ሴቶች ቦታ በንፁህ እስልምና

ክፍል ሦስት - ሴት ምንድናት?

[ክፍል አንድ] [ክፍል ሁለት] [ክፍል አራትና አምስት] [ክፍል ስድስት] [ክፍል ሰባትና ስምንት] [ክፍል ዘጠኝ] [ክፍል አስር]

M. Rafiqul-Haqq and P. Newton

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

ሴት አሻንጉሊት ናት

ሴቶች የወንድ ጓደኛ ከመሆን የምትጎድልበት ጉድለት ከዚህ በፊት ተጠቅሷል፡፡ በእውቀት እና በሃይማኖት ላይ ያላት የእርሷ ጉድለት ዓለማዊና ቅዱስ በሆኑ፣ ወይንም በሃይማኖትና በሌሎች ጉዳዮችና ሐሳቦች ላይ እንዳትሳተፍ ያግዳታል፡፡ የእነዚህ ጉድለቶች መጠቀስ ሴቶችን ያዋረዳቸው ወይንም ዝቅ ያደረጋቸው እስከምን ድረስ ነው?

ኦማር (ከካሊፋቶች አንዱ) አንድ ጊዜ ሚስቱ በነገር ጣልቃ ገብታ በነበረበት ጊዜ ለእርሷ እንደሚከተለው አላት፡- ‹አንቺ አሻንጉሊት ነሽ፣ ከተፈለግሽ እንጠራሻለን፡፡› 21. Al-Musanaf by Abu Bakr Ahmad Ibn 'Abd Allah Ibn Mousa Al-Kanadi who lived 557H., Vol. 1 Part 2, p. 263. See also Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p. 52.

እንዲሁም ሌላው ካሊፍ የነበረው አምሩ ቢን አል-አስ ስሴቶች የተናገረው የሚከተለውን ነበር፡- ‹ሴቶች አሻንጉሊት ናቸው ስለዚህም ምረጥ› በማለት ነው፡፡ Kanz-el-'Ummal, Vol. 21, Hadith No. 919፡፡

ሴቶች አሻንጉሊቶች ናቸው የሚለው ይህ ሐሳብ የአምሩ ቢን አል-አስና የኦማር ብቻ ሳይሆን የመሐመድም የራሱም ሐሳብ ጭምር ነበር፣ እርሱም የተናገረው እንደሚከተለው ነው፡- ‹ሴት አሻንጉሊት ናት እርሷን የወሰዳት ማንም ቢኖር ለእርሷ ጥንቃቄን ያድርግላት› Tuffaha, Ahmad Zaky, Al-Mar'ah wal-Islam, Dar al-Kitab al-Lubnani, Beirut, first edition, 1985, p. 180፡፡

በታላቁ የሙስሊም ፈላስፋ ጋዛሊ መሠረት ደግሞ ሴት አሻንጉሊት ናት ብሎ ማመን ለወንዶች መንፈሳዊ ጤናነት በጣም ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ ‹ከሴቶች ጋር በሚኮንበት፣ እነሱን በመመልከት እና ከእነርሱ ጋር በመጫወት ጊዜ፣ ነፍስ ትነቃቃለች፣ ልብም ያርፋል እናም ወንድም እግዚአብሔርን ለማምለክ በጣም ይጠነካከራል ለዚህ ነው እግዚአብሔር የተናገረው፡ ‹እርሱ በእርሷ ያርፍ ዘንድ› በማለት ቁርአን 7.189፡፡ Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p. 34፡፡

ሴት አውራህ ናት

ከሴት ጎዶሎነት ባሻገር እርሷ አስር ‹አውራት› አላት፡፡ የእስላም ኢንሳይክሎፒዲያ ‹አውራት› ወይንም ‹አውራህ› የሚለውን ቃል የሚተረጉመው እንደ ‹ፑደንደም› ነው በማለት ነው፡፡ የፑደንደም ትርጉም ደግሞ የሴት የግብረ ስጋ ግንኙነት ብልት ውጫዊ አካል ነው›፡፡ (ፑንደም የሚለው ቃል የላቲን ቃል ሲሆን ቃል በቃል ሲተረጎም የሚታፈርበት ነገር ማለት ነው) The World Book Dictionary፡፡

መሐመድ ስለዚህ የተናገረውን አሊ እንደሚከተለው ዘግቦታል፣ ነቢዩ አለ፡- ‹ሴት አስር አውራት አላት፡፡ ስታገባ ባሏ አንዱን ይሸፍነዋል ስትሞት ደግሞ መቃብር አስሩንም ይሸፍነዋል›፡፡ Kanz-el-'Ummal, Vol. 22, Hadith No. 858. See also Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p. 65፡፡

በሚቀጥለው ሐዲት መሠረት ደግሞ፣ ሴቶች አስር አውራት ብቻ ሳይሆን ያላቸው ነገር ግን ሴት እራሷ እንደ አውራት እንደምትቆጠር ነው፡፡ ‹ሴት አውራህ ናት፡፡ እርስዋም ከቤት ወደ ውጪ ስትወጣ ሰይጣን (እንኳን ደህና መጣሽ በማለት ይቀበላታል› Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p. 65. Reported by Tirmizi as a true and good Ahadith፡፡ (ይህ ሐዲት የሚመደበው ሣሂህ ተብሎ ሲሆን እርሱም ጤናማና ምንም ስህተት የሌለበት ተብሎ የሚታመን ነው)፡፡ ስለዚህም በዚህ ሐዲት መሠረት አንዲት ሴት ከቤት ወደ ውጪ መውጣቷ አውራህን የማጋለጥ መንገድ ነው ማለት ነው፣ ይህ ደግሞ ሰይጣንን የሚያስደስት ነገር ነው ማለት ነው፡፡

ለዚህ ነው ሴቶች ከቤት ወደ ውጪ እንዳይሄዱ የሚበረታቱት፣ ወደ መስጊድም ስለመሄድም እንኳን የሚከተለው ሐዲት እንደሚከተለው ይናገራል፡- ‹ሴት በቤቷ ማዕከል ውስጥ እስካለች ድረስ ለእግዚአብሔር ፊት በጣም ቅርብ ናት፡፡ እንደዚሁም ደግሞ በቤት ውስጥ የሚደረገው የሴት ፀሎት በመስጊድ ከምታደርገው ፀሎት የተሻለ ነው› Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p. 65. Reported by Tirmizi as a true and good Ahadith፡፡ (ይህ ሐዲት የሚመደበው ‹ሃሳን› ከሚባሉት ነው እናም ተቀባይነት ያለው ነው)፡፡

ዘመናዊ የእስልምና ሊቅ የሆነው ዶክተር ቡቲ እንደተናገረው፡- ‹በየትኛውም ትውልድ ያሉ የሙስሊም አስተማሪዎች በአንድነት የሚስማሙት ሴት ከእጆቿና ከፊቷ በስተቀር ሞላ አካሏን እንድትሸፍን ነው፣ ፊቷም ከእንግዶች ፊት መታየት ያለበት ያለምንም ሜክአፕ ሆኖ ነው› Dr. Mohammad Sa'id Ramadan al-Buti, Ela kul Fataten Tu'min be-Allah, Mu'asasat ar_Risalah, Beirut, 1987, Eighth edition, p. 41,42፡፡ ምንም እንኳን የሀንባል እና የሻፍ ተከታዮች እጅንና ፊትን አውራህ ነው ስለዚህ መሸፈን አለበት በማለት ቢቆጥሩም› ገፅ 43፡፡

‹እነዚያ ሴት እጆቿንና ፊቷን እንድትሸፍን የሚፈቅዱት - ማሊኪያ እና ሃኒፊያ - የሚያደርጉት ምንም የውበት መስጫ ነገርን ሳይጠቀሙ ነው፣ ነገር ግን የሴት ፊት በተፈጥሮ ውብ ከሆነ ግን ለወንዶች ፈተና እንዳትሆን እርሷ መሸፈን አለባት› ገፅ 47፣ 48፡፡

ዶክተር ቡቲ በሂጃብ የመሸፈንን መሰረታዊ ምክንያት ሰጥቷል፡

‹በጣም ታላቁ አላህ ሴት መሸፈን እንዳለባት ወስኗል፡፡ ይህንንም ያደረገው እሷን የሚመለከቱትን የወንዶችን ንፅህና ለመጠበቅ በማለት ነው እንጂ ወደ እርሷ ከሚመለከቱት ከወንዶች ዓይኖች የሴቶችን ንፅህና ለመጠበቅ በማለት አይደለም› ገፅ 98፡፡

ሴት እንደ - የጎድን አጥንት - ናት

የሴቶች ባህርይ ልክ ከጎድን አጥንት ጋር ተመሳስሏል፡፡ ይህንን በተመለከተ ቡካሪ በሐዲት ውስጥ የሚከተለውን ሪፖርት አድርጓል፡

‹ሴት ልክ እንደ ጎድን አጥንት ናት፣ ልታቃኗት ብትሞክሩ ትሰበራለች፡፡ ስለዚህም ከእርሷ ዘንድ አንድ ጥቅምን ለማግኘት የምትፈልጉ ከሆነ ማድረግ ያለባችሁ ጠማማነት በእርሷ ውስጥ እንዳለ ነው› Sahih Bukhari, Arabic-English translation, vol. VII Hadith No. 113፡፡ ይህ ሐዲት የሚታየው ተቀባይነት ያለው ተደርጎ ነው፡፡

ሌላው ሐዲት ለዚህ የጠማማነት ተፈጥሮ ተጨማሪ እስተዋፅዖን የሰጠው ሴት ከጎድን አጥንት ስለተፈጠረች ነበር ይላል Sahih Bukhari, Arabic-English translation, vol. VII Hadith No. 114፡፡ ይህ ጠማማነት ስለዚህም የተፈጥሮ ውስጥ እና በፍፁም የማይድን ነው፣ ወንድ ከዚህ ጠማማነት ጋር መኖርና ከእዚህም ጠማማነት ውስጥ የሚቻለውን ሁሉ ለማግኘት መሞከር አለበት፡፡ ይህ እምነት ተቀባይነት ያለው በአጠቃላይ ብዙዎች ዘንድ ብቻ ሳይሆን በጣም በታወቁት ሊቆችም ነው ለምሳሌም እንደ ኢማም ሻፊ ባሉትም ዘንድ ነው እሱም እንደሚከተለው ብሏል፡

‹ሦስት ሰዎች ብታከብሯቸው ያዋርዷችኋል እንዲሁም ደግሞ ብታዋርዷቸው ያከብሯችኋል እነሱም ሴት፣ አሽከር (ሰራተኛ) እና ናባትያ ናቸው› Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p. 51፡፡

እንዲሁም ጋዛሊ የተናገረው፡

‹የሴትን ልጓም ለጥቂት እንኳን ላላ ብታደርጉት ትወስዳችሁና እንደ አራዊት ትደነብራለች፡፡ የማገቻውን ገመድ አንድ ስንዝር ያህል ወረድ ብታደርጉት ደግሞ እርሷ አንድ ክንድ የሚሆንን ርዝመት ትጎትታችኋለች ... ማታለላቸው ደግሞ መጠን የለውም ክፋታቸውም ተላላፊ ወይንም ሌላውን ሁሉ የሚበክል ነው፣ ክፉ ባህርይና ደካማ አዕምሮ የተለመደ ዋና ባህርያቸው ነው ... መሐመድ አለ› The authority of that Hadith is classed as Sahih. It is quoted by Ahmad and al-Nisa'i፡፡ ‹ከሴቶች መካከል የጥሩ ሴት ምስያ ከመቶ አውራ ዶሮዎች መካከል ቀይ መንቆር (አፍ) እንዳለው አውራ ዶሮ የሚመስል ነው፡፡› Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p. 51፡፡ ስለዚህም የሚታመነው የጎድን አጥንት ጠማማነት የተፈጥሮ እንደሆነው ሁሉ ጥሩ ሴቶች እና የእነሱም ጠማማነት ተፈጥሮአዊ ነው፡፡

ከእነዚህ ሁሉ ጉድለቶች ባሻገር ጋዛሊ ጥቂት የሚያድኑ ባህርያትን በሴቶች ውስጥ አግኝቷል፡ ‹(የአንድ ወንድ ሚስት) እርሱን ትፈራዋለች፣ እርሱ እርሷን ሳይፈራ፣ የእርሷ ምንም ነገር ለእርሱ ምንም ጠቃሚ ባልሆነበት ጊዜ፤ ከእርሱም ዘንድ መልካም ቃላት እርሷን ያረካታል፣ እርሷ ናት የቅምጦችን መኖር መታገስ ያለባት፣ የእርሷ መሞት እርሱን ግዴለሽ ሲያደርገው እርሱ ሲታመም መጨነቅ ያለባት እርሷ ናት› Al-Ghazali, Nasihat al-Muluk, as quoted in: Essid, Yassine, A critique of the origins of Islamic economic thought, E.J. Brill, Leiden, New York, Koln, 1995, p. 205፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

የእስልምና እምነት ለዘመናት ስለሴቶች የሚከተለውንና የሚያስተምረውን አመለካከት ከዚህ በላይ የሰፈረው ጽሑፍ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል፡፡ እስልምና በሴቶች ላይ ያለው ይህ አመለካከት ትክክለኛ ምንጩ ምንድነው? መልስ ለመስጠት የሚረዳ ፍንጭ ለመጠቆም ያህል የሚከተሉትን ሁለት ሐሳቦች መሰንዘር ይቻላል፡፡ እስልምና በሴቶች ላይ ያለው አመለካከት ምንጩ እግዚአብሔር አምላክ ነው ወይንስ የሰዎች (ማለትም ጥንታዊ የፓጋን አረቦች) ባሕል ነው?

ፈጣሪ አምላክ ያለውን የፈጣሪነት ባህርይ በደመ ነፍስ እንኳን የሚያስብ ማንም ሰብአዊ ፍጡር ቢኖር እስልምና ለሴቶች ያለው አመለካከት ከእግዚአብሔር እንዳልመጣ ያውቀዋል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር፣ በፆታ፣ በመደብ፣ በቀለም እና በዕድሜ ልዩነት፣ በሰዎች መካከል መበላለጥንና አድልዎን አያደርግም፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ የሚናገረው ሰዎች ሁሉ ያለምንም የፆታ ልዩነት ኃጢአተኞች መሆናቸውን ነው፡፡ ‹ልዩነት የለምና ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሏቸዋል› ሮሜ 3.23 በማለት ይናገራል፡፡ ሁሉም ሴቶችም ወንዶችም ኃጢአትን ስለሠሩ በእግዚአብሔር ፍርድ ውስጥ ናቸው፡፡ ሁለቱም በኃጢአታቸው ተፀፅተው ንስሐ በመግባት፣ እግዚአብሔር ባዘጋጀው የመዳን መንገድ፣ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በመታመን ወደ እርሱ ቢመጡ፣ ያለምንም የፆታ ልዩነት የኃጢአታቸውን ይቅርታ በነፃ ማለትም በእግዚአብሔር ፀጋ በማግኘት የመንግስቱ ወራሽ የመሆን መብት ይሰጣቸዋል፡፡ ይህንንም መጽሐፍ ቅዱስ እንሚከተለው ይገልጠዋል፡ ‹አይሁዳዊ ወይንም የግሪክ ሰው የለም፣ ባሪያ ወይንም ጨዋ ሰው የለም፣ ወንድም ሴትም የለም፣ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና› በማለት ገላትያ 3.27 ላይ፣ ይናገራል፡፡

ይሁን እንጂ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች እግዚአብሔር ባዘጋጀው የደኅንነት መንገድ ወደ እርሱ ባይመጡ ሁለቱም ያለምንም የፆታ ልዩነት ለዘላለም በዚያ ለመሰቃየት ወደ ሲዖል ይሄዳሉ፡፡

የዚህ ገፅ አዘጋጆች ትልቅ ዓላማ ሙስሊሞች ይህንን እውነት እንዲያዩና ወደ እውነተኛው አምላክ በንስሐ ተመልሰው የእግዚአብሔርን ምህረት እንዲቀበሉ፣ ለዘላለምም በመንግስተ ሰማይ ከእርሱ ጋር እንዲኖሩ ነው፡፡ ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ እና የወንጌል መልእክት ወደሚነገርበት ቤተክርስትያን በመሄድ የእግዚአብሔር የንስሐና የደህንነትን መንገድ እንድትገነዘቡ እንጋብዛችኋለን፡፡ እግዚአብሔር በፀጋው ወደ እውነቱ እንድትመጡ ይርዳችሁ አሜን፡፡

ወደ ክፍል አራትና አምስት ይቀጥሉ::

የትርጉም ምንጭ:  The Place of Women in Pure Islam  

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ