ቁርአንና ሳይንሳዊ ተዓምሮቹ
የፈጠራ ወሬ  

ኒል አርምስትሮንግ (ጨረቃን ለመጀመሪያ ጊዜ የረገጠው) እንዴት ሙስሊም ተደረገ
ትርጉምና ቅንብ በአዘጋጁ

በእስላም ዓለም ውስጥ ከሚዘዋወሩት ብዙ የፈጠራ ወሬዎች ውስጥ  ጨረቃን ለመጀመሪያ ጊዜ የረገጠውና በጣም ታዋቂው ጠፈርተኛ ኒል አርምስትሮንግ ሙስሊም ሆኗል ተብሎ የተነገረው አንዱ ሲሆን እርሱም በፍፁም የማይከስም ዜና የሆነ ይመስላል፡፡ 

ይህንን ወሬ የሚያሳፍረው የሚቀጥለው አረፍተ ነገር ይሆናል፡- መስከረም 6 ቀን 2005 ዓ.ም በማሌዥያ በተካሄደው የዓለም አቀፍ የመሪዎች ስብሰባ (ፎረም) ላይ ኒል አርምስትሮንግ ተሳትፎ ነበር፡፡ በማሌዥያ ውስጥ በጣም ተነባቢ የሆነው ማሌዢያዊው የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ‘The Star Malaysia’ ያንን አጋጣሚ በመጠቀም ወደ ጨረቃ ጉዞ በተደረገው ሚሽን ተሳታፊ ሆኖ በአፖሎ 11 መጓዙንና ጨረቃ ላይ ማረፉን በተመለከተ ለኒል አርምስትሮንግ ቃለ መጠይቅ አድርጎለት ነበር፡፡ በማግስቱም መስከረም 7 ቀን 2005 በታተመው ጋዜጣ ላይ Armstrong recalls moon landing በሚል ርዕስ በቀረበው ጽሑፍ በሕትመት እንዲሁም በድረገፅ ላይ የሚከተለውን አረፍተ ነገር አንድ አንባቢ ያገኛል፡-

የ75 ዓመቱ አርምስሮንግ የሙስሎሞችን የፀሎት ጥሪ በጨረቃ ላይ ሰምቶ እስላም ሆኗል በመባል ይነገር የነበረው ዜና ውሸት ነው ብሏል፡፡

በዚህ ጋዜጣ ላይ የቀረበው ጽሑፍ የቀረው ክፍል በመጀመሪያ በ1996 የተጻፈው ሲሆን ከዚያን ጀምሮ ለብዙ ጊዜ እንደገና ተሸሽሏል፣ ይህም ደግሞ ከዚያ ቀደም አንድም ሰው ኒል አርምስትሮንግን እንዲህ ዓይነት ጥያቄ እንዳልጠየቀውና ይህንንም ጉዳይ ግልፅ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ያሳየናል፡፡

ለእኛም በ1996 ሕዳር ወር መካከል ላይ የሚከተለው ሪፖርት ደረሶን ነበር፡-

“እኛ በጣም ጥሩ የሆነ የእስላሞች ማህበረሰብ የሬዴዮ ጣቢያ በኬፕ-ታዎን አለን፡፡  የሚከተለውም ታሪክ የእኛ የሙስሊም ሬዲዮ እውነተኛና የከበረ እውነትን እንደሚናገር በሌላው ቀን ተነግሮን ነበር፡ ይህም ሉዊስ አርምስትሮንግና ጓደኞቹ በጨረቃ ላይ መራመዳቸውን የሚገልጥ ነበር እነርሱም በማይረዱት ማለትም በተለየና ባልተመለደ ቋንቋ ድምፆችን ሰምተዋል፡፡ ጥቂትም ቆይቶ በመሬት ከተመለሱ በኋላ ነበር ድምፁ በእርግጥ አዛን የነበረ መሆኑን የተረዱት፡፡  እኔም አንዳንድ መስጊዶች እጅግ በጣም ኃይለኛ በሆነ የድምፅ ማጉያ አዛን ሲያደርጉ አይቻለሁ፣ ኦ! ይገርማል በዚያን ቀን አንድ ሰው እዚህ ምድር ላይ በእርግጥ ደምፁን በጣም ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል ማለት ነው፡፡”(ማሳሰቢያ፡ በእርግጥ ይህ ማገናዘቢያ የተደረገው ጠፈርተኛውን ኒል አርምስትሮንግን በተመለከተ ነበር እንጂ የጃዝ ሙዚቀኛውን ሉዊስ አርምስትሮንግ በተመለከተ አልነበረም)፡፡

ይህ ወሬ በየወሩ በእስላማዊ አዳዲስ የዜና ማሰራጫዎች ቡድኖች ዘንድ ይነገራል፣ በጣም የቅርቡ ምሳሌ የሚከተለው ነው፡

አርምስትሮን ሙስሊም ነውን? በሚል ርዕስ በ1996 ነሐሴ 26 ቀን University of Canberra, Australia ውስጥ በsoc.religion.islam በተባለ የዜና ቡድን የሚከተለው መልእክት ተሰራጭቷል፡፡ ጥያቄው የተነሳው በነሐሴ 20 1996 eshaikh@alpha2.curtin.edu.au wrote የሚከተለውን ከጻፈ በኋላ ነው፡

አርምስትሮንግ ሙስሊም የመሆኑ ነገር እውነት መሆኑን የሚነግረኝ እባካችሁ ይኖራልን? 

ሰላም፡

እኔ የሰማሁት እርሱ ጨረቃ በነበረበት ጊዜ እርሱ አዛን (የፀሎት ጥሪ) ሰምቶ እንደነበር እንዲሁም ያንን አዛን ምድር ላይ ተመልሶ እንደሰማውና ሙስሊም እንደሆነ ነው፡፡ እንዲሁም እርሱ ሊባኖን እንደሚኖርና (በኔ አገር) የእርሱም ጎረቤቶች፤ እርሱ ከማንም ጋር አይነጋገርም በማለት እንደገለፁ የሚናገርን ጽሑፍን አንብቤያለሁ፡፡ እርሱ በጣም ገናና ሰው ሊሆን ይችል ነበር ምክንያቱም በጨረቃ ላይ የረገጠ ሁለተኛው ሰው ጨረቃን የረገጠው አሁንም ዝነኛ ነውና፡፡ ነገር ግን ኒል ለመኖር የወሰነው እንደዚህ ሆኖ ነው፡፡ አላህ አላም (እግዚአብሔር ያውቃል) ስለ እርሱ ብዙ የሚያውቅ ሰው ካለ እኔም ተጨማሪ ማወቅ እወዳለሁኝ፡፡ 

ዋ ሳላም፡፡

እዚህ ላይ በsoc.religion.islam  የዜና ቡድኖቹ የተረጩት ሁለት ዜናዎች ሙስሊሞች በሚያቀርቡት ጥያቄዎችና ንግግሮች ላይ ቢያንስ ያቀረቡት ይህ ተባራሪ ወሬ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ጊልበርቶ በሌሎች አንዳንድ ተባራሪ ወሬዎች ላይ ሪፖርት ሲያደርግ እንዴት ነገሩ እንደመነጨ (ተባራሪ ወሬ በተባራሪ ወሬ ላይ በሚለው ርዕሱ ላይ ነገሩ በጣም ውስብስው እየሆነ እንደመጣ ገልጧል)፡፡

ስለዚህም በሚከተለው መልእክት ላይ የቀረበው እንደሚከተለው ነው በ1996 ነሐሴ 23 ቀን ከ ጊልበርቶ ከsoc.religion.islam ቡድን፡ 

አሳላም አሊኩም  

ከብዙ ጊዜ በፊት እኔ የሰማሁት በዚህ ቡድን ውስጥ ኒል አርምስትሮንግ ወደ ግብፅ ሄዶ አዛንን እንደሰማና በቃለ መጠይቅም ላይ ይህ ውብ ማለቱን ነው፡፡ እናም ያ አባባል በሆነ በአንድ መንገድ ተለውጦ ወደ ግሩም ታሪክነት ተቀየረ ታሪኩም “እርሱ በጨረቃ ላይ በነበረ ጊዜ  ያልተለመደ (እንግዳ የሆነ ድምፅ) እንዴት እንደሰማና በመጨረሻም ምድር ከተመለሰ በኋላ አዛን ሆኖ እንዳገኘው ከዚህም ልምምዱ የተነሳ እርሱ ሙስሊም እንደሆነ ነው፡፡” በሚገባ እንደማውቀው ከሆነ እርሱ ሙስሊም አይደለም (አላሁ አሊም)፡፡  

ሳላም  ጊልበርቶ

እንዲሁም ደግሞ፡  

ማሱድ አህመድ ካን በጻፈው <50k5cg$lnt@usenet.srv.cis.pitt.edu>, mas@crosfield.co.uk ጽሑፍ ላይ የሚከተለው ቀርቧል፡ 

 አይደለም! ይህ ነገር በየጊዜው ተደጋግሞ እንደገና እየመጣ ነው፣ እኔ ከተረዳሁት ኒል አርምስትሮንግ በፍፁም ሙስሊም አይደለም በፍፁምም አልነበረም፣ እርሱ በአሜሪካ ነው የሚኖረው ገለልተኛ ሰው ነው አንዳንዴ ሌክቸሮች ያደርጋል፡፡ አንድ ሰው እንደነገረኝ እርሱ በግልጥ የሚናገረው ሙስሊም እንዳልነበረና፤ ይህም ተባራሪ ወሬ እንዴት እንደመነጨም እንደማያውቅ ነው፡፡  አንዳንድ ሙስሊሞች የበረዶ ኳስ የሆኑ የፈጠራ ታሪኮችን መፍጠራቸው በጣም አሳዛኝ ነገር ነው እነዚህም ኳሶች ወዲያውኑ ወይንም ዘግይቶ ሙስሊሞች የሚጉራሩባቸውና የሚመኩባቸው ነገሮችም እውነታቸው መውጣቱ አይቀርም፡፡ ስለ አርምስትሮንግ የሚያውቁ ሰዎች ምን ዓይነት ስሜት እንደሚሰማቸው ልትገምቱ ትችላላለችሁን?  

ዋኣስ ሳላም 

 ማሱድ

በሚከተሉት ጥቂት አረፍተ ነገሮች ውስጥ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ በአርምትሮንግ ፈቃድ መሰረት ስለ እርሱ እንዲናገር ስልጣን በተሰጠው ሰው (ቃል አቀባይ) የሚከተለው ተነግሯል፡-  የሚከለተለው ደብዳቤ የተጻፈው ሐምሌ 14 ቀን 1983 ዓ.ም ለሚስተር ፊሊ ፓርሻል የኤሺያ ምርምር ማዕከል አለም አቀፍ የክርስትያን ህብረት ሚሺጋን ላለ ሰው ነው፡፡ ደብዳቤው እንደሚከተለው ይላል፡

ክቡር ሚስተር ፓርሻል፡

ሚስተር አርምስትሮንግ ለደብዳቤህ መልስን እንድሰጥ እንዲሁም ለጥያቄህ ትህትናዊነት  እንዳመሰግንህም ጭምር ጠይቆኛል፡፡

እርሱ በጨረቃ ላይና በሌላም ቦታ አዛንን ሰምቷል ከዚያም ወደ እስልምና እምነት ተቀይሯል የሚለው ሪፖርት በአጭሩ ከእውነት የራቀ ነው፡፡

በማሌሺያ፣ በኢንዶኔዥያ እንዲሁም በሌሎች ብዙ አገሮች ውስጥ ያለምንም ማረጋገጫ እነዚህን ሪፖርቶች በጋዜጦቻቸው ላይ አትመዋቸዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ብቃት ያጣ የጋዜጠኝነት ስራ በእናንተ ላይ ስላደረሰው ችግር በጣም እናዝናለን፡፡

ከዚህም አስከትሎ ሚስተር አርምስትሮን የቴሌፎን ቃለ መጠይቅ ለመደረግና  ለነዚህም የፈጠራ ታሪኮች ያለውን ምላሽ ለመስጠት ተስማምቷል፡፡ ከዚህም ጋር የዩናይትድ ስቴት የመንግስት ዲፓርትመንት ጋር ከዚህ በፊት ግንኙነቶች የተደረጉባቸውን ፋይሎች ከቃለመጠይቁ በኋላ አያይዣለሁኝ፡፡

በአክብሮት  

ቪቫ ኋይት  

የአስተዳደር ክፍል

አስተያየት፡ በእጃችን ውስጥ የዚህ ደብዳቤ ፎቶ ኮፒ አለን ከዚህ በላይ ካለው ጽሑፍ ጋር ተመሳሳይ የሆነ፣ ከሚስተር አርምስትሮንግ የመንገድ ቁጥርና የቴሌፎን ቁጥር መሰረዝ በስተቀር፡፡ ከዚህም በላይ ያለው ሐሳብ የሚያሳየው ነገር ይህ ወሬ ከየት እንደመጣ ነው፡፡ ምክንያቱም እንደተገመተው ሁሉ ሚስተር አርምስትሮንግ በሊባኖን እንደሚኖር ነው፤ አዎን ሊባኖን የሚለው የመኖሪያ አድራሻ ትክክል ነው፡፡ ነገር ግን ይህ “ሊባኖን” የመካከለኛው ምስራቅ ሊባኖን ሳይሆን በዩናይትድ ስቴት አሜሪካ ሚድ ዌስት በሚባለው አካባቢ ያለው ስፍራ ነው እንጂ፡፡  በእስላም አገሮች ሁሉ ውስጥ ላሉት ለኤምባሲዎችና ለኮንሱላር ቢሮዎች በዩናይስትድ ስቴት የመንግስት ቢሮ የተላከው መረጃ እንደሚከተለው ይነበባል፡-

 

P 04085 0Z MAR 83 ZEX

 

 

FM SECSTATE WASHD C

 

 

TO ALL DIPLOMATIC AND CONSULAR POSTS PRIORITY 

 

 

BI

 

 

UNCLAS STATE 056309

 

 

 

 

 

FOLLOWING REPEAT SENT ACTION ALL EAST ASIAN AND

 

 

PACIFIC DIPLOMATIC POSTS DTD MAR 02.

 

 

 

 

 

QUOTE:   UNCLAS STATE 056309

 

 

E.O.  12356: N/A

 

 

TAGS:  PREL, PGOV, US, ID

 

 

SUBJECT:     ALLEGED CONVERSION OF NEIL ARMSTRONG TO ISLAM

 

 

REF: JAKARTA 3281 AND 2374 (NOT ..)

 

1.     የቀደመው አስትሮኖት ኒል አርምስትሮንግ በአሁኑ ጊዜ በግል ድርጅት የሚሰራ ሲሆን በግብፅ፣ በማሌዥያ እና ኢንዶኔዥያ (እንዲሁም ምናልባትም በሌሎች አገሮችም ሁሉ ውስጥ) የጋዜጦች ሪፖርት ላይ ዋነኛ ርዕስ ሆኗል፡፡ ይህም እርሱ በጨረቃ ላይ ባረፈበት ጊዜ በ1969 ወደ እስልምና እምነቱን ቀይሯል ይላል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሪፖርቶች መሰረት አርምስትሮንግ ከግለሰቦችና ከሃይማኖት ድርጅቶች ጋር ግንኙነቶች ተደርገውለታል፤ እንዲሁም ከእስልምና እንቅስቃሴ ጋር ሊተባበር ይችል እንደሆነ የሚሞላ ቅፅም ቢያንስ ከአንድ መንግስትም ቀርቦለታል፡፡

2.     ማንንም እና የማንኛውንም ሃይማኖት ድርጅት ለማሳዘን ምንም ፍላጎት እንደሌለው በጣም አጥብቆ እየተናገረ ያለው አርምስትሮንግ ለአሜሪካ መንግስት ቢሮ ያሳሰበው የእሱ ወደ እስልምና እምነት መቀየር ሪፖርቶች ሁሉ ስህተቶች መሆናቸውን ነው፡፡

3.     ስለዚህም ኤምባሲዎች ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ጥያቄዎች ቢቀርቡላቸው አርምስትሮንግን የጠየቀው ጥያቄ ኤምባሲዎች በትህትና ነገር ግን በአፅንዖት እርሱ ወደ እስልምና እምነቱን እንዳልቀየረ እንዲናገሩና በአሁኑም ጊዜ በእስላማዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ለመሳተፍ ወደየትኛውም አገር ለመሄድ አሁንም ወደፊትም ምንም ዓይነት ዕቅድ እንደሌለው ነው፡፡ 

ከዚህም በተጨማሪ በአረቢያ ጆርናል The Islamic World Review, Issue June 1985/Ramadan 1405, page 5: ላይ ለአዘጋጁ የተላከ የሚከተለው ደብዳቤ ታትሟል፡፡ 

አንድ ሙስሊም በጨረቃ ላይ?

በሙስሊሙ ዓለም ውስጥ ምን እየሆነ እንዳለ በመዘገብ በኩል አረቢያ ከሁሉም የላቀች የዜና መጽሔት ናት፡፡ የእናንተም ሪፖርት ዝርዝርና ተጨባጭ ለመሆን በተቻለው መጠን ይጥራል፡፡ የፖሊቲካዊ ፖሊሲዎችንና የሃይማኖታዊ ክስተቶችን ለመተቸት ያላችሁ ፈቃደኝነት በሙስሊሙ ዓለም ውስጥ የሚያድስ (የሚያዝናና) ነው፡፡ እንደ አንድ አሜሪካዊ ስለ ምዕራቡ ዓለም እናንተ የምታቀርቡት ትችት በመሠረቱ ትክክለኛ ነው፡፡

በሙስሊሙ ዓለም ውስጥ ሁሉ የተሰራጨውን የተሳሳተ ግንዛቤ ደግሞ ብትቃወሙ እጅግ በጣም የሚረዳ ይሆናል፡፡ ከሞሮኮ ጀምሮ እስከ ፊሊፒንስ ድረስ በአጠቃላይ የሚታመነው ኒል አርምስትሮንግ በጨረቃ ላይ እንዳለ አዛንን እንደሰማና ወደ እስልምና እንደተለወጠ ነው እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ ሙሉ ጊዜውን ሰጥቶ የሙስሊምን እምነት ለማስፋፋት እየሰራ እንዳለ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴት ኦፍ አሜሪካ የመንግስት ቢሮ ይህ የአርምስትሮንግ ታሪክ እውነት እንዳልሆነ የሚገልፅ ማስታዎሻን አስተላልፏል፡፡ ማስታዎሻው የሚለው “ማንንም እና የማንኛውንም ሃይማኖት ድርጅት ለማሳዘን ምንም ፍላጎት እንደሌለው በጣም አጥብቆ እየተናገረ አርምስትሮንግ ለመንግስት ቢሮ ያሳሰበው የእሱ ወደ እስልምና እምነት መቀየር ሪፖርቶች ሁሉ ስህተቶች መሆናቸውን ነው፡፡ ስለዚህም ኤምባሲዎች ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ጥቄዎች ቢቀርቡላቸው አርምስትሮንግ የጠየቀው ጥያቄ ኤምባሲዎች በትህትና ነገር ግን በአፅንዖት እርሱ ወደ እስልምና እምነቱን እንዳልቀየረ እንዲናገሩና በአሁኑም ጊዜ በእስላማዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ለመሳተፍ ወደየትኛውም አገር ለመሄድ አሁንም ወደፊትም ምንም ዓይነት ዕቅድ እንደሌለው ነው፡፡”  ማስታዎሻ፡ ይህ ጽሑፍ ለሁሉም አገር ዲፕሎማቶችና የኮንሱላር ጽሕፈት ቤቶች ሁሉ ተልኳል፡፡ 

 ዶ/ር ፊል ፓርሻል 

የኤሺያውያን የምርምር ማዕከል ዳይሬክተር፣ ማኒላ ፊሊፒንስ

የሚያሳዝነው ከዚህ በላይ እንደተመዘገበው ይህ ተባራሪ ወሬ አሁንም በብዙ የእስላም አገሮች ውስጥ እየተነዛ ነው ለብዙ አስርተ ዓመታት ውስጥ ስህተት መሆኑ ከተነገረ በኋላም አሁንም በተደጋጋሚ ይነዛል፡፡ ይህም አፍ በአፍ በሆነ ፕሮፓጋንዳ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በሙስሊሞች የሬዴዮ ጣቢያዎች ጭምርም እየተሰራጨ ይገኛል፡፡

አሁንም እንኳን አንዳንድ ሙስሊሞች ለወንድሞቻቸው የውሸት ወሬ መሆኑን ሲናገሩ አያምኗቸውም፡፡ አዲሶችም የዜና ቡድኖች እንደገና እንደ አዲስ ያሰራጩታል ለምሳሌም ያህል በ1997 ጥር 17 ቀን alt.religion.islam በተባለው የዜና ድርጅት ኒል አርምስትሮን የመጀመሪያው ሰው በጨረቃ ላይ በሚል ርዕስ የቀረበው፡

“ትክክል አይደለም ይህ በሙስሊም አገር ውስጥ የሚነዛ ተረት ነው፡፡ አርምስትሮንግ ይህንን ታሪክ ክዶታል እርሱ ሙስሊም አይደለም ወ.ዘ.ተ፡፡ ቀጥሎም፡-  ነገር ግን እርሱ በቱርክ ውስጥ ማልኮም እከሌ በሰገደበት መስጊድ ውስጥ ሰግዷል እናም እጅግ በጣም ብዙ ሕዝብ ከእርሱ በስተጀርባ ሲሰግድ ነበር፡፡”

ሳላምስ

ይህ ተባራሪ ወሬ ያከስም ይሆን? የኔ ጥያቄ የሚሆነው ፋርዛድ ይሆናል (ልክ እንደሌሎች የተባራሪ ወሬን እንደሚያዛምቱት ሁሉ) እናንተ እርሱ በዚህ መስጊድ ውስጥ ሲሰግድ በቦታው ላይ ነበራችሁን? አይደለም? አልነበራችሁም እኔ እንደዚያ አስባለሁ፡፡

ነገር ግን ብዙዎች በፍፁም አይረኩም ለማንኛውም ግን ይህ ሰው ቢያንስ ለዚህ ተባራሪ ወሬ ምንጭነት የሚተለውን ማገናዘቢያ ሰጥቷል፡- 

“እኔ የማስበው እርሱ ወደ እስልምና ተለውጧል ብዬ ነው፡፡ እርሱ ወደ እስልምና የተቀየረ አንድ አሜሪካዊ መሆኑን የሚገልጡ እስላማዊ ያልሆኑና እስላም የሆኑ ምንጮች ላይ አግኝቻለሁ፤ እነዚህም “የሙስሊም ፕራይመር” መጽሐፍ በኢራ ዚፕ እና “የእግዚአብሔር መካቾች” ከሚባሉት መጽሐፍት ላይ ነው፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

እስከ አሁን ድረስ በሙስሊም አገሮች እንደ ተዓምር ሆኖ የሚነገረው ነገር ኒል አርምስትሮንግ ጨረቃ ላይ አርፎ እንደተመለሰ ሙስሊም ሆነ የሚለው ዜና ነው፡፡ ይህ አስገራሚ ዜና ከቁርአን ሳይንሳዊና ትንቢታዊ ተዓምራቶች ጋር ሊያያዝ እንደሚችል መታሰቡና እንደማስረጃ መቆጠሩም አልቀረም፡፡ ኒል አርመስትሮንግ ወደ እስልምና ለመቀየሩ የተሰጠው ተዓምራዊ ማስረጃ ደግሞ በጨረቃ ላይ የሰማውን አዛን በምድር ላይ በግብፅ እያለ እንደገና ስለማው ነበርም ተብሏል፡፡

ይሁን እንጂ ከዚህ በላይ በቀረቡት ማስረጃዎች ስለ አርምስትሮንግ እስላም መሆን የተነዙት ዜናዎች ሁሉ ውሸት እንደሆኑ፣ እራሱ አርምስትሮንግ በተደጋጋሚ፣ በእርሱም አሳሳቢነት የአሜሪካ መንግስት በየአገሩ ላሉ የኤምባሲ ቢሮዎቹ ሁሉ ያስተላለፈው ሰርኩላር ደብዳቤ በግልፅ ያስረዳሉ፡፡

እዚህ ላይ ትልቅ ጥያቄ የሚሆነው ነገር፣ ምንም ዓይነት ማስረጃ ሳይኖራቸው አርምስትሮንግ ሙስሊም ሆነ በማለት ሙስሊሞች መናገር ለምን አስፈለጋቸው? ከተባራሪው ወሬ የተነሳ የጋዜጣ አዘጋጆቹ መስሏቸው ነው ብለን ብንል እንኳን ውሸት ሆኖ ካገኙት በኋላስ ለምን አላስተባበሉትም? አርምስትሮንግን እና በዚህ የውሸት መረጃ መሰረት የተወናበዱትን ይቅርታ ለምን አልጠየቁም? መልሱን ለሙስሊም አንባቢዎች እንተወው፡፡

ይህንን እና ሌሎች ተመሳሳይ የውሸት ዜናዎችን በቅንነት የሚመከታተል አንድ ጠያቂ አዕምሮ ውስጥ ከፍተኛ ውዥንብር መፈጠሩ ተገቢ ነው፡፡ ከአምላክ መጣ የሚባል ሃይማኖት “የውሸት” ማረጋገጫ ያስፈልገዋልን? ከአምላክ ለመጣ ሃይማኖት ዜና ማሰራጫ ቡድኖች (የእምነቱ ዋና ፕሮፓጋንዳ ክፍሎች)  የውሸትን ዜና እውነተኛ እንደሆነ ማቅረባቸው ትክክል ነውን? ወ.ዘ.ተ የሚሉ ተጨማሪ ጥያቄዎችንም ለመደርደር ይቻላል፡፡

ቁርአን ከአምላክ እንደመጣ ከሚሰጡት ማረጋገጫዎች አንዱ ሳይንሳዊ ተአምርና ሳይንሳዊ ትንቢት የተካተተበት መሆኑ በአሁኑ ጊዜ በጣም እየተነገረለት ነው፡፡ በቁርአን ውስጥ ሳይንሳዊ ማስረጃ እየተባሉ የማይሉትን እንዲሉ የሚጠመዘዙትን ጥቅሶች ሁሉ አንድ ሰው በጭፍን መቀበል ይገባዋል ብለን እኛ አዘጋጆቹ አናምንም፡፡ ስለዚህም ለሙስሊም አንባቢዎች አንዳንድ ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን በዚህ ገፅ ላይ ለማቅረብ እንወዳለን፡፡

የእኛ ዋናው ዓላማችን ግን የአንባቢዎች የዘላለም ሕይወት ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን በተመለከተ ለእኛ በሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ስራ የሰራውን የእግዚአብሔርን መልእክት ለአንባቢዎች ልንጠቁማቸው እንፈልጋለን፡፡ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ በቅንነትና ክፍት በሆነ አዕምሮ ሊያነበው ለመጣ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገር መጽሐፍ ነው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ለሰው ውስጥ፤ ለሰው ልብ ማለትም ለነፍስ ይናገራል፡፡ በመሆኑም ለነፍስ ጥማትና ዋና ፍላጎት መፍትሔ የሚሆነውን ነገር ይናገራል፡፡ በዚህች ምድር የሰው ሕይወት ትርጉም እና ዓላማ ያለው የሚሆነው እንዴት እንደሆነም ያሳያል፡፡ አዎ መጽሐፍ ቅዱስ ለሰው የሚያስፈልገውን መሰረታዊውን ነገር ይገልጣል፡፡ ከዚያም የመዳንን እና አዲስ ሕይወትን እንዴት ለማግኘትና ለመቀበል እንደሚቻል ይነግረናል፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊው የክርስትና እምነትም በታዋቂና በዝነኛ ሰዎች ላይ አልተመሰረተም የእነርሱንም ማንነትና ሕይወት ለእውነተኛነቱ ማረጋገጫነት ተጠቅሞ አያውቅም፡፡ ክርስትና የተመሰረተውና የታተመው በምንጩ በእግዚአብሔር ኃይልና እውነት ብቻ ላይ ነው፡፡

ኦ አንባቢዎች ሆይ ይህንን እውነት ለማየትና የእግዚአብሔርን መንገድ ለመከተል እንድትችሉ መጽሐፍ ቅዱስን አግኝታችሁ እንድታነቡት እንጋብዛችኋለን፤ ስለዚህም ኑ! ኦ ወደ ጌታ ቃል ኑ! ጌታም በእውነቱና በኃይሉ አዲስ ሕይወት የምታገኙበትን መንገድ ያሳያችኋል በንስሐም ወደ ምህረቱ ብትመጡ ስለ እናንተ በሞተው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል አዲስን ሕይወት ይሰጣችኋል፡፡ ጌታ እግዚአብሔር በምህረቱና በፀጋው ይርዳችሁ አሜን፡፡

የትርጉም ምንጭ: How Neil Armstrong "became" a Muslim

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ