ሴቶች ቦታ በንፁህ እስልምና

ክፍል ሁለት - የሴቶች ጉድለቶች

[ክፍል አንድ] [ክፍል ሦስት] [ክፍል አራትና አምስት] [ክፍል ስድስት] [ክፍል ሰባትና ስምንት] [ክፍል ዘጠኝ] [ክፍል አስር]

M. Rafiqul-Haqq and P. Newton

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

 

1. ቶች በእውቀትና በሃይማኖት ጎደሎዎች ናቸው

የሴት የአዕምሮና የሃይማኖት ጉድለት በሚከተለው በሳሂህ አል-ቡካሪ ሐዲት ውስጥ ተጠቅሷል፣ ይህም ሐዲት በሙስሊም ሊቃውንት ዘንድ ‹ከአላህ መጽሐፍ (ከቁርአን) ቀጥሎ እጅግ በጣም ታማኝ ነው› የሚባለው ነው Sahih Bukhari, Arabic-English translation, vol. 1, Introduction, p. xiv.፡፡

‹የአላህ ሐዋርያ አንድ ጊዜ ለተሰበሰቡ ሴቶች እንዲህ አለ፡ ‹በእውቀትና በሃይማኖት ከእናንተ ይልቅ ጎዶሎ የሆነ አላጋጠመኝም፡፡ ከእናንተ በአንዳንዶቻችሁ በጣም ጠንቃቃ የሆነ ጨዋ ሰው ሊሳሳት ይችላል፡፡› ሴቶቹም ጠየቁ፡ ‹ኦ የአላህ ሐዋርያ በእኛ እውቀትና ሃይማኖት ውስጥ ምንድነው የጎደለው?› እርሱም አለ፡ የሁለት ሴቶች ማስረጃ ከአንድ ወንድ ምስክርነት ጋር እኩል አይደለምን? እነሱም በማረጋገጥ መለሱ፡፡ እርሱም አለ፡ ‹ይህ ነው የእናንተ እውቀት ጉድለት› ... ‹ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መፀለይም ሆነ መፆም የማትችል መሆኗ እውነት አይደለምን?› ሴቶቹም በማረጋገጥ መለሱ፡፡ እርሱም አለ፡ ‹ይህ ነው በሃይማኖት ያላችሁ ጉድለት› Sahih Bukhari, Arabic-English translation, vol. 1,  Hadith No. 301. See also vol. 3, Hadith No. 826.፡፡

ከዚህ በላይ የተጠቀሰው ሐዲት እውነተኛነት ምንም ጥያቄ ውስጥ አልገባም፡፡ በጣም ታማኝነት ባላቸው ሁለት የሐዲት ስብስቦች ማለትም በቡካሪና በሙስሊም ላይም ተጠቅሷል፡፡ በዚህ ሐዲት ታማኝነት ላይ የቡካሪና የሙስሊም ስምምነት ይህንን ሐዲት (mutafaqun 'alayhi) ወይንም ‹የተመሰከረለት› አድርጎታል፣ ይህም በጣም ከፍተኛ ደረጃ ያለው ተቀባይነት አለው ማለት ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ሐዲት በጣም በታወቁት ሊቃውንት ተቀባይነት ያለው እና አገልግሎት ላይ የዋለ ነው ለምሳሌም እንደ ጋዛሊ፣ ኢብን አል-አራቢ፣ ራዚ፣ ሱዩቲ፣ ቆርቶቢ፣ ናዋዊ እና ኢብን ካታር እንዲሁም በጽሑፎቻቸው ውስጥ፡፡

ከላይ ያለው ሐዲት የሚናገረገው ከእስልምና በፊት የሆነውን የሴቶችን ሁኔታ ሳይሆን የሁል ጊዜ ገለጣውን ነው፣ ስለዚህም ‹ሴቶች በወር አበባቸው ወቅት አይፆሙም ወይንም አይፀልዩም› እንዲሁም እስከ አሁን ‹የሁለት ሴቶች ማስረጃ እንደ አንድ ወንድ ማስረጃ ነው የሚታየው›፡፡ ይህ አነጋገር የጊዜው ብቻ ሳይሆን ከቁርአን የተወሰደ፣ በጥልቅ የተመሰረተና እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ የሚቀጥል ነው፡፡

‹ለናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ታምራቶች አልሉ› የሚለውን የቁርአንን 30.21 ጥቅስን ሲተነትን ራዚ የተናገረው እንደሚከተለው ነው፡

የእሱ አባባል ‹ለእናንተ ... መፍጠሩ› የሚለው ሴቶች የተፈጠሩት እንደ እንሰሳትና እፀዋት እንዲሁም እንደ ሌሎች ጠቃሚ ነገሮች ነው፣ ልክ ታላቁ እንደተናገረው ‹በምድር ላይ ያለውን ለእናንተ ፈጠረው› እናም ያ ነው ሴት ከአምልኮና ለመለኮት የሚሆን ትዕዛዛትን ለመፈፀም እንዳትፈጠር ያደረጋት፡፡ እኛም የምንለው ሴቶችን መፍጠሩ በእኛ ላይ ከተሰጡት ፀጋዎች አንዱ ነው እንዲሁም እነሱን በመለኮት ትዕዛዛት ማዘዝ በእኛ ላይ ያለውን ፀጋ ይሞሉ ዘንድ በእኛ ላይ ነው ይሁን እንጂ እኛ ሃላፊነት እንደተሰጠን እነሱ አልተሰጣቸውም፡፡ እኛ እንደተሰጠን ሴቶች ብዙ ትዕዛዛትን አልተሰጣቸውምና፣ ምክንያቱም ሴቶች ደካማዎች ናቸው፣ የማይረቡ ናቸው በአንድ መንገድም እነሱ ልክ እንደ ሕፃን ናቸው እንዲሁም በህፃን ላይ ምንም ትዕዛዝ ሊጫን አይችልም ነገር ግን የአላህ ፀጋ በእኛ ላይ ይሟላ ዘንድ - ሴቶች መታዘዝ አለባቸው ይህም እነሱ የፍርድን ቅጣት ይፈሩ ዘንድ እና ባሎቻቸውን ይከተሉ ዘንድ ነው እንዲሁም ከተከለከለው እንዲርቁ ነው ይህ ካልሆነ ግን ዓመፀኝነት ይዛመታል› At-Tafsir al-Kabir, Razi, commenting on Q. 30:21.፡፡

ሌላው ታዋቂ የሙስሊም ፈላስፋ፣ ሃዲ ሳባዝቫሪ፣ በሳድር አል-ሞቴያልሂን ትንተና ላይ፡

‹ሳድር አድ-ዲን ሺራዚ ሴቶችን እንደ እንሰሶች መመደቡ ሴቶች ለሆኑት እውነታ ብልህ የሆነ ጥቆማ ነው፣ በእውቀት ጉደለታቸው እና ውስብስብ ነገሮችን የመረዳት ጉድለታቸው እንዲሁም ለዓለም መቆነጃጀት ላላቸው ናፍቆት (ጉጉት) በእውነትና በትክክል እነሱ ከማይናገሩት እንስሶች መካከል ናቸው፡፡ እነሱ የአራዊት ተፈጥሮ አላቸው፣ ነገር ግን እነሱ የሰው ልጆች ማሳሳቻነት ተሰጥቷቸዋል ስለዚህም ወንዶች ከእነሱ ጋር ለመነጋገር አይታክቱም እንዲሁም ከእነሱ ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነትን ለማድረግ ይገደዳሉ፡፡ ለዚህ ነው የእኛ እንከን የሌለው ሕግ (ሻሪና አል-ሙታሃር) ለወንዶች የሚያደላውና በብዙዎቹ ነገሮች ላይ ለእነሱ የበላይነትን የሰጣቸው፣ ፍቺንም ጨምሮ ወ.ዘ.ተ፡፡ (Quoted in Soroush, Abdolkarim, _Farbehtar az ideoloji_, Sera^t, Tehran, 1373 A.H.S.). [A.H.S. = After the Hegira, in Solar years]፡፡  

ከዚህ በላይ ያለው ተቀባይነት ካለውና ሴቶች በእውቀትና በሃይማኖት ደካማዎች ናቸው ከሚለው ሐዲት ጋር የሚስማማ ነው፡፡ ይህ እምነት ባለፉት አስራ ሦስት መቶ ዓመታት ውስጥ ሁሉ ባሉት በሙስሊም ሊቃውንትና ጸሐፊዎች ዘንድ ተቀባይነት አለው፡፡

አንድ ዘመናዊ ጸሐፊ እንዲህ አለ፡ ‹የሴት የእውቀት ድርሻ ከወንድ ደረጃ አይደርስም› Al-Islam wa-l-Mar'ah al-Mu'aserah, Al-Bahi al-Khuli, Dar al-Qalam, Quwait, 1984, p. 241.፡፡ ከዚያም እርሱ የሚከተለውን መናገርን በመቀጠል ‹አል-አካድ በጣም ታወቂ ከሆኑት የአረብ ጸሐፊዎች አንዱ ‹አል- ማራህ ዋል ቁርአን በሚባለው መጽሐፉ ውስጥ፣ ‹በጣም ውድ የሆነ ምዕራፍ አለው በዚያም አካድ የወንዶችንና የሴቶች የእውቀት እኩልነት አፈራርሶታል› Al-Islam wa-l-Mar'ah al-Mu'aserah, Al-Bahi al-Khuli, Dar al-Qalam, Quwait, 1984, p. 241. እንደ እውነቲ ከሆነ "naqisatan 'aqlan wa dinan" ማለትም (በእውቀትም በሃይማኖትም ጎደሎ) የሚለው አባባል በአረብ አገሮች ውስጥ ባሉ በብዙዎች አንደበት ከሚነገሩት የተለምዶ ቃላትና የሕይወት ዘይቤ መግለጫዎች አንዱ ነው፡፡

2. ሴቶች በምስጋና ጎደሎ ናቸው

ሴቶች ጎደሎ የሆኑት በእውቀት ብቻ ሳይሆን፣ እነሱ ምስጋናም ይጎድላቸዋል፡፡ የሴቶች ምስጋና ቢስነት ከቡካሪ በሆነው በሌላው ሐዲት ውስጥ እንደሚከተለው ተገልጧል፡

‹ሴቶች ለባሎቻቸው ምስጋና ቢሶች ናቸው እንዲሁም ለእነሱ ለተደረገው ሞገስ እና በጎ ስጦታ ሁሉ ምስጋና ቢሶች ናቸው፡፡ ከእነሱ ለአንዷ ደግ ብትሆኑ ከዚያም በእናንተ ውስጥ አንድ የማትወደውን ነገር ነው እርሷ የምትፈልገው ከዚያም እርሷ እንዲህ ማለትም ‹ከአንተ ምንም መልካምን ነገር በፍፁም አልቀበልም› ትላለች፡፡ Sahih Bukhari, Arabic-English translation, vol. 1 Hadith No. 28፡፡ ስለዚህም በዚህ ሐዲት መሠረት ሴቶች በእውቀትና በሃይማኖት ብቻ ሳይሆን በምስጋናም የጎደሉ ናቸው፡፡

3. ሴቶች እንደ ምስክሮች ጎደሎዎች ናቸው

የሴት ምስክርነት ከወንድ እኩል አይደለም፡፡ የገንዘብ ጉዳዮችን በተመለከተ የእሷ ምስክርነት ከአንድ ወንድ በግማሽ ያነሰ ነው፡፡ ቁርአን ይህን በተመለከተ የሚከተለውን ይናገራል፡

‹ከወንዶቻችሁም ሁለት ምስክሮች አስመስክሩ፣ ሁለትም ወንዶች ባይሆኑ ከምስክሮች ሲሆኑ ከምትወድዱዋቸው የሆኑን አንድ ወንድና አንደኛዋ ስትረሳ አንደኛይቱ ሌላዋን ታስታውሳት ዘንድ ሁለት ሴቶች (ይመስክሩ)፤› ቁርአን 2.282፡፡

አንዲት የተማረች ሙስሊም ሴት የሴቶች ምስክርነት ለምን የወንዶችን ግማሽ ሆነ የሚለውን ለመግለጥ ስትሞክር እንደሚከተለው ብላለች፡

‹ሴቶች የተሰሩት ልጆችን ለመመገብና ለመሸከም ነው፡፡ ስለዚህ እርሷ በጣም ስሜታዊ ናት፡፡ እንዲሁም እርሷ የምትረሳ ናት፣ ምክንያቱም መውለድ እንዴት እንደነበረ ባትረሳ ኖሮ ሌላ ልጅ አይኖራትም ነበር፡፡ ለዚህ ነው እርሷ እንደ ወንድ ለምስክርነት ልትታመን የማትችለው› The Age, Life behind a veil of Islam, 3/3/1992, p.11. This lady has an arts degree and post-graduate diploma in education፡፡

ስለዚህም በእስልምና፣ ሴት በሦስት በጣም ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ጎደሎ ሆና ነው የምትታየው፣ የወንድን ደግነት ለሌሎች በመካዷ፣ ለእራሷ ደግሞ በአውቀት ጎደሎ በመሆኗ፣ እንዲሁም እግዚአብሔርን በተመለከተ በሃይማኖት የጎደለች በመሆኗ ነው፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

ሴቶች በንፁህ እስልምና ውስጥ በሚለው በዚህ አጫጭር ጽሑፎች ውስጥ፣ ከዚህ በላይ ያለው ክፍል ሴቶች ከወንዶች በአዕምሮ እንዲሁም በሃይማኖት የጎደሉ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በዚህ የቁርአን እንዲሁም የእስልምና ትምህርት ዘመናዊ የሙስሊም ምሁራን እንዲሁም ምሁራን ሴቶችም ይስማማሉ፡፡ እንዲያውም ከሙስሊም ምሁራን ሴቶች አንዲቷ በሰጠችው አስተያየት ሴት ለምስክርነት የማትበቃው ስለምትረሳ፣ በተለይም መውለዷን መርሳቷን ለዚህ ዋና ዋቢ አድርጋ አቅርባለች፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ትልቅ ጥያቄ የሚሆነው፣ ነገሩ ትክክል ነው? ወይ የሚለው ነው፡፡ የዚህ ገፅ አዘጋጆች አሁንም ደግመን  የምናሳየው ነገር ይህ በሴቶች ላይ ያለው የእስልምና አመለካከት ትክክል አለመሆኑን ነው፡፡ ማስረጃችንም የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሴቶች የሚናገረው ነገር ነው፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ሴቶች በአዕምሮም በሃይማኖትም ጎደሎ ተደርገው አልተቆጠሩም፡፡ ወንዶች ለሴቶች እንክብካቤን ማድረግ እንደሚገባቸው፣ እንዲወዷቸው፣ አብረዋቸው የመንግስተ ሰማይ ወራሾች እንደሆኑ በመደጋገም ይናገራል፡፡

ወንዶች ለሴቶች መልካም የሆነ አመለካከት እንዳላቸው ሁሉ፣ ሴቶችም ባሎቻቸውን እንዲያከብሩ እንዲታዘዙ እና እግዚአብሔራዊ ሕይወትን እንዲኖሩ ይመክራቸዋል፡፡ የሴቶች ጉድለት የተነገረው ከወንዶች ጉድለት ጋር እኩል ሆኖ ነው፡፡ ይህም ሁለቱም በተፈጥሮ ኃጢአተኞችና ያለ እግዚአብሔር የኃጢአት ይቅርታ መንገድ ጎደሎ መሆናቸው ነው፡፡ ሴቶችም ወንዶችም በአዕምሮም በሃይማኖትም እኩል ጎደሎዎች ናቸው፡፡ ይህ ጉድለታቸው የሚሞላው በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ወደ እግዚአብሔር ሲቀርቡ እና ከእርሱ ዘንድ ምህረትን ሲቀበሉ ብቻ ነው፡፡

የዚህ ገፅ አዘጋጆች ይህንን የምስራች ዜና ለአንባቢዎች እናስተላልፋለን፡፡ የሰው ልጅ በሙሉ በኃጢአተኝነቱ ከእግዚአብሔር ክብር ጎድሎ የወደቀ ነው፡፡ ወደ ቀደመው ክብሩ የሚመለሰው በክርስቶስ ሞት አማካኝነት በተሰጠው የነፃ ይቅርታ ብቻ በኩል ነው፡፡ ስለዚህም ወደዚህ እንድትመጡ እንጋብዛችኋለን፣ እግዚአብሔርም ሊቀበላችሁ ዝግጁ ነውና ወደ እርሱ ምህረት በክርስቶስ በኩል ቀርባችሁ ምህረትን እንዲሰጣችሁ ለምኑት ጌታም ይቀበላችኋል የመንግስቱም ወራሾች ያደርጋችኋል፣ እርሱ በምህረቱና በፀጋው ይርዳችሁ፣ አሜን፡፡

 

ወደ ክፍል ሦስት ይቀጥሉ።

የትርጉም ምንጭ:  The Place of Women in Pure Islam  

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ