናት ጣዖት አምላኪዎች የግጥም ስራዎቻቸውን ከጣዖቶቻቸው በመገለጥ እንዳገኙት በመናገር በጣም የታወቁ ነበሩ፡፡ መሐመድ በቃሉ የተናገራቸው ጥቅሶችም የእነሱንየጣዖት አምላኪዎቹንመገለጥ የሚሉትን ነገር የሰው ፈጠራዎች ናቸው በማለት ይቃወማቸው ነበር፡፡

በተመሳሳይም መንገድ ቁርአን የሚናገረው ጥቅሶችን የፈጠሩ ክርስትያኖችና አይሁዶች ነበሩ በማለት ነው፡፡ ቁርአን እነሱን የሚከሳቸው አስመሳይ የሆኑትን ጥቅሶች ልክ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ናቸው በማለት ይሸጡ ነበር በማለት ነው፡፡ ነገር ግን ቁርአን እነዚህ የሰው ፈጠራዎች ወይንም የሐሰት አስተማሪዎቹ የተናገሯቸው ነገሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተጨመሩ በግልጥ አይናገርም፡፡ ምክንያቱም የሐሰት አስተማሪዎቹን የሚላቸው መጽሐፍን በአደባባይ እንዲያነቡና እነሱ የሚሉት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በፍፁም እንደሌለ እንዲያረጋግጡ ብቻ ነው፡፡

አንድ በአንድ ነጥቦቹ ከጥቅሶቹ ጋር፡፡

በመሐመድ ጊዜ ብዙ ገጣሚዎች ነበሩ፡- የማያምኑት የሚሉት ነገር መሐመድ ዝም ብሎ ገጣሚ ነው በማለት ነው 52.30፡፡ ገጣሚዎች በእያንዳንዱ ሸለቆ ውስጥ ያለምንም ዓላም ይዞሩ ነበርና፡፡ እነሱም ስህተትን ሊያምኑ የሚችሉ ተከታዮችን ይሰበስቡ ነበር፡፡ ገጣሚዎቹም የማይኖሩበትን ነገርና እራሳቸውም የማይለማመዱትን ነገር ያስተምሩ ነበር 26.224-226፡፡

እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የምኞት ጥቅሶች፡- እያንዳንዱ የማያምን ሰው ከዚህ ሕይወት በኋላ ስለሚሆነው ምንም ነገር እንዳይፈራ የሚፈልገው በራሱ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ነገርን የሚናገርለት መጽሐፍ እንዲቀርብለት ነው 74.52-53፡፡

ጣዖት አምላኪዎች ቅዱስ መጽሐፍን ያስመስላሉ፡- እጅግ በጣም ክፉ (ኃጢአተኛ) የሆኑት ሰዎች የስህተት ራዕይን የሚፈጥሩትና የአላህን መገለጥ የሚክዱት ናቸው፡፡ እነሱም ምንም ኃይል የሌላቸውን ጣዖታትን ያመልካሉ 10.17-18፡፡

ጣዖት አምላኪዎች የቀረበላቸው ፈተና፡- ጣዖት አምላኪዎች የሚሉት ቁርአን የተፈጠረ ነው (የሰው ፈጠራ) በማለት ነው፡፡ እነሱ የተጠየቁት በአምላኮቻቸው እርዳት እሱን የሚመስል አንድ ምዕራፍን እንዲጽፉ ነበር 10.38፡፡

ሕፃናትን መግደል፡- ሕፃናትን መግደል የጣዖት አምላኪዎች ሰዎችን ለማሳሳት የፈጠሩት አስተምህሮ ነበር፡፡ አላህም በሻ ኖሮ ባልሰሩት ነበር ከቅጥፈታቸውም ጋር ተዋቸው 6.137፡፡

የተፈጠረ ሕግ፡- የጣዖት አምላኪዎች ሰዎች ስለማይበሉት እህልና ስለ እንስሶች ውሸትን ይፈጥራሉ፡፡ ስለሚጫኑና ስለማይጫኑ እንስሶችም በአላህ ስም ይናገራሉ ይህም ኃጢአት ነው፡፡ እነሱም የራሳቸውንም ልጆች ግድያ ይፈቅዳሉ፡፡ ስለዚህም ስህተትን እራሳቸው ይፈጥራሉ፡፡ ልቅ ሆነዋል ምንም አልተማሩምም 6.137-140፡፡

ገዝተዋል፡- አንዳንዶች የውሸት ታሪክን በደስታ ገዝተዋል ይህንንም ሌሎችን ለማሳሳት እና ቁርአን ላይ ለማሾፍ ይጠቀሙበታል፡፡ እነዚህም ሰዎች የሚያዋርድ ቅጣትን ይቀበላሉ 31.6፡፡

ያልተማሩ ክርስትያኖችና አይሁዶች፡- በክርስትያኖች እና በአይሁዶች መካከል ያልተማሩና ስለመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማያውቁ ሰዎች አሉ፡፡ እነሱም የሚያውቁት መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚናገረው ነገር ውሸትንና ግምትን ብቻ ነው፡፡ እነሱም መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳቸው በእጃቸው በመጻፍ በጣም በትንሽ ገንዘብ ይሸጡታል፡፡ እነሱም ይቀጣሉ 2.78-79፡፡

የሐሰት የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች፡- የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በምላሶቻቸው የሚያጣምሙ የመጽሐፉ ሰዎች አሉ፡፡ የሐሰት አስተማሪዎቹም የሚጠየቁት የሚናገሩት እውነት እንደሆነ ለማረጋገጥ ቶራን አምጥተው እንዲያነቡት ነው፡፡ ከንባቡም በኋላ እነዚያ ስለ አላህ ውሸትን የፈጠሩት ትልቅ ኃጢአተኞች ናቸው 3.93-94፡፡ ኃጢአተኛ የሆኑት አይሁዶች ለሙሴ የተሰጠውን ቃል በማጣመማቸው በእነሱ ላይ ቁጣ ተልኮ ነበር 2.59፡፡

አልተለወጠም፡- የአላህ ቃላት በእውነትና በፍርድ ፍፁም የሆኑ ናቸው፡፡ ማንም እነሱን ሊለውጣቸው አይችልም 6.115፡፡

ተጠብቋል፡- ማንም ሰው የአላህን ቃል ሊለውጠው አይችልም፡፡ 18.27፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡-

ከዚህ በላይ በጥንቃቄ የሰፈሩት ሃያ ሁለት ጥቅሶች እውነትን ለመረዳት እጅግ ጠቃሚ ናቸው፡፡ ሙስሊሞች ክርስትያኖችን እና መጽሐፍ ቅዱስን አምርረው የሚጠሉት ያለ ምንም ተጨባጭ ምክንያት እንደሆነ ግልጥ ያደርጋሉ፡፡ ጥቅሶቹ ሲታዩ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገሩ ስለሚስሉ ብዙዎች ተሳስተውባቸዋል፡፡

ክርስትያኖች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እውነትነት ምንም እንኳን ከራሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ማስረጃ ባያስፈልጋቸውም እነዚህ ሃያ ሁለት ጥቅሶች መጽሐፍ ቅዱስን በተመለከተ የሚያቀርቡት ምንም ውንጀላ የለም፡፡ በመሆሁም ሙስሊሞች መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብና በውስጡ ያለውን መልእክት ለመረዳት የሚቸገሩበት ምክንያትም ሆነ መጽሐፍ ቅዱስን ለመቃወም የሚነሱበት ምንም ምክንያት አይኖራቸውም፡፡

ስለዚህም እናንተ መጽሐፍ ቅዱስን አግኝታችሁ እንድታነቡ ወይንም በዚህ ድረ-ገፅ ላይ ያለውን መጽሐፍ ቅዱስ እንድታነቡ እንጋብዛችኋለን፡፡ መልእክቱንም በማስተዋል እንድትረዱት የዘወትር ፀሎታችን ነው፡፡ እግዚአብሔር በምህረቱ ይርዳችሁ፡፡

 

የትርጉም ምንጭ: Counterfeit Verses, Chapter 19 of "A Topical Study of the Qur'an From a Christian Perspective" by M.J Fisher, M.Div

ሙሉ መጽሐፉ በአማርኛ: ርእሳዊ የቁርአን ጥናት በክርስትና አይን ሲመረመር

 

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ