የሴቶች ሁኔታ በቁርአን

M. J. Fisher, M.Div.

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

መግቢያና ማነፃፀሪያ

በአጠቃላይ ሙስሊም ወንዶች ሴቶችን ዝቅተኛ አድርገው ያዩአቸዋል፡፡ ይህ ባህርይ የባህል ችግር ነው ወይንስ መሐመድ ባስታወሳቸውና በቁርአን ላይ በተመዘገቡት ጥቅሶች ላይ የተመሰረተ ነው? በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የተሰበሰቡት ሃያ ዘጠኝ ጥቅሶች ግልፅ የሚያደርጉት በእስልምና ወንዶች የበላዮች መሆናቸውንና በሴቶች ላይ ስልጣን ያላቸው ብቻ ሳይሆን፤ ሴቶች ለወንዶች ታዛዦች የማይሆኑ ከሆነ እንዲመቷቸውም እንደታዘዙ ያረጋግጣሉ፡፡

የክርስትና ውርስ ባላቸው አገሮችም ውስጥ ያሉ ሴቶች በወንዶች እንደሚጨቆኑ ብዙ ዘገባዎች አሉ፡፡ ልዩነቱ ያለው ግን መጽሐፍ ቅዱስ በቅድሚያ የሚናገረው ሰዎች ሁሉ ያለ ምንም የፆታ ልዩነት እኩል ክብር እና መብት እንዳላቸው ነው፡፡ ታሪክም እንዳሳየው ወንጌል በግልፅ ተቀባይነት ባገኘባቸው ቦታዎች ሁሉ የሰብዓዊ መብትም ቀስ በቀስ እንደተሻሻለ ነው፡፡ ለእንደዚህ ዓይነቱም ሁኔታ በቂ የሆኑ ምክንያቶች አሉ፡፡

ክርስትያኖች እንሚያምኑት ሕይወታቸው ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌነትን መከተል እንዳለበት ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ በዘመኑ በነበረው ባህል መሠረት ሴቶችን ለማስተማር ጊዜውን ሰጥቶ ነበር፡፡ ይህንንም በሚገባ ለማየት ሉቃስ ወንጌል 10.38-42 መመልከት ይቻላል፡፡ ለሴቶች የነበረውም አክብሮት ለኃጢአተኞችም ሴቶች እንኳን ባደረገው እርህራሄ ወደ እሱ በተመለሱት ሴቶችም ሕይወት ውስጥ እንኳን ግልፅ ሆኗል ሉቃስ 7.36-39፡፡ እሱም የዘርንና የባህልን ገደብ አልፎ የእሱን እውነተኛ ማንነት ለሰማርያቷም ሴት ግልፅ አድርጓል ዮሐንስ 4.1-42፡፡ ከትንሳኤውም በኋላ እንኳን ኢየሱስ ለሴቶች ደቀመዛምርት በቅድሚያ እራሱን በመግለጥ ያለውን ክብር ገልጦላቸዋል፤ ማቴዎስ 28.8-10፡፡

መጽሐፍ ቅዱስን ክፍል የሚያብራሩ ብዙ ክርስትያኖች እንደሚናገሩት ሴቶችና ወንዶች በቤትና በቤተክርስትያን የሚጫወቱት ጠቃሚ ሚና እንዳለ ነው፡፡ ክርስትያኖች ሁሉ የሚያምኑት መጽሐፍ ቅዱስ በፆታ እኩልነት እንደሚያምን እና በግልፅም  እንደሚያስተምር ነው፡፡ በመጀመሪያም መጽሐፍ ቅዱስ የገለጠው እግዚአብሔር ሰውን ሴትና ወንድ አድርጎ እንደፈጠራቸው ነው፡፡ እነሱም የተፈጠሩት በእሱ ምሳሌ መሠረት ነው (ዘፍጥረት 1.27)፡፡ በእግዚአብሔር ዓይን ፊት ባልና ሚስት በጋብቻ አንድ ሰው ነው የሚሆኑት ዘፍጥረት 2.24፡፡ በአዲስ ኪዳንም ውስጥ የተጻፈው እንደክርስትያኖች በአማኞች ሁሉ መካከል እኩልነት እንዳለ ነው፡፡ ስለዚህም በቤተክርስትያን ውስጥ የተገለጠው ነገር ወንድና ሴት አይሁዳዊና የግሪክ ሰው ባሪያና ጨዋ የሚባል ልዩነት ማድረግ እንደሌለ ነው፤ ገላትያ 3.28፡፡

ቁርአን ግን ሴቶችን በተመለከተ እንደሚከተለው ይናገራል፡-

የሴቶች ዝቅተኝነት፡- ‹ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው፡፡ ... እነዚያን ማመጣቸውን የምትፈሩትን ገሥጹዋቸው በመኝታዎችም ተለዩዋቸው (ሳካ ሳታደርሱ) ምቱዋቸውም ...› 4.34፡፡ እንዲሁም ደግሞ ‹... ለወንዶችም በእነሱ ላይ ብልጫ አላቸው አላህም አሸናፊ ጥበበኛም ነው› 2.228፡፡

ንበረቶች፡- ወንዶች ከሚፈተኑበት ነገር ውስጥ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ልጆች፣ ወርቅ እና ብር ፈረሶች ከብቶች እና እርሻዎችን ስለማግኘት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ የዚህ ዓለም ንብረቶች ናቸው ነገር ግን አላህ ዘንድ መልካም መመለሻ (ገነት) አለ፤ 3.14፡፡

የወንዶች የበላይነትና ሚስቶችን መምታት፡- ወንዶች የሴቶች ገዢዎች ወይንም የበላዮች ናቸው ምክንያቱም ከሴቶች የበለጡ ሆነው ተፈጥረዋልና እንዲሁም ሴቶችን ይደግፋሉና፡፡ ባለመታዘዝ የሚጠረጠሩ ሴቶች መዋረድ አለባቸው ብቻቸውንም መተኛት እና መመታት አለባቸው፡፡ ወደ መታዘዝም በሚመለሱበት ጊዜ ተጨማሪ ቅጣት ሊገባቸው አይገባም፡፡ 4.34፡፡

የሚታረሱ ሜዳዎች (የእርሻ ቦታዎች)፡- ሴቶቻችሁ ለእናንተ እርሻ ናቸው እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ድረሱ ለነፍሶቻችሁም (መልካም ስራን) አስቀድሙ አላህንም ፍሩ እናንተም ተገናኝዎቹ መኾናችሁን ዕወቁ ምእመናንንም (በገነት) አብስር፣ 2.223፡፡

ጠላቶች፡- ሴቶችና ልጆች ለአማኞች ጠላቶች ናቸው እነሱን ተጠንቀቋቸው፡፡ አማኙ የበደሉትን ይቅር የሚል ከሆነ አላህም ይቅር ይላል፡፡ ልጆችና ሐብት ፈተናዎች ናቸው፡፡ የአንድ ሰው የመጀመሪያው ድርሻው (የቅድሚያ ሃላፊነቱ) ለአላህ መገዛት ነው፣ አላህን ታዘዙት እንዲሁም ልግስናን አድርጉ፣ 64.14-17፡፡

የሴቶች ተፈጥሮና ዋጋ፡- ወንድ ልጆችን ማድረግ ሴቶችን ልጆች ከማግኘት የበለጠ ዋጋ ያለው ነገር ነው ምክንያቱም ሴቶች ርካሽ ጌጣጌጥን በማድረግ ስለሚያድጉና በክርክርም ወቅት ሎጂካዊ መልስን መናገርን ስለማይችሉ ነው፡፡ እነዚያም፣ መላእክት ሴቶች ናቸው በማለት የሚያስቡት ለዚህ እምነታቸው ምላሽን ይሰጡበታል፡፡ እነዚያም አላህ ሴት አማልክት የሆኑ ሴቶችን ልጆች አሉት በማለት የሚያምቱ ስህተቶችና ትክክል ያልሆኑ ናቸው፡፡ እሱ ሴት ልጆች የሉትም፣ አላህ ለምንድነው ሴት ልጆች የሚኖሩት? ወንዶች የተመረጡ ሆነው ሳሉ? 17.40፣ 43.16-19፣ 53.19-22?

የሴቶች ታማኝነት፡- ለብድር ስምምነት (ውል) ለመመስከር የሚበቁቱ ሁለት ወንዶች ናቸው፡፡ ሁለት ወንዶች የማይገኙ ከሆነ ከዚያም አንድ ወንድና ሁለት ሴቶች ሊበቁ ይችላሉ፡፡ ሴቶቹም መመረጥ ያለባቸው በጥንቃቄ ነው፡፡ የሚያስፈልጉት ሁለት ሴቶች ነው ምክንያቱም አንዳቸው ስህተት ቢሰሩ ወይንም ነገሩን ቢረሱ ሌላዋ ልታስታውስ ትችላለችና 2.282፡፡

ገንዘብን በተመለከተ የሚኖር መበላለጥ፡- ወንዶች ከሴቶች ይልቅ እጥፍ ውርስን መውረስ ይኖርባቸዋል፡፡ ሁለት ወይንም ከዚያ በላይ ሴቶች ቢኖሩ እነሱም መሬቱን ሁለት ሦስተኛ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ አንዲት ሴት ብቻ ብትኖር ልትወርስ የምትችለው ግማሹን ንብረት (መሬት) ነው 4.11፡፡ አንዲት ሴት ብትሞት ባሏ ምንም ልጆች የሌሉት ከሆነ የንብረቷን ግማሽ ይወርሳል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ባሏ የሞተባት ሴት ግን የባሏን ንብረት አንድ አራተኛ ነው የምትወርሰው (ልጆች ከሌሉ)፤ 4.12፡፡ አንድ ወንድ፤ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት እና እህት ብትኖረው እሷ የእሱን ንብረት ግማሹን ልትወርስ ትችላለች፡፡ አንዲት ሴት ልጅ ሳይኖራት ብትሞት ወንድሟ የእሷን ንብረት በሙሉ መውረስ ይችላል፡፡ አንድ ሰው ልጅ ሳይኖረው ቢሞት እና ወንድሞችና እህቶች ቢኖሩት የአንድ ወንድ ድርሻ መሆን ያለበት የሁለት ሴቶች ድርሻ ነው 4.176፡፡

መሸፈን፡- የመሐመድ ሚስቶችና ሙስሊም ሴቶች ሰውነታቸውን በመጎናፀፊያ መሸፈን አለባቸው፡፡ ይህም ከቤት ውጪ ሲሆኑ ነው ይህም እንዳይታወቁና እንዳይጎዱ ነው፣ 33.59፡፡

የባሪያ ነገር፡- ሙስሊሞች ከሚስቶቻቸው እና በጦርነት ከማረኳቸው ከሴት ባሪያዎቻቸው ውጪ ግብረ ስጋ ግንኙነትን ማድረግ የለባቸውም፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ግንኙነት የተነቀፈ ነው 23.5-6፡፡ ባሪያዎች አላህ ለባለቤቶቻቸው ከሰጠው ሐብት አይካፈሉም፡፡ የባሪያ ባለቤቶች እንደሌሎቹ ሙስሊሞች ባሪያዎቻቸውን መፍራት የለባቸውም፣ 30.28፡፡

ወንድ ልጆች በረከቶች ናቸው፡- ሚስቶች ወንድ ልጆች እና ወንድ የሆኑ ልጅ ልጆች ለአማኞች ሽልማቶች ናቸው 16.72፡፡

በራቁትነት የተገኘች ሴት፡- አንዲት ሴት እራቁትዋን መገኘቷ በአራት ምስክር ቢረጋገጥና ብታምን እስከ እለተ ሞቷ ድረስ ወይንም አላህ አንድ መንገድን እስከከፈተ ድረስ በቤት ውስጥ ተወስና ትኖራለች፡፡ ነገር ግን ሁለት ሰዎች በተመሳሳይ ወንጀል ውስጥ ቢገኙ ሁለቱም ይቀጡ ነገር ግን ንስሐ ቢገቡ ሁለቱን ተዋቸው 4.15፣16፡፡

አመንዝራ 100 ግርፋት ይገረፍ፡- ወንድና ሴት አመንዝራ ሆነው ከተገኙ ወይንም ለአቅመ አዳም ከመድረሳቸው በፊት ዝሙትን ቢፈፅሙ አንድ መቶ ጊዜ ይገረፉ፡፡ ለእነሱም ምንም ምህረት አይደረግላቸውም፡፡ ይህም በሙስሊም ቡድኖች መመስከር ይገባዋል፡፡ እነሱም ሊያገቡ የሚችሉት በተመሳሳይ ወንጀል ኃጢአተኛ የሆነውን ሰው ብቻ ነው ወይንም በእስልምና የማያምነውን ሰው ነው 24.2፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡-

የሙስሊሞች ቁርአን ስለ ሴቶች የሚያስተምራቸውን ጥቅሶች በሙሉ ከዚህ በላይ በዝርዝር አይተናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በፆታ ላይ የተመሠረተ ምንም ልዩነትን አያደርግም፡፡ ወንዶችም ሴቶችም በእግዚአብሔር የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ወንዶችም ሴቶች እኩል ኃጢአተኞችና የእግዚአብሔር የፍርድ ቁጣ የሚጠብቃቸው ናቸው፡፡

እግዚአብሔር ግን ለወንዶችም ለሴቶችም የሚሆን የደስታ ዜና አለው፣ ይህንን የደስታ ዜና የምስራች ወንጌል ብለን እንጠራዋለን፡፡ ወንዶችም ሴቶችም ኃጢአታቸውን ተናዘዘው በዚህ የደስታ ዜና አማካኝነት ወደ እግዚአብሔር ቢመጡ ሙሉ ይቅርታን እና የዘለላለም ሕይወትን ተስፋ ይቀበላሉ፡፡ ሕይወታቸውም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልቶ ይለወጣል፣ ከእግዚአብሔርም የሚገኝን ደስታንና ሰላምንም ይሞላሉ፡፡

የዚህ ድረ ገፅ አዘጋጆች ዓላማም አንባቢዎች አዳኝ ከሆነው፣ በእውነት ከሚያስብላቸውና ከሚወዳቸው ፈጣሪያቸው ጋር በቃሉ መሠረት እንዲታረቁ ነው፡፡ ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስን አግኙና አንብቡ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኝ የወንጌል አማኞች ቤተክርስትያን በመሄድ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ ወደ እርሱም በንስሐ ቅረቡ ይቅር ይላችኋል፣ እግዚአብሔር በምህረቱ ይርዳችሁ፤ አሜን፡፡

የትርጉም ምንጭ: Status of Women,  Chapter 4 of "A Topical Study of the Qur'an From a Christian Perspective" by M.J Fisher, M.Div

ሙሉ መጽሐፉ በአማርኛ: ርእሳዊ የቁርአን ጥናት በክርስትና አይን ሲመረመር

 

ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ